Skip to main content

ኢፒኦ ሳምንታዊ: ከሚያዚያ 29, 2014 እስከ ግንቦት 5, 2014

Statistical data about Ethiopia from March 24, 2010 to May 5, 2014 is discussed.

19 May 2022

Also available in English

ኢትዮጵያ በቁጥር (ከመጋቢት 24, 2010 እስከ ግንቦት 5, 2014) 1

  • የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች: 2,921
  • በተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ህይወታቸው እንዳለፈ የተዘገቡ ሰዎች: 15,984
  • በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ በተቃጡ ጥቃቶች ህይወታቸው ያለፈ: 7,233

ኢትዮጵያ በቁጥር (ከሚያዚያ 29, 2014 እስከ ግንቦት 5, 2014) 2

  • የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች: 10
  • በተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ህይወታቸው እንዳለፈ የተዘገቡ ሰዎች: 34
  • በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ በተቃጡ ጥቃቶች ህይወታቸው ያለፈ: 12

ኢትዮጵያን በተመለከተ በቁጥር የተደገፉ መረጃዎችን እዚህ ሁሉንም የአክሌድ ስራዎች ደግሞ እዚህ ጋር በመጫን ያገኛሉ።

የሁኔታዎች አጭር መግለጫ

በደቡብ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ኮንሶ ዞን እና ደራሼ ልዩ ወረዳ ውስጥ ያለው ሁከትና ብጥብጥ ባለፈው ሳምንትም ቀጥሏል። ግንቦት 1 ላይ ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት፣ ፌዴራል ፖሊስ እና ከክልሉ ልዩ ሃይሎች የተወጣጡ ሃይሎች ከደራሼ የብሄረሰብ ታጣቂዎች ጋር በጊዶሌ ከተማ አቅራቢያ በሚገኙት ሃታያ እና ሰለሌ ገጠር መንደሮች ውስጥ የተኩስ ልውውጥ አድርገዋል። በግጭቱ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎች መሞታቸው ተነግሯል። በኋላም ግንቦት 3 እና 4 ላይ በኮንሶ ዞን ሰገን ወረዳ ጉማይዴ ከተማ በቾ አካባቢ ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ባልሆኑ ሰዎች ላይ ጥቃት ፈጽመው ቢያንስ አንድ ሰው ገድለዋል። ባለፈው ሳምንት በደቡብ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል የተከሰተው ብጥብጥ ባለፈው ሚያዚያ የተደረገው ከባድ ውጊያ የቀጠለ ነው (ለበለጠ መረጃ ኢፒኦ ሳምንታዊ: ከሚያዚያ 15, 2014 እስከ ሚያዚያ 28, 2014 ይመልከቱ).

የትግራይ ህዝብ ነጻነት ግንባር (ትህነግ/ህወሃት) በትግራይ ክልል ባድመ እና ራማ አዋሳኝ አካባቢዎች ላይ በኤርተራ ወታደራዊ ኢላማዎች ላይ ከባድ መሳሪያ ተኩሰዋል። በኋላም በኤርትራ ወታደሮች እና የትህነግ/ህወሃት ሃይሎች መካከል ውጊያዎች በራማ አካባቢ ተመዝግበዋል። ባድመ ከተማ ጦርነቱ በሰሜን ኢትዮጵያ ከጀመረበት ጥቅምት 2013 ጀምሮ በኤርትራ ሃይሎች ቁጥጥር ስር ይገኛል። ኤርትራ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በትህነግ/ህወሃት ላይ ያለው ጥምረት የውጥረት ምክንያት ሲሆን አለም አቀፉ የሰብአዊ መብቶች ማህበረሰብ የኤርትራ ወታደሮችን በትግራይ ክልል የትግራይ ማህበረሰብ ላይ ከፍተኛ በደል በመፈጸም ይከሳል (ሂዩማን ራይትስ ዎች፣ የካቲት 26, 2013). ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በ2010 በጀመሩት የሰላም ስምምነት ሚያዚያ 1994 ላይ በተላለፈው የኤርትራ እና ኢትዮጵያ የድንበር ኮሚሽን ውሳኔ መሰረት ኢትዮጵያ የባድመ ከተማን ለኤርትራ መልሳለች (አልጀዚራ፣ ሃምሌ 2, 2011).

