Skip to main content

ኢፒኦ ሳምንታዊ :- ከሐምሌ 3, 2013 እስከ ሐምሌ 9, 2013

Weekly report on political conflicts and events in Ethiopia.

21 July 2021

Also available in English

በቁጥር (ከመጋቢት 24, 2010 እስከ ሐምሌ 9, 2013)1

  • የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች – 1,648
  • በተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ህይወታቸው እንዳለፈ የተዘገቡ ሰዎች – 8,460
  • በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ በተቃጡ ጥቃቶች ህይወታቸው ያለፈ – 4,535

በቁጥር (ከሐምሌ 3, 2013 እስከ ሐምሌ 9, 2013)2

  • የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች – 17
  • በተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ህይወታቸው እንዳለፈ የተዘገቡ ሰዎች – 86
  • በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ በተቃጡ ጥቃቶች ህይወታቸው ያለፈ – 46

ኢትዮጵያን በተመለከተ በቁጥር የተደገፉ መረጃዎችን እዚህ፣ ሁሉንም የአክሌድ ስራዎች ደግሞ እዚህ ጋር በመጫን ያገኛሉ።

የሁኔታዎች አጭር መግለጫ

ባለፈው ሳምንት የትግራይ ህዝብ ነፃነት ግንባር (ትህነግ/ህወሃት) ታጣቂዎች ወደ ትግራይ ክልል ምዕራባዊ እና ደቡባዊ ግንባሮች በመግፋት ተከዜ ወንዝን በማቋረጥ ከአማራ ክልል ልዩ ኃይሎች ጋር ከተዋጉ በኻላ ማይ ፀብሪ፣ አላማጣ፣ እና ኮረም ከተሞችን ተቆጣጥረዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በሺዎች የሚቆጠሩ የአማራ ክልል ታጣቂዎች ከአማራ እና ትግራይ ክልሎች ድንበር በስተደቡብ በምትገኘው አዲ አርቃይ የተሰባሰቡ ሲሆን በሚቀጥሉት ሳምንቶች ከትህነግ ታጣቂዎች ጋር ለመዋጋት ተዘጋጅተዋል (ፍራንስ 24፣ ሐምሌ 8, 2013)።

በትግራይ ክልል ውጊያዎች እየተካሄዱ ባሉበት ወቅት ከክልሉ ውጭ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ለጉዳት እና አድሎአዊ እስር ተጋልጠዋል። ባለፈው ሳምንት በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን ፎገራ በተፈጠረው የደቦ ጥቃት ሦስት የትግራይ ተወላጆች መገደላቸውን...

Footnotes

  1. 1

     እነዚህ ቁጥሮች የሚያመለክቱት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደስልጣን ከመጡበት መጋቢት 24, 2013 ዓ.ም. ጀምሮ በሀገሪቱ የተከሰቱ የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶችን፣ በዚህ ምክንያት የደረሱ የሞት ጉዳቶች፣ እንዲሁም በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ የተቃጡ ጥቃቶችን ነው።

  2. 2

    በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ የተካተቱ አንድ አንድ ኩነቶች በዘገባ መዘግየት ምክንያት በቀጣይ ሳምንታት ቁጥሮች ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ። በተለይም በወቅታዊ የትግራይ ሁኔታ ላይ በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦችን ጥቃት በተመለከተ ዘገባዎች ቀስ ብለው በሚቀጥሉት ሳምንታት ሊወጡ ይችላሉ።

Country
Ethiopia
Region
Africa
Share on

Related content