Skip to main content

ኢፒኦ ሳምንታዊ: ከግንቦት 12-18, 2015

Analysis of recent conflicts in Ethiopia including political and civilian impacts.

2 June 2023

Also available in English

  • የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች ብዛት: 1,104
  • በፖለቲካ ግጭቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 5,809
  • በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተሰነዘሩ ጥቃቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 2,581
  • የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች ብዛት: 19
  • በፖለቲካ ግጭቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 44
  • በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተሰነዘሩ ጥቃቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 38

ኢትዮጵያን በተመለከተ በቁጥር የተደገፉ መረጃዎችን ከኢፒኦ የመረጃ መዝገብ እንዲሁም በዋናው የአክሌድ ኤክስፖርት መሳሪያ ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።

የሁኔታዎች አጭር መግለጫ

በኦሮሚያ፣ በጋምቤላ እና በአማራ ክልሎች በሰላማዊ ሰዎች ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች እና ውጊያዎች ቀጥለዋል። በአዲስ አበባ የፀጥታ ኃይሎች ሙስሊም ተቃዋሚዎችን በኃይል አፈነዋል። ባለፈው ሳምንት አክሌድ በኦሮሚያ ውስጥ አምስት የውጊያ እና ስምንት በሰላማዊ ሰዎች ላይ ያነጣጠሩ የጥቃት ኩነቶችን መዝግቧል (ከዚህ በታች ያለውን ካርታ ይመልከቱ)። ሁሉም የተመዘገቡት ውጊያዎች በኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ)-ሸኔ እና በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መካከል የተደረጉ ሲሆን እነዚህ ውጊያዎች የተከሰቱት በጉጂ፣ ምዕራብ ጉጂ እና ምስራቅ ሸዋ ዞኖች ነው። በተለይም ከዚህ ቀደም ምንም አይነት የኦነግ-ሸኔ እንቅስቃሴ ባልተመዘገበባቸው ከተሞች ኦነግ-ሸኔ አዲስ እንቅስቃሴ ማድረጉን ቀጥሏል። አብዛኛዎቹ እነዚህ ጥቃቶች ከቡድኑ ጋር ግንኙነት ያላቸውን እስረኞችን የመፍታት አላማ ያላቸው ይመስላል። ለምሳሌ በግንቦት 12 ቀን ኦነግ-ሸኔ እንደሆኑ የተገመቱ የታጠቂ ቡድን አባላት በአርሲ ዞን በበቆጂ ከተማ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት የሰነዘሩ ሲሆን የአካባቢው ታጣቂዎች አሰልጣኝን ጨምሮ አራት ሰላማዊ ሰዎችን ገድለዋል። ቡድኑ በከተማው ከሚገኝ አንድ እስር ቤት እስረኞችንም ማስፍታት ችሎ ነበር።

አሁንም ውጥረቱ ከፍተኛ ቢሆንም የአማራ ክልል ባለፈው ሳምንት በአንጻራዊ ሁኔታ የተረጋጋ ነበር። ግንቦት 17 ቀን በምዕራብ ጎጃም ዞን ባህር ዳር ከተማ ሙሉ አለም አዳራሽ አካባቢ የከነማ እግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎች ክለባቸውን ለመደገፍ ወደ ሀዋሳ ለመጓዝ በአውቶብስ እየተሳፈሩ በነበሩበት ወቅት ማንነታቸው ያልታወቁ ሰዎች ሁለት የእጅ ቦንቦችን ወርውረዋል። በዚህ ጥቃት 23 ሰዎች ቆስለዋል።2 በማግስቱ በኦሮሚያ ልዩ ዞን ደዋ ሀሬዋ ወረዳ መልካ ዲዱ ቀበሌ የመንግስት ኃይሎች – የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና የአማራ ክልል ፖሊስ ኃይሎች – ከኦነግ-ሸኔ ጋር ተዋግተዋል። የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አንድ የኦነግ-ሸኔ አባል መግደሉን ሌላ አንድ የቡድኑን አባል ማቁሰሉን እና ሁለት የኦነግ-ሸኔ አዛዦችን መያዙን ገልጿል።

Country
Ethiopia
Region
Africa
Share on

Related content