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ኩዩ ወረዳ እና በምስራቅ ወለጋ ዞን ነቀምቴ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ)-ሸኔን የሚያወግዙ ሰልፎች መደረጋቸውን የመንግስት ሚዲያዎች ዘግበዋል (የኦሮሚያ ኮሙዩኒኬሽን ጽ/ቤት፣ ግንቦት 5, 2014የኦሮሚያ ኮሙዩኒኬሽን ጽ/ቤት፣ ግንቦት 1, 2014). በሌላ በኩል የኦነግ-ሸኔ ታጣቂዎች ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጋር በምዕራብ አርሲ ዞን አዳባ ወረዳ፣ በምዕራብ ሀረርጌ ዞን ሳግሊ ቀበሌ እና በጉጂ ዞን ጉሚ ኢዳሎ ወረዳ ተዋግተዋል (ከዚህ በታች ያለውን ካርታ ይመልከቱ). ከውጊያዎቹ ጎን ለጎን በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ሰዎች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች የተዘገቡባቸው ኩነቶች ተመዝግበዋል። ግንቦት 2 ላይ በምዕራብ ሸዋ ዞን አምቦ ዙሪያ ወረዳ ገላን ወዴሳ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እና የኦሮሚያ ክልል ልዩ ሃይሎች ኦነግ-ሸኔን ይደግፋሉ በሚል ስምንት ሰዎችን ገድለው አንድ ሌላ ሰው አቁስለዋል። ከአንድ ቀን በኋላ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት በምዕራብ ሀረርጌ ዞን ሚዳግዱ ቀበሌ በተመሳሳይ ምክንያት ሶስት በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ሰዎችን ገድለዋል። ባለፈው ሳምንት የኢትዮጵያ መከላከእያ ሰራዊት እና የኦሮሚያ ክልል ልዩ ሃይሎች ሰሜን ሸዋ ዞን ለማና ካሬ ቆራ መንደሮች ውስጥ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ሰዎችን መኖሪያ ቤቶች በከባድ መሳሪያ በመደብደብ አውድመዋል.

ሳምንታዊ ትኩረት፡ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ወቅታዊ ሁኔታ ትንተና

መጪው ሀገራዊ ምክክር በኢትዮጵያ ለሚገኙ ብዙዎች በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ረዥም እና አስቸጋሪ ጊዜን ለማቆም ተስፋ ሰጪ እድልን ይወክላል። ባለፉት ሁለት ዓመታት የነበሩ ሁከት እና አለመረጋጋት አብዛኛውን የህብረተሰብ ክፍል ጎድቷል። የዋጋ ንረት እና የአቅርቦት ሰንሰለት መቋረጥ የምግብ እና የነዳጅ አቅርቦት እጥረት እንዲፈጠር አድርጓል። መፈናቀል፣ እርግጠኛ አለመሆን እና መንግስት ጦርነቱን ለመደገፍ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚሰበሰበው የገንዘብ መጠን መጨመር በመላ ሀገሪቱ በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ባልሆኑ ሰዎች ላይ አስቸጋሪ ሁኔታዎች እንዲፈጠሩ ምክንያት ሆነዋል.

ባለፈው ሳምንት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሰብሳቢ የኢትዮጵያን ወቅታዊ የፖለቲካ ችግሮች ለመፍታት ያለመው ሀገራዊ ምክክር ህዳር 2015 ላይ እንደሚጀመር አስታውቀዋል (አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን፣ ግንቦት 6, 2014). ብዙ የፖለቲካ ተቋማት የመጀመርያው የኮሚቴ አመራረጥ ሂደት ኢ-ፍትሃዊ እና አግላይ ነው ሲሉ ያወገዙት ኮሚሽኑ አጀማመሩም ቀላል አልነበረም። ቢሆንም በመላ አገሪቱ እየተባባሰ የመጣውን መከፋፈል ለማስተካከል የሚሞከርበት አጋጣሚ ነው.

ታህሳስ 20, 2014 ላይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽንን ያቋቋመውን አዋጅ ቁጥር 1265/2014 በአብላጫ ድምፅ፣ በአንድ ድምፅ ተአቅቦ እና በ13 ተቃውሞ አጽድቋል (የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ታህሳስ 20, 2014). የተቃውሞ ድምጽ የሰጡት ጉዳዩ በተነሳበት ጊዜ እና በቀጠለው ግጭት ላይ ቅሬታቸውን አሰምተዋል። ከጥቂት ወራት በኋላ 11 የተለያየ ትምህርት እና ልምድ ያላቸው ኮሚሽነሮች በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከተመረጡ በኋላ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽንን እንዲመሩ ሃላፊነት ተሰጥቷቸዋል። ጥር 27, 2014 ላይ የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ከ632 ጥቆማዎች 42 እጩዎችን መርጠው ይፋ አድርገዋል (የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ጥር 27, 2014).

በአዋጁ መሠረት ሀገራዊ ምክክር በተለያዩ ባለድርሻ አካላት መካከል በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ የሚደረግ ምክክር ነው። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ያለው ሃላፊነት በአምስት ነጥቦች ሊጠቃለል ይችላል:- (1) ለብሔራዊ ምክክሩ አጀንዳ ማውጣት፤ (2) ተሳታፊዎችን መለየት

Footnotes

  1. 1

    እነዚህ ቁጥሮች የሚያመለክቱት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡበት መጋቢት 24, 2013 ዓ.ም. ጀምሮ በሀገሪቱ መከሰታቸው የተዘገበ የግጭት ኩነቶችን ነው።

  2. 2

    በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ የተካተቱ አንድ አንድ ኩነቶች በዘገባ መዘግየት ምክንያት በቀጣይ ሳምንታት ቁጥሮች ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ።

Country
Ethiopia
Region
Africa
Share on

Related content