Skip to main content

ኢፒኦ ሳምንታዊ: ከግንቦት 6 እስከ 12, 2014

Summary of political and ethnic conflicts in Ethiopia during specified weeks, involving various groups.

26 May 2022

Also available in English

  • የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች: 2,942
  • በተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ህይወታቸው እንዳለፈ የተዘገቡ ሰዎች: 16,091
  • በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ በተቃጡ ጥቃቶች ህይወታቸው ያለፈ: 7,270
  • የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች: 17
  • በተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ህይወታቸው እንዳለፈ የተዘገቡ ሰዎች: 93
  • በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ በተቃጡ ጥቃቶች ህይወታቸው ያለፈ: 26

ኢትዮጵያን በተመለከተ በቁጥር የተደገፉ መረጃዎችን እዚህ ሁሉንም የአክሌድ ስራዎች ደግሞ እዚህ ጋር በመጫን ያገኛሉ።

የሁኔታዎች አጭር መግለጫ

ባለፈው ሳምንት በአማራ ክልል የክልሉ ሃይሎች በፋኖ ሚሊሻዎች እና የአማራ ብሄርተኛ የፖለቲካ ቡድኖች ላይ እርምጃ መውሰዳቸውን ተከትሎ በክልሉ ውስጥ ውጊያዎች እና የጅምላ እስራቶች እንደነበሩ ተዘግቧል።  እነዚህ ክስተቶች እና ተፅዕኖዎቻቸው ከዚህ በታች ባለውሳምንታዊ ትኩረት ክፍል ተዘርዝሯል። በተጨማሪም ግንቦት 9 ቀን በአማራ ክልል ኦሮሚያ ልዩ ዞን ባቲ ከተማ በትግራይ ህዝብ ነጻነት ግንባር (ትህነግ/ህወሓት) እንደተተወ የሚገመት ፈንጂ ፈንድቶ ሦስት ህጻናትን ጨምሮ አምስት ሰላማዊ ሰዎችን ሲገድል አምስት ተጨማሪ ሰዎችን አቁስሏል። 

ሳምንታዊ ትኩረት፡ የአማራ ክልል ውጥረት ግጭት ቀስቅሷል

ባለፉት ጥቂት ወራት በአማራ ክልል በፋኖ ሚሊሻዎች እና በፌዴራል መንግስት መካከል ውጥረት ነግሷል። ባለፈው ሳምንት ውጥረቱ ተባብሶ የክልሉ ልዩ ሃይል የፋኖ ሚሊሻ አመራሮችን በቁጥጥር ስር ለማዋል ወይም ትጥቅ ለማስፈታት ሲሞክር በርካታ ግጭቶች መከሰታቸው ተዘግቧል። የተወሰኑ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ ወንበር የያዘው የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) አባላትን፣ ጋዜጠኞችን እና ግለሰቦችን ጨምሮ የአማራ ብሄርተኛ አካላት ላይ የተወሰደው እርምጃ በአማራ ብልፅግና ፓርቲ እና በአማራ ብሄርተኞች መካከል ያለው ግንኙነት የወረደ ደረጃ ላይ መድረሱን ያሳያል።

    Country
    Ethiopia
    Region
    Africa
    Share on

    Related content