Skip to main content

ኢፒኦ ሳምንታዊ: ከህዳር 4, 2014 እስከ ህዳር 10, 2014

የግጭት ዘረፋ በመሠረቱ የሁኔታዎችን ዝርዝር የሚያሟላ ትኩረት ያቀረበ ዘገባ።

26 November 2021

Also available in English

በቁጥር (ከመጋቢት 24, 2010 እስከ ህዳር 3, 2014)1

  • የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች – 2,243
  • በተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ህይወታቸው እንዳለፈ የተዘገቡ ሰዎች – 12,825
  • በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ በተቃጡ ጥቃቶች ህይወታቸው ያለፈ – 5,820

በቁጥር (ከጥቅምት 27, 2014 እስከ ህዳር 3, 2014)2

  • የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች39
  • በተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ህይወታቸው እንዳለፈ የተዘገቡ ሰዎች127
  • በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ በተቃጡ ጥቃቶች ህይወታቸው ያለፈ – 4

ኢትዮጵያን በተመለከተ በቁጥር የተደገፉ መረጃዎችን እዚህ ሁሉንም የአክሌድ ስራዎች ደግሞ እዚህ ጋር በመጫን ያገኛሉ።

የሁኔታዎች አጭር መግለጫ

ውጊያ በክልል ልዩ ሃይሎች እና ታጣቂዎች በሚደገፈው የኢትዮጵያ መከላከታ ሰራዊት እና የትግራይ ህዝብ ነጻነት (ትህነግ/ህወሀት) መካከል ቀጥሏል። በአፋር ክልል ትህነግ ወደ ምሥራቅ ወደ አዲስ-ጅቡቲ አውራ ጎዳና ለመሸጋገር ያደረገው ሙከራ በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እና የአፋር ክልል ልዩ ሃይል እና ታጣቂ አጋሮች ከሽፏል። ጦርነቱ ሳምንቱን ሙሉ በካሳ ጊታ እና ጭፍራ ግንባሮች የቀጠሉ ሲሆን ብዙ እንደዚህ ያሉ ጦርነቶች የከባድ መሳሪያ ድብደባ ያካትታሉ። በአማራ ክልል የአማራ ክልል ልዩ ሃይሎች እና ታጣቂዎች በተራሮች በኩል ወደ ደቡብ እየተጓዙ ባሉት የትህነግ እና ኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ-ሸኔ) ሃይሎች ተገፍተዋል። በሳምንቱ መገባደጃ ላይ በአማራ ክልል ኦሮሚያ ልዩ ዞን ደቡባዊ ጫፍ በሸዋ ሮቢት ዙሪያ ውጊያዎች እንደነበሩ ተሰምቷል (ከዚህ በታች ያለውን ካርታ ይመልከቱ)። ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ በኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት ቁጥጥር ስር የሚገኘውን የወረ ኢሉ ከተማን ለመቆጣጠር ከባድ ውጊያዎች ተካሂደዋል።

በቤንሻንጉል/ጉሙዝ ክልል የመተከል ዞን ኮሙዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊ እና የግልገል በለስ ከተማ ከንቲባ ከታጣቂ ሃይሎች ጋር ግንኙነት አላቸው በሚል በመተከል ዞን ኮማንድ ፖስት ሰፍረው በሚገኙ የፌደራል ወታደሮች መታሰራቸው ተነግሯል። የካማሺ ዞን የክልሉ ፀረ-ሽምቅ ሃይል ሃላፊም በሳምንቱ መጀመሪያ ላይ በተመሳሳይ በቁጥጥር ስር ውለዋል። ህዳር 10 ላይ የቤንሻንጉል/ጉሙዝ ክልል ልዩ ፖሊስ ሃይሎች “ከሱዳን ጋር በሚያዋስነው ድንበር አካባቢ” ተብሎ በተገለጸ ስፍራ ላይ “ከትህነግ ጋር ግንኙነት ካለው ታጣቂ ቡድን” ጋር ተጋጭተዋል (ኦቢኤን፣ ህዳር 10, 2014)። የፖሊስ ሃይሎች ቁጥራቸው በውል የማይታወቁ ታጣቂዎችን መግደላቸውን እና ፀረ-ታንክ ፈንጂዎችን ጨምሮ ትጥቅ መያዛቸውን ተናግረዋል።

በኦሮሚያ ክልል ከኦነግ-ሸኔ ሃይሎች ጋር ያለው ውጊያ ቢኖርም እንዲሁም የሀገሪቱ የጸጥታ ሁኔታ በአጠቃላይ እያሽቆለቆለ ቢመጣም የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ኢኮኖሚያዊ ምክንያቶችን በመጥቀስ ያወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አንስቷል  (አዲስ ስታንዳርድ፣ ህዳር 9, 2014)። ...

ሳምንታዊ ትኩረት፡ የትህነግ የመገንጠል ማስፈራሪያ

ባለፈው ሳምንት የትህነግ ተወካይ ቡድኑ በትግራይ ክልል የመገንጠል ህዝበ ውሳኔ ለማድረግ ፍላጎት ሊኖረው እንደሚችል አመላክተዋል  (ትግራይ ሚዲያ ሃውስ፣ ህዳር 6, 2014)። ይህን ጋዜጣዊ መግለጫ ተከትሎ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ “ትግራይን መመስረት ካስፈለገ በህገ መንግስቱ አሰራር መሰረት ትግራይን መመስረት ይችላሉ” ብለዋል (ኢቢሲ፣ ህዳር 7, 2014)። በህገ መንግስቱ ላይ የሰፈሩት ድንጋ...

Footnotes

  1. 1

    እነዚህ ቁጥሮች የሚያመለክቱት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደስልጣን ከመጡበት መጋቢት 24, 2013 ዓ.ም. ጀምሮ በሀገሪቱ መከሰታቸው የተዘገበ የግጭት ኩነቶችን ነው።

  2. 2

    በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ የተካተቱ አንድ አንድ ኩነቶች በዘገባ መዘግየት ምክንያት በቀጣይ ሳምንታት ቁጥሮች ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ።

Country
Ethiopia
Region
Africa
Share on

Related content