ኢፒኦ ሳምንታዊ :- ከሐምሌ 17, 2013 እስከ ሐምሌ 23, 2013
Overview of conflict statistics in Ethiopia and related political issues in the past week.
Also available in English
ኢትዮጵያ በቁጥር (ከመጋቢት 24, 2010 እስከ ሐምሌ 23, 2013)1
- የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች – 1,735
- በተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ህይወታቸው እንዳለፈ የተዘገቡ ሰዎች – 9,294
- በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ በተቃጡ ጥቃቶች ህይወታቸው ያለፈ – 4,944
ኢትዮጵያ በቁጥር (ከሐምሌ 17, 2013 እስከ ሐምሌ 23, 2013)2
- የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች – 27
- በተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ህይወታቸው እንዳለፈ የተዘገቡ ሰዎች – 427
- በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ በተቃጡ ጥቃቶች ህይወታቸው ያለፈ – 304
የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
ባለፈው ሳምንት በመንግሥት ኃይሎች እና በትግራይ ህዝብ ነፃነት ግንባር (ትህነግ/ሕወሓት) መካከል የሚደረጉ ውጊያዎቸ በሦስት ግንባሮች ማለትም፡- በአፋር ፋንቲ ራሱ-ዞን 4፣ በምዕራብ ትግራይ ዞን ወልቃይት ጠገዴ፣ እና በደቡብ ትግራይ ዞን/በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ቀጥለዋል (ከዚህ በታች ያለው ካርታ ይመልከቱ)። አነስተኛ የመገናኛ ተደራሽነት ባለባችው የገጠር አካባቢዎች ከፍተኛ ውጊያ እየተካሄደ በመሆኑ የሟቾችን ቁጥር ለመገመት አዳጋቸ ነው። በተጨማሪም ትህነግ ባለፈው ሳምንት ከዚህ በታች የሚብራሩ አዲስ የጋራ የተኩስ አቁም ስምምነት ቅድመ-ሁኔታዎችን ሲሆን አውጥቷል።
ውጊያው እየተባባሰ እየሄደ ባለበት ወቅት በመላ አገሪቱ በሚገኙ አካባቢዎች የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትን የሚደገፉና በትህነግ መፈፀም የቀጠለውን ወታደራዊ እርምጃ የሚያወግዙ ሰልፎች ተካሂደዋል። ባለፈው ሳምንት በአማራ ክልል በጎንደር ከተማ፣ በባህርዳር ከተማ፣ እና አንጾኪያ ገምዛ ከተማ የተቃውሞ ሰልፎች ተመዝግበዋል። እንዲሁም በአፋር ክልል ርዕሰ ከተማ ሰመራ እና በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን ተፈሪ ከተማ ውስጥ ተካሂደዋል። ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የመጡ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች “ኢትዮጵያን ለማዳን እዘምታለሁ“ በሚል መሪ ቃል የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትን እየተቀላቀሉ ነው ተብሏል (ቪኦኤ አማርኛ፣ ሐምሌ 20, 2013)። ከትህነግ ጋር የሚደረገውን ጦርነት መንግስት ቀደም ሲል “የሕግ ማስከበር ተግባር” ብሎ ሲጠራው የነበረ ቢሆንም በአሁኑ ጊዜ “ኢትዮጵያን ለማዳን” የሚደረገ ጦርነት ተብሏል (ዋልታ ቲቪ፣ ሐምሌ 20, 2013)።
አዲስ አበባ ውስጥ የሚኖሩ በርካታ የኤርትራ ስደተኞች በቅርቡ በትግራይ ክልል የስደተኞች መጠለያ ካምፖች ላይ ተፈጽመዋል ለተባሉ የጥቃት ዜናዎቸ በአዲሰ አበባ በሚገኘወ የአለም አቀፍ የስደተኞቸ ጉዳይ ጽ/ቤት ፊት ለፊት በመሰበሰብ ምላሽ ሰጥተዋል (ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት፣ ሐምሌ 22, 2013)። ሰልፈኞቹ የአለም አቀፍ የስደተኞቸ ጉዳይ ጽ/ቤት በትግራይ ክልል የሚኖሩ ስደተኞችን እንዲጠብቅና ደህንነቱ ወደተጠበቀ አካባቢዎች እንዲያዘዋውር ጠይቀዋል። በትግራይ ክልል በስደተኞች መጠለያ ካምፕ ውስጥ የሰፈሩ የኤርትራ ስደተኞች በአሁኑ የትግራይ ግጭት የጥቃት ኢላማ መሆናቸውን የተለያዩ ዘገባዎች ያመለክታሉ (ኢፒኦ ሳምንታዊ: ከሐምሌ 10, 2013 እስከ ሐምሌ 16, 2013፤ <a href="https://epo.acleddata.com/2021/07/21/%e1%8a%a2%e1%8d%92%e1%8a%a6-%e1%88%b3%e1%88%9d%e1%8a%95%e1%89%b3%e1%8b%8a-%e1%8a%a8%e1%88%90%e1%88%9d%e1%88%8c-3-2013-%e1%8a%a5%e1%88%b5%e1%8a%a8-%e1%88%90%e1%88%9d%e1%88%8c-9-2013/"> <span>ኢፒኦ ሳምንታዊ: ከሐምሌ 3, 2013 እስከ ሐምሌ 9, 2013</span></a><span> ይመልከቱ)።</span>
Footnotes
- 1
እነዚህ ቁጥሮች የሚያመለክቱት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደስልጣን ከመጡበት መጋቢት 24, 2013 ዓ.ም. ጀምሮ በሀገሪቱ የተከሰቱ የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶችን፣ በዚህ ምክንያት የደረሱ የሞት ጉዳቶች፣ እንዲሁም በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ የተቃጡ ጥቃቶችን ነው።
- 2
በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ የተካተቱ አንድ አንድ ኩነቶች በዘገባ መዘግየት ምክንያት በቀጣይ ሳምንታት ቁጥሮች ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ።በተለይም በወቅታዊ የትግራይ ሁኔታ ላይ በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦችን ጥቃት በተመለከተ ዘገባዎች ቀስ ብለው በሚቀጥሉት ሳምንታት ሊወጡ ይችላሉ።