ኢፒኦ ከመጋቢት 23 እስከ ሚያዚያ 22, 2015 ወርሀዊ፡ የተቀረው የአገሪቱ ክፍል ሲረጋጋ በአማራ ክልል የተከሰተው አለመረጋጋት
ዘገባ በመጀመሪያ ላለመረጋጋት በኢትዮጵያ ውስጥ የፖለቲካ ውጊያዎች እንዴት እንደታየ ተረዥዕላል።
Also available in English
በዚህ ዘገባ ውስጥ የተካተቱ
- ከመጋቢት 23 እስከ ሚያዚያ 22 በጨረፍታ
- አበይት ክንውኖች
- ከመጋቢት 23 እስከ ሚያዚያ 22 ድረስ የተከሰቱ ቁልፍ ኩነቶች
- ወርሀዊ ትኩረት፡ የተቀረው የአገሪቱ ክፍል ሲረጋጋ በአማራ ክልል የተከሰተው አለመረጋጋት
ከመጋቢት 23 እስከ ሚያዚያ 22 በጨረፍታ
አበይት ክንውኖች
- ከመጋቢት 23 እስከ ሚያዚያ 22 ድረስ አክሌድ 37 የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች እና 69 ሪፖርት የተደረጉ ሟቾች መዝግቧል። ባለፈው ወር የፖለቲካ ግጭቶች መቀነሳቸውን የቀጠሉ ሲሆን ህዝባዊ ስልፎች ግን ጨምረዋል።
- ባለፈው ወር በአማራ ክልል ከፍተኛ ቁጥር ያለው ኩነቶች እና በፖለቲካ ግጭት ምክንያት ሪፖርት የተደረገ ከፍተኛ የሟቾች ቁጥር የተመዘገበ ሲሆን 26 ኩነቶች እና 47 ሪፖርት የተደረጉ ሟቾች ተመዝግቧል። ከ68% በላይ የሚሆነው በሃገሪቱ ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር የተመዘገበው በአማራ ክልል ነው።
- ከመጋቢት 23 እስከ ሚያዚያ 22 ባለው ጊዜ ውስጥ በጣም ተደጋግሞ የተከሰተው የኩነት ዓይነት ተቃውሞ ሲሆን 33 የተቃውሞ ኩነቶች ተመዝግበዋል። አብዛኛዎቹ የተመዘገቡት ተቃውሞዎች በአማራ ክልል ሲሆን እነዚህም መንግስት የክልል ልዩ ኃይልን ለመበተን ከያዘው እቅድ ጋር የተያያዙ ነበሩ።
ወርሀዊ ትኩረት፡ የተቀረው የአገሪቱ ክፍል ሲረጋጋ በአማራ ክልል የተከሰተው አለመረጋጋት
በኢትዮጵያ ያለው የፖለቲካ ብጥብጥ ከመጋቢት 23 እስከ ሚያዚያ 22 ባለው ጊዜ ውስጥም መቀነሱን የቀጠለ ሲሆን አክሌድ የሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት ከመጀመሩ በፊት ከመስከረም 2013 ቀጥሎ ዝቅተኛውን የፖለቲካ ግጭት ኩነቶችን በለፈው ወር መዝግቧል (ከዚህ በታች ያለውን ግራፍ ይመልከቱ)። ሰላምን ለማምጣት የሚደረጉ ጥረቶች የቀጠሉ ሲሆን ባለፈው ወር በጋምቤላ እና በኦሮሚያ ክልሎች በሚንቀሳቀሱ ታጣቂ ቡድኖች እና በመንግስት መካከል ውይይት መደረጉ ተገግሯል። ሆኖም የሀገሪቱ ልዩ ኃይል ወደ ተለያዩ የፀጥታ ማዋቅር እንዲዋሃድ የታቀደው እቅድ በአማራ ክልል ቅሬታን ያስናሳ ሲሆን በዚህም ምክንያት ሰልፎች እና ውጊያዎች በክልሉ ተቀስቅሷል። የአማራ ክልል የብልፅግና ፓርቲ ኃላፊ በወሩ መጨረሻ መገደሉ በአማራ ክልል በቀጣይ ወራቶች የበለጠ መጠነ ሰፊ አለመረጋጋት እንደሚኖር ሊያመላክት ይችላል።

በአማራ ክልል የታጠቁ አካላት፡ በአማራ ክልል ያለ አንድነት
የአማራ ክልል ልዩ ኃይል በአማራ ክልል ውስጥ የሚደረጉ የሸምቅ ውጊያ ሙከራዎችን በተለይም የራስ ገዝ አስተዳደር እንዲኖር የሚፈልጉ ብሔርተኛ ቡድኖችን በመቆጣጠር ከፍተኛውን ሚና ተጫውቷል። ከትህነግ/ህወሓት በተጨማሪ የአማራ ክልል ልዩ ኃይል በኦሮሚያ ልዩ ዞን ከኦሮሞ ብሔር ታጣቂዎች እና ከኦነግ-ሸኔ ታጣቂዎች ጋር፣ በጎንደር ከተማ አቅራቢያ ከሚገኙ የቅማንት ታጣቂዎች ጋር፣ ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ ደግሞ በክልሉ ምስራቅ አካባቢ ከሚገኙ የፋኖ ታጣቂዎች ጋር ውጊያ ሲያካሂድ ቆይቷል። ከአማራ ክልል ውጪ የአማራ ክልል ኃይሎች በቤንሻንጉል/ጉሙዝ ክልል – ብዙ የአማራ ተወላጆች በሚኖሩበት አካባቢ በመተከል ዞን15 – በሱዳን ድንበር እና በሰሜን በነበረው ግጭት በትግራይ ክልል በተከሰቱ ውጊያዎች ተሳትፈዋል። እንደሌሎች ክልል ልዩ ኃይሎች ሁሉ የአማራ ክልል ልዩ ኃይል በእነዚህ የፀረ-ሽምቅ ዘመቻዎች ወቅት የተለያዩ ከባድ ወንጀል በመፈፀም ተከሰዋል።