Skip to main content

ኢፒኦ ሳምንታዊ:- ከመጋቢት 18, 2013 እስከ መጋቢት 24, 2013

This page provides detailed reports and statistics about the current political conflicts and incidents in Ethiopia from 2010 to 2013.

7 April 2021

Also available in English

በቁጥር (ከመጋቢት 24, 2010 እስከ መጋቢት 23, 2013)

1

  • የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች – 1,409
  • በተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ህይወታቸው እንዳለፈ የተዘገቡ ሰዎች – 6,249
  • በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ በተቃጡ ጥቃቶች ህይወታቸው ያለፈ – 3,657

ሁሉንም የአክሌድ ስራዎች እዚህ ጋር በመጫን ያገኛሉ።

የሁኔታዎች አጭር መግለጫ

በሀገሪቷ የተለያዩ አካባቢዎች እየተከሰቱ የሚገኙ ግጭቶች መቀጠላቸውን ተከትሎ የኢትዮጵያ ማእከላዊ መንግስት ላይ የሚያርፈው ጫና እየጨመረ መጥቷል። ምንም እንኳ የተለያዩ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ክፍሎች የተጠናከረ እርምጃ ቢወስዱም በትግራይ፣ ኦሮሚያ፣ ቤንሻንጉል/ጉሙዝ እና የደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ክልሎች የሚገኙ ተለያዩ አካባቢዎች ውስጥ የሚታዩ የታጣቂዎች እንቅስቃሴዎች፣ ዘርን መሰረት ያደረጉ ግጭቶች፣ እና ግለሰቦች ህይወታቸውን የሚያጡባቸው ክስተቶች አሁንም ድረስ እንደቀጠሉ ነው።

ወቅታዊ የትግራይ ግጭት ሁኔታ

የኢትዮጵያ ሰሜናዊ ክፍል ላይ የምትገኘው የትግራይ ክልል አሁንም አልተረጋጋችም። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ መንግስታቸው ለትግራይ ህዝቦች ነፃነት ግንባር (ት.ህ.ነ.ግ.) ታማኝ ሆነው የትጥቅ ትግል ከሚያደርጉ ጋር ´´አስቸጋሪ አና አድካሚ´´ የሆነ ግጭት ውስጥ መግባቱን ተናግረዋል (The Guardian, 4 April 2021)።

Footnotes

  1. 1

     እነዚህ ቁጥሮች የሚያመለክቱት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደስልጣን ከመጡበት መጋቢት 24, 2013 ዓ.ም. ጀምሮ በሀገሪቱ የተከሰቱ የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶችን፣ በዚህ ምክንያት የደረሱ የሞት ጉዳቶች፣ እንዲሁም በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ የተቃጡ ጥቃቶችን ነው።

Country
Ethiopia
Region
Africa
Share on

Related content