ኢፒኦ ከጥር 24 እስከ የካቲት 21, 2015 ወርሃዊ፡ የኃይማኖት አለመግባባቶች እና የመንግስት ጣልቃ ገብነት በኢትዮጵያ
የኢትዮጵያ ወርሃዊ ዘገባ በአንዳንድ እንቅስቃሴ በመግለጫ ይዝጋል
Also available in English
- ከጥር 24 እስከ የካቲት 21 በጨረፍታ
- አበይት ክንውኖች
- ከጥር 24 እስከ የካቲት 21 ድረስ የተከሰቱ ቁልፍ ኩነቶች
- ወርሀዊ ትኩረት፡ የኃይማኖት አለመግባባቶች እና የመንግስት ጣልቃ ገብነት በኢትዮጵያ
- አበይት ክንውኖች - አክሌድ ከጥር 24 እስከ የካቲት 21 ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ 41 የፖለቲካ ግጭት ኩነቶችን እና 268 ሪፖርት የተደረጉ ሟቾች መዝግቧል። ከባለፈው ወር ማለትም ከታህሳስ 23 እስከ ጥር 23 ካለው ጊዜ ጋር ሲነፃፀር ከተቃውሞ ስልፍ ኩነቶች በስተቀር የተመዘገቡ ሁሉም የኩነቶች ዓይነቶች ቁጥር ቀንሷል።
- ከጥር 24 እስከ የካቲት 21 ድረስ በፖለቲካ ግጭት ከፍተኛው የኩነት መጠን - በኦሮሚያ ክልል 31 ኩነቶች ሲመዘገቡ በአማራ እና በጋምቤላ ክልሎች በእያንዳንዳቸው ሦስት ኩነቶች በመመዝገብ የኦሮሚያ ክልልን ይከተላሉ። ከታህሳስ 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ኦሮሚያ በኢትዮጵያ በፖለቲካ ግጭት ምክንያት ከፍተኛውን የኩነት መጠን እያስመዘገበ ይገኛል።
- ተደጋጋመው የተከሰቱት የኩነት አይነትች - በሰላማዊ ሰዎች ላይ የተፈፀሙ ጥቃቶች እና ጦርነትሲሆኑ 22 በሰላማዊ ሰዎች ላይ የተፈፀመ ተስፋከቶች 17 የጦርነት ኩነቶች ተከስተዋል። ከባለፈው ወር ማለትም ከታህሳስ 23 እስከ ጥር 23 ካለው ጊዜ ጋር ሲነፃፀር የውጊያ ኩነቶች ቁጥር በ74% ቀንሷል። አብዛኛው በሰላማዊ ሰዎች ላይ የተፈፀመ የጥቃት በኦሮሚያ ክልል የተመዘገበ ሲሆን በኦሮሚያ ልዩ ኃይል የተፈፀሙ ናቸው ።

ወርሃዊ ትኩረት፡ የኃይማኖት አለመግባባቶች እና የመንግስት ጣልቃ ገብነት በኢትዮጵያ
በኢትዮጵያ በኃይማኖት ውስጥ በሚከሰቱ አለመግባባቶች ምክንያት አለመረጋጋት እየጨመረ መጥቷል። ከጥር 24 እስከ የካቲት 21 ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ አክሌድ የተለያዩ የኃይማኖት አካላት የተሳተፉበት 13 የግርግር ኩነቶችን መዝግቧል። አብዛኛው ኢትዮጵያዊ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ሲሆን ቀጥሎ ደግሞ ሙስሊም ነው። ከእነዚህ ኃይማኖቶች ጋር በተያያዘ በቅርቡ የተከስቱ ግጭቶች መንግሥት በኃይማኖት ጉዳዮች ላይ ጣልቃ መግባቱ ከኃይማኖት ጋር የተያያዙ አለመግባባቶችን ከመፍታት ይልቅ እንዴት የበለጠ እንደሚያቀጣጥለው ያሳያል። ይህ ሪፖርት መንግሥት በኃይማኖት ጉዳዮች ላይ ያለውን ጣልቃ ገብነት እና ግጭቶቹ ሊባባሱ የሚችሉበት ሁኔታዎችን ጨምሮ የእነዚህ አለመግባባቶች ዋና መንስኤዎችን የተነትናል።
