Update
ኢፒኦ ሳምንታዊ: ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3, 2014
Summary of conflict events and political issues in Ethiopia.
Also available in English
- የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች: 3,000
- በተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ህይወታቸው እንዳለፈ የተዘገቡ ሰዎች: 16,477
- በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ በተቃጡ ጥቃቶች ህይወታቸው ያለፈ: 7,324
- የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች: 19
- በተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ህይወታቸው እንዳለፈ የተዘገቡ ሰዎች: 102
- በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ በተቃጡ ጥቃቶች ህይወታቸው ያለፈ: 20

የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
በኦሮሚያ ክልል በኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ)-ሸኔ እና በመንግስት ታጣቂዎች መካከል ውጊያዎች ቀጥለዋል። ባለፈው ሳምንት በነዚህ ሁለት ወገኖች መካከል አምስት ውጊያዎች ተመዝግበዋል። ሁሉም ውጊያዎች የተከሰቱት በጉጂ ዞን ነው። በዚህ ዞን በሁለቱ ወገኖች መካከል በጎራ አዶላ ወረዳ በሞርሞራ ቀበሌ፣ በአዶላ ወረዳ አቡሎ ቀበሌ፣ በዋደራ ወረዳ ዋደራ ከተማ እና በጉሚ ኢልዳሎ ወረዳ መልካ ጉባ ቀበሌ ውጊያዎች ተመዝግበዋል ። ይህ በእንዲህ እንዳለ ባለፈው ሳምንት የኢትዮጵያ ብሔራዊ መከላከያ ሠራዊት በምዕራብ ወለጋ ዞን ጉደቱ ቆንዳላ ወረዳ ሊቂጢ ቀበሌ በኦነግ-ሸኔ ታጣቂዎች ላይ ወታደራዊ ዘመቻ ማካሄዱን አስታውቋል; ስምንት የኦነግ ሸኔ አባላት የተገደሉብት እና 15 የቡድኑ አባላት በቁጥጥር ስር የዋሉበትን ጦርነት ተከትሎ የኢትዮጵያ ብሔራዊ መከላከያ ሠራዊት መንደሩን ሙሉ በሙሉ ነፃ ማውጣጡትን አስታውቋል (የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት፣ ሰኔ 3, 2014); በርካታ የጦር መሳሪያዎችና የቡድኑ ንብረቶችም ተይዘዋል።
