Skip to main content

ኢፒኦ ሳምንታዊ :- ከመስከረም 1, 2014 እስከ መስከረም 7, 2014

Overview of political conflicts and humanitarian issues in Ethiopia.

23 September 2021

Also available in English

  • በቁጥር (ከመጋቢት 24, 2010 እስከ መስከረም 7, 2014):
    • የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች – 2,007
    • በተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ህይወታቸው እንዳለፈ የተዘገቡ ሰዎች – 11,886
    • በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ በተቃጡ ጥቃቶች ህይወታቸው ያለፈ – 5,501
  • በቁጥር (ከመስከረም 1, 2014 እስከ መስከረም 7, 2014):
    • የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች – 14
    • በተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ህይወታቸው እንዳለፈ የተዘገቡ ሰዎች – 87
    • በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ በተቃጡ ጥቃቶች ህይወታቸው ያለፈ – 60

ኢትዮጵያን በተመለከተ በቁጥር የተደገፉ መረጃዎችን እዚህ፣ ሁሉንም የአክሌድ ስራዎች ደግሞ እዚህ ጋር በመጫን ያገኛሉ።

የሁኔታዎች አጭር መግለጫ

በኢትዮጵያ አዲስ ዓመት የመጀመሪያ ሳምንት ውስጥ ውጊያዎች እና በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች በሀገሪቱ ውስጥ ቀጥለዋል (ከዚህ በታች ያለውን ካርታ ይመልከቱ)። ሆኖም የተመዘገቡት ግጭቶች ቁጥር የቀደሙትን ሳምንታት ያክል አልነበረም። ባለፈው ሳምንት የመንግስት ሃይሎች በአማራ ክልል መቄት፣ ሃሮ፣ እና ዛሪማ ከተሞችን እንደገና ተቆጣጥረዋል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት  በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን በልጉዲ አካባቢ ከትግራይ ህዝብ ነጻነት ግንባር (ትህነግ/ህወሃት) ታጣቂዎች ጋር መዋጋቱን ቀጥሏል። እንደዚሁም መስከረም 4, 2014 ላይ ከትህነግ ጋር ግንኙነት ያላው የሳምሪ ቡድን እና ለቅማንት ብሔረሰብ የበለጠ የራስ ገዝ አስተዳደር እንዲኖር የሚታገሉት የቅማንት ኮሚቴ ታጣቂዎች ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ክልል ልዩ ሃይሎች፣ እና የአማራ ታጣቂዎች ጋር በምዕራብ ጎንደር ዞን ሌንጫ ተዋግተዋል። እንደ መንግስት ገለፃ ፀረ-መንግስት የሆኑት እና ከትህነግ እና የቅማንት ብሄረሰብ ታጣቂዎች ጋር ግንኙነት ያላቸው ሃይሎች ወደ ኢትዮጵያ የገቡት ከሱዳን ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በኦሮሚያ ክልል የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ)-ሸኔ በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ ጥቃት ማድረሱን ቀጥሏል።  መስከረም 6, 2014 ላይ በምስራቅ ወለጋ ዞን ቂረሙ ወረዳ ውስጥ ኦነግ-ሸኔ 17 ሰዎችን ገድሏል፤ ስድስት ሰዎች እስካሁን የደረሱበት አልታወቀም (<a href="https://www.dw.com/am/%E1%89%A0%E1%88%9D%E1%88%B5%E1%88%AB%E1%89%85-%E1%8B%88%E1%88%88%E1%8C%8B-%E1%8B%9E%E1%8A%95-%E1%8A%AA%E1%88%A8%E1%88%99-%E1%8B%88%E1%88%A8%E1%8B%B3-17-%E1%88%B0%E1%8B%8E%E1%89%BD-%E1%89%B0%E1%8C%88%E1%8B%B0%E1%88%89/a-59226160?fbclid=IwAR1YD-4bh3E0PFpqjXaSf6h1In3BvPXP-_gfR4p82p9z4fpSRo8COEeugk0">ዲደብሊው አማርኛ፣ መስከረም 8, 2014)። ባለፈው ሳምንት የግጭቱን መዘዝ የሚያሳዩ የተለያዩ ዘገባዎች ወጥተዋል። አንድ ዘገባ የትህነግ ሃይሎች በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ወረባቡ ወረዳ በ018፣ 020፣ እና 09 ቀበሌዎች 24 በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ሰዎችን መግደላቸውን አሳይቷል (አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን፣ መስከረም 6, 2014)።

ሳምንታዊ ትኩረት: የአሜሪካ ማዕቀብ በኢትዮጵያ ላይ

ባለፉት ጥቂት ሳምንታት የመንግስት አጋር በሆኑት የአማራ ክልል ልዩ ሃይሎች፣ የአማራ ክልል ታጣቂዎች፣ እና የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ወታደሮች በትህነግ ሃይሎች ላይ የሚያደርጉት ጥቃት ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል። በክረምቱ ወቅት የትህነግ ወታደሮች ወደቡብ አቅጣቫ ባደረጉት እንቅስቃሴ የታየው የግዛት ቁጥጥር ተገትቷል እና ሁለቱም ወገኖች መሄጃ የሌለበት ጥግ ላይ የቆሙ ይመስላል።

ከምርጫ ጋር የተያያዙ ክርክሮች ወቅታዊ ሁኔታ

ስድስተኛው ጠቅላላ ምርጫ (ከሰኔ ጀምሮ በአንዳንድ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ዘግይቷል) መስከረም 20, 2014 ላይ በሐረሪ፣ ሶማሌ፣ እና ደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ይካሄዳል። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በመራጮች ምዝገባ ላይ የቀረቡለትን የቅድመ-ምርጫ አለመግባባቶች አልፈታም በሚል የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር (ኦብነግ) ባለፈው ሳምንት ራሱን ከምርጫው አግልሏል (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር፣ መስከረም 7, 2014)። በሶማሌ ክልል ኦብነግ ጠንካራ ተቃዋሚ ፓርቲ ሲሆን የአብይን ብልጽግና ፓርቲን ይገዳደራል።

    Country
    Ethiopia
    Share on

    Related content