ባለፈው ወር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን (ኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ) ውስጥ የተፈጠረውን የውስጥ አለመግባባት ተከትሎ በሀገሪቱ የኃይማኖት ውጥረት ነግሶ ነበር። አለመግባባቱ የጀመረው ጥር 14 ቀን ሲሆን ሊቀ ጳጳስ አቡነ ሳዊሮስ ከሌሎች ሁለት ሊቀነ ጳጳሳት ጋር በመሆን በኦሮሚያ ክልል በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ወሊሶ ከተማ በሚገኘው ሐሮ በዓለ-ወልድ ቤተ-ክርስቲያን 26 ጳጳሳትን በመሾም ከኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሲኖዶስ እውቅና ውጪ ‘የኦሮሚያ እና ብሔር ብሔረሰቦች ቅዱስ ሲኖዶስ’ መቋቋሙን ይፋ ባደረጉበት ወቅት ነው።1 ምእመናንን በቤተ-ክርስቲያን በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው በማገልገል ረገድ የነበረውን የቆየ ችግር ለመፍታት እነዚህ ሹመቶች አስፈላጊ መሆናቸውን አዲሱ ቡድን አስታውቋል። አዲሱ ሲኖዶስ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሲኖዶስ አመራሩን በአብዛኛው “ከአንድ ቡድን” በመሾም ሁሉንም ያሳተፈ መሆን አልቻለም ሲልም ከሷል።2 የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሲኖዶስ በበኩሉ አዲሱን ሲኖዶስ የቤተ-ክርስቲያኒቱን ቀኖና አልተከተለም ሲል የከሰሰው ሲሆን የኦሮሚያ እና ብሔር ብሔረሰቦች ቅዱስ ሲኖዶስን “ህገ-ወጥ” በማለት ሦስቱን ሊቃነ ጳጳሳት እና 25ቱን ጳጳሳት አግዷል።3 የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሲኖዶስ በአቡነ ሳዊሮስ ከሚመራው ቡድን ጋር የሚደረግ ድርድርን “በተዘዋዋሪ የቤተ-ክርስቲያናችንን ቀኖና መጣስ ነው” በሚል ድርድርን ህገ-ወጥ አድርጓል።4
መንግስት በዚህ ጉዳይ ጣልቃ በገባበት ወቅት በሀገሪቱ ውስጥ ያለው ውጥረት ይበልጥ ጨምሯል። የፀጥታ ኃይሎች በኦሮሚያ የሚገኙ የኦርቶዶክስ አብያተ-ክርስቲያናትን አዲስ ለተቋቋመው የኦሮሚያ እና ብሔር ብሔረሰቦች ቅዱስ ሲኖዶስ ለማስረከብ ፈቃደኛ ያልሆኑትን ሊቀነ ጳጳሳት፣ ጳጳሳት እና ምእመናን ማሰር ሲጀምሩ ሁኔታው ወደ ግጭት ተቀይሯል። በክልሉ የሚገኙ አብያተ-ክርስቲያናትን ለመቆጣጠር በተለያዩት ሲኖዶሶች መካከል በተፈጠረ ግጭት ቢያንስ ስምንት ሰዎች መሞታቸውና በርካቶች መቁሰላቸው ተነግሯል (ለተጨማሪ መረጃ ......

የኢትዮጵያ ህዝብ ኃይማኖተኛ ሲሆን በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ እና በሙስሊም ማህበረሰቦች ውስጥ የሚከሰቱ መከፋፈሎች ብዙ የሀገሪቱን ነዋሪዎች የሚነካ ስሜታዊ ጉዳይ ነው። በቅርቡ በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ውስጥ በተነሳው አለመግባባት እና ግጭት ብዙ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞች ቤተ-ክርስቲያንን እየጠበቁ ‘እንደ ቅዱሳን’ ለመሞት መዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል።5፣ ‘ሰማዕታት የዚችን ዓለም ጣዕም በእውነት ናቁ፤ ደማቸውን ስለ እግዚአብሔር አፈሰሱ፤ ስለ መንግሥተ ሰማያመራራ ሞትን ታገሱ፣” , የኢ’ ግርማ፣ ‘ኃይማኖት እና ማህበራዊ ለመ’ ማንሳ፣ “ወዲህ ይዞላጥና ነው፣” , በኢትዮጵያ ውስጥ በኃይማኖት መካከል የተፈጠረው አለመግባባት እንዲባባስ የፖለቲካ ተጽዕኖ እና ኃይማኖትን እንደ ፖለቲካ መሳሪያ መልካም ሚልኩን አዲአ ይፋ አደረጋል።6 ልቁያ
>