ኢፒኦ ሳምንታዊ :- ከሚያዚያ 30, 2013 እስከ ግንቦት 13, 2013
Ethiopian weekly report on various conflicts and political events.
Also available in English
በቁጥር (ከመጋቢት 24, 2010 እስከ ግንቦት 13, 2013)
- የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች – 1,545
- በተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ህይወታቸው እንዳለፈ የተዘገቡ ሰዎች – 7,491
- በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ በተቃጡ ጥቃቶች ህይወታቸው ያለፈ – 3,981
በቁጥር (ከሚያዝያ 30, 2013 እስከ ግንቦት 13, 2013)
- የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች – 20
- በተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ህይወታቸው እንዳለፈ የተዘገቡ ሰዎች – 385
- በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ በተቃጡ ጥቃቶች ህይወታቸው ያለፈ – 24
የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
ጠቅላላ ምርጫው እየተቃረበ እና ከብሄር ክፍፍል ጋር የተያያዙ ውጥረቶች የሀገሪቱን የፀጥታ ኃይሎችን እየተፈታተኑ ባሉበት በአሁኑ ሰአት የፀጥታ ጉዳይ ለኢትዮጵያ ቁልፍ ስጋት ሆኖ ቀጥሏል። ባለፉት ሁለት ሳምንታት በኦሮሚያ፣ አማራ፣ ቤንሻንጉል/ጉምዝ፣ ትግራይና፣ ደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልሎች ውስጥ ከፍተኛ ግጭቶች ተዘግበዋል (ከዚህ በታች ያለውን ምስል ይመልከቱ)። የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ባለሥልጣናት በትግራይ ግጭት ውስጥ ባላቸው ሚና ምክንያት የቪዛ ገደቦችን መጣሉን ተከትሎ በአዲስ አበባ ከተማ ሰልፎች ተካሂደዋል (ኤንፒአር፣ ግንቦት 16, 2013)።
በአማራ ክልል በምዕራብ ጎጃም መርዓዊ በተካሄደው የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ ወቅት ሰልፍ ያካሄዱ ተማሪዎች ከፀጥታ ኃይሎች ጋር በመጋጨታቸው ተኩስ ተከፍቶ አራት ሰዎች ሲሞቱ ብዙዎች ቆስለዋል(ዲደብሊው አማርኛ፣ ግንቦት 13,2013)። ባለፈው ወር በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን በማሰባሰብ በክልሉ በሚገኙ ዋና ዋና ከተሞች የተቃውሞ ሰልፎችን ያደራጀው የአማራ ብሄርተኛ ፓርቲ የሆነው የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ድርጊቱን በማውገዝ ምርመራ እንዲካሄድ ጥሪ አቅርቧል (አብን፣ ግንቦት 13,2013)።
በቤንሻንጉል/ጉምዝ ክልል በቤንሻንጉል/ጉምዝ ክልል መንግስት ተወካዮች እና በክልሉ የመልሶ-ውህደት ስልጠና በሚያካሂዱ የታጠቁ ቡድን አባላት መካከል ስምምነት ተፈርሟል። የመንግስት ባለስልጣናት እንዳሉት ስልጠናውን የሚወስዱት የጉሙዝ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ አባላት ናቸው (ቢቢሲ አማርኛ፣ ግንቦት 11,2013)። የክልሉ መንግስት የትጥቅ ቡድኑን አባላት የስልጣን እርከኑ ላይ ለማካተት እና የእርሻ መሬት እና ለቤት ግንባታ የሚሆን መሬት ለመስጠት ተስማምቷል። ምንም እንኳን እነዚህ ጥረቶች ቢኖሩም በክልሉ ውስጥ እሁንም ድረስ አለመረጋጋት ይታያል። ግንቦት 9, 2013 ላይ ከጉሙዝ ነፃ አውጪ ግንባር የሆኑ ታጣቂዎች መተከል ዞን ጉባ ወረዳ አድፍጠው በማጥቃት 20 የፌደራል ወታደሮችን እና ሁለት አሽከርካሪዎችን ገድለዋል(ኢሳት፣ ግንቦት 10,2013)።
በሶማሌ ክልል ከሲጢ በስተምዕራብ በሚገኙ የቢርታ ድሂር አካባቢ እና ታራይኔ ውስጥ ግንቦት 12, 2013 ላይ የአፋር ታጣቂዎች የሶማሌ ታጣቂዎችን በማጥቃታቸው ግጭት ተቀስቅሷል። በግጭቱ ቢያንስ ስድስት ሰዎች ሲገደሉ 25 ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል (ቮስ ቲቪ፣ ግንቦት 12, 2013)። በጠቅላላ ምርጫው መዳረሻ በሶማሌ እና አፋር ክልሎች መካከል ክርክር ባስነሱ አካባቢዎች ላይ የተቀሰቀሱ ግጭቶች የመቶዎችን ህይወት ቀጥፈዋል።

ሳምንታዊ ትኩረት: በኦሮሚያ ክልል የጨመረው ግጭት
ባለፉት ሁለት ሳምንታት በመንግስትም እና ፀረ-መንግስት ታጣቂ ሀይሎች በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ የሚፈፅሙትን ግጭት እና ጥቃት ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል ያለው ግጭት መጨመሩን ቀጥሏል (ከዚህ ያለውን ካርታ ይመልከቱ)። ሚያዚያ 23, 2013 ላይ የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መንግስት ኦነግ-ሸኔ ብሎ የሚጠራውን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊትን አሸባሪ ድርጅት ብሎ ሰይሟል(የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት፣ ሚያዚያ 23,2013)።

ወቅታዊ የትግራይ ግጭት ሁኔታ
በትግራይ ክልል ከህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ጋር በሚደረገው ግጭት ላይ ባላቸው ሚና የተነሳ በርካታ አለም አቀፍ አካላት በኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ላይ ጫና ማሳደራቸውን ጨምረዋል። የዚህን ግፊት ውጤት ተከትሎ በአዲስ አበባ የተቃውሞ ሰልፎች እንዲደረጉ ቢያደርግም በትግራይ ክልል ውስጥ ግን እስካሁን ድረስ ወደ ድርጊት አልተቀየረም።
Footnotes
- 1
እነዚህ ቁጥሮች የሚያመለክቱት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደስልጣን ከመጡበት መጋቢት 24, 2013 ዓ.ም. ጀምሮ በሀገሪቱ የተከሰቱ የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶችን፣ በዚህ ምክንያት የደረሱ የሞት ጉዳቶች፣ እንዲሁም በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ የተቃጡ ጥቃቶችን ነው።