Skip to main content

ኢፒኦ ሳምንታዊ: ከግንቦት 13 እስከ 19, 2014

የሳምንቱ ዘገባ በአማራ ክልል እና አዲስ አበባ ደቂቃ ህትመት ያስነቁት ነጥቦችን ጊሜደባ

2 June 2022

Also available in English

  • የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች: 2,957
  • በተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ህይወታቸው እንዳለፈ የተዘገቡ ሰዎች: 16,210
  • በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ በተቃጡ ጥቃቶች ህይወታቸው ያለፈ: 7,279
  • የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች: 10
  • በተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ህይወታቸው እንዳለፈ የተዘገቡ ሰዎች: 89
  • በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ በተቃጡ ጥቃቶች ህይወታቸው ያለፈ: 9

ኢትዮጵያን በተመለከተ በቁጥር የተደገፉ መረጃዎችን እዚህ፣ ሁሉንም የአክሌድ ስራዎች ደግሞ እዚህ ጋር በመጫን ያገኛሉ። 

ባለፈው ሳምንት በአማራ ክልል እና በዋና ከተማዋ አዲስ አበባ ጋዜጠኞችን ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ታስረዋል። መንግስት በሀገሪቱ “የህግ ማስከበር” ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን አስታውቋል። የፌዴራል ፖሊስ እና የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ በአዲስ አበባ ከ349 በላይ ሰዎችን በቁጥጥር ስር ማዋላቸው ተዘግቧል ። በቁጥጥር ስር የዋሉት ግለሰቦች በማህበራዊ ሚዲያ ሁከትን በመቀስቀስ፣ ከአል ሸባብ እና የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ)-ሸኔ ጋር ግንኙነት በመፍጠር እና በከተማዋ ሃይማኖትን መሰረት ያደረገ ረብሻ ለመፍጠር ማሴርን የመሳሰሉ የተለያዩ “የወንጀል ተግባራትን” በመፈጸም ተጠርጥረው ታስረዋል (የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ፣ ግንቦት 18, 2014)። ከአል ሸባብ ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉት 84 ሰዎች የታሰሩት ከሶማሌ ክልል ፖሊስ ጋር በመተባበር ነበር። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመጉ) እስከ ግንቦት 19 ድረስ በሀገሪቱ 18 ጋዜጠኞች እና የሚዲያ ሰራተኞች መታሰራቸውን ዘግቧል (የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን፣ ግንቦት 20, 2014)።

በመጨረሻም አንዳንድ ዘገባዎች በቤንሻንጉል/ጉሙዝ ክልል ካማሺ ዞን ከዚህ ቀደም አባላቱ እጃቸውን ለመስጠትና ጥያቄያውን በሰላማዊ መንገድ ለማቅረብ ተስማምቶየነበረ ማንነቱ ያልተጠቀስ ታጣቂ ቡድን አንዳንድ አባላት ተመልሰው ወደ ጫካ መመለሳቸውን አሳታውቀዋል (ኢሳት፣ ግንቦት 19, 2014)። መጋቢት 10 ላይ የክልሉ መንግስት እና የጉሙዝ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጉሕዴን) የፖለቲካ እና የትጥቅ ክንፍ አመራሮች በዞኑ ባህላዊ የሰላም እና የዕርቅ ሥነ-ሥርዓት አድርገዋል (ስለካማሺ ባህላዊ የሰላም እና የእርቅ ሥነ ሥርዓት የበለጠ መረጃ ለማግኘት ኢፒኦ ሳምንታዊ: ከመጋቢት 3, 2014 እስከ መጋቢት 9, 2014 ይመልከቱ)። ወደ ጫካ ለመመለስ የወሰኑት የጉሕዴን አባላት ይሁኑ አይሁኑ ከሆኑም ለምን ወደጫካ ለመመለስ እንደወሰኑ ግን ግልጽ አይደለም። ቀደም ሲል በክልሉ ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተደረጉ የተለያዩ ሙከራዎች አልተሳኩም። ባለፈው ሳምንት የጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት  “በዚህ ቡድን ላይ አስፈላጊውን እርምጃ ሁሉ” ሊወስድ እንደሚችል አስጠንቅቀዋል (ኢሳት፣ ግንቦት 19, 2014)።

    Country
    Ethiopia
    Region
    Africa
    Share on

    Related content