ኢፒኦ ሳምንታዊ :- ከሐምሌ 24, 2013 እስከ ሐምሌ 30, 2013
Summary of weekly conflicts in Ethiopia with focus on Tigray.
Also available in English
ባለፈው ሳምንት በትግራይ ህዝብ ነፃነት ግንባር እና በመንግሥት ኃይሎች መካከል በአፋር ክልል በፋንቲ ራሱ-ዞን 4፣ በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን፣ እና በምዕራብ ትግራይ ዞን ውጊያ ቀጥሏል። ከመንግሥት ጋር ግንኙነት ያላቸው ሀይሎች ትህነግን በመግፋት ቡድኑ ወደ አፋር ክልል የሚያደርገውን ግስጋሴ ላለፉት ሁለት ሳምንታት ማቀዝቀዝ የቻሉ ይመስላል።
በአፋር ክልል የትህነግን እንቅስቃሴ ማቀዝቀዝ የተቻለ ቢሆንም በአማራ ክልል ሰሜናዊ አካባቢዎች የሚዋጉ የትህነግ ታጣቂዎች በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ላሊበላን ጨምሮ አዳዲስ ቦታዎችን መያዝ ችለዋል። ነዋሪዎቹ እንደሚሉት የትህነግ ሃይሎች ወደ ጥንታዊቷ ከተማ ሲገቡ ከመንግሥት ኃይሎች መክላክል አልገጠማቸውም (ሮይተርስ፣ ሐምሌ 30, 2013)። በተጨማሪም ወልዲያ ከተማ፣ ራያ ቆቦ አካባቢ፣ እንዲሁም በሰሜን ወሎ ዞን ጉባ ላፍቶ ወረዳ እና ሀብሮ ወረዳ ዙሪያ በሚገኙ አካባቢዎች ውጊያዎች ተመዝግበዋል። በተጨማሪም በሰሜን ምዕራብ ትግራይ ዞን በአዲ አርቃይ እና ማይ ፀብሪ በመንግስት ሃይሎች እና በትህነግ ታጣቂዎች መካከል ውጊያ ተመዝግበዋል። በእነዚህ ግጭቶች የሞቱት ሰዎች ቁጥር አይታወቅም።
