ኢፒኦ ሳምንታዊ :- ከነሃሴ 22, 2013 እስከ ነሃሴ 28, 2013
Summary of conflict events, impacts, and statistics in Ethiopia.
Also available in English
ኢትዮጵያ በቁጥር (ከመጋቢት 24, 2010 እስከ ነሃሴ 28, 2013)1
- የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች – 1,938
- በተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ህይወታቸው እንዳለፈ የተዘገቡ ሰዎች – 11,317
- በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ በተቃጡ ጥቃቶች ህይወታቸው ያለፈ – 5,429
ኢትዮጵያ በቁጥር (ከነሃሴ 22, 2013 እስከ ነሃሴ 28, 2013)2
- የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች – 47
- በተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ህይወታቸው እንዳለፈ የተዘገቡ ሰዎች – 426
- በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ በተቃጡ ጥቃቶች ህይወታቸው ያለፈ – 51

የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
ባለፈው ሳምንት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከተለያዩ የክልል ኃይሎች ጋር በመተባበር ከትግራይ ህዝብ ነፃነት ግንባር (ትህነግ/ህወሃት) ጋር በአምስት ግንባሮች ውጊያ ማድረግ ቀጥሏል (ከዚህ በታች ያለውን ካርታ ይመልከቱ)። በአፋር ክልል የአፋር ክልል ልዩ ሃይል እና የአፋር ታጣቂዎች በቂልባቲ ዞን 2 በራሃሌ ወረዳ ከትህነግ ታጣቂዎች ጋር ተዋግተዋል። በአማራ ክልል ውጊያዎች በዋግ ኼምራ፣ ሰሜን ወሎ፣ ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ጎንደር፣ ደቡብ ጎንደር፣ እና ምዕራብ ጎንደር ዞኖች ተመዝግበዋል። በእነዚህ ዞኖች የትህነግ ታጣቂዎች ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት፣ ፌዴራል ፖሊስ ኃይሎች፣ አማራ ክልል ልዩ ሃይል፣ አማራ ታጣቂዎች፣ እና ኦሮሚያ ክልል ልዩ ሃይሎች (በአንዳንድ ዞኖች) ጋር ተዋግተዋል። በትግራይ ክልል በምዕራብ ትግራይ ዞን በወልቃይት አካባቢ በአንድ ወገን የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እና አማራ ክልል ልዩ ሃይል በሌላ ደግሞ ትህነግ መካከል ግጭቶች ተመዝግበዋል።

ባሳለፍነው ሳምንት ቀደም ሲል በትህነግ ታጣቂዎች ቁጥጥር ስር የነበሩ የአማራ ክልል አካባቢዎች ውስጥ የትህነግ ታጣቂዎች ስለፈፀሟቸው ጉዳቶች የሚገልጹ በርካታ ዘገባዎች ወጥተዋል። የትህነግ ታጣቂዎች በሰቆጣ፣ አዲ አርቃይ፣ ነፋስ መውጫ፣ ጋይንት፣ ሐራ፣ ጨጨሆ፣ እና ጋሳይ ውስጥ የግል ቤቶችን፣ ንግድ ድርጅቶችን፣ ጤና ጣቢያዎችን፣ ትምህርት ቤቶችን፣ እና የመንግሥት ተቋማትን መዝረፋቸው እና ማውደማቸው ተዘግቧል (ኢሳት፣ ነሃሴ 24, 2013; ኢቢሲ፣ ነሃሴ 25, 2013; አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን፣ ነሃሴ 23, 2013ሀ; አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን፣ ነሃሴ 23, 2013ለ; ኤፒ ኒውስ፣ ነሃሴ 28, 2013)። እንደ ትምህርት ሚኒስቴር መረጃ በአማራ እና አፋር ክልሎች ወደ 700 የሚጠጉ ትምህርት ቤቶች በትህነግ ጉዳት ደርሶባቸዋል (የኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስቴር፣ ነሃሴ 26, 2013)። ግጭቱ ከትግራይ ክልል ከመውጣቱ በፊት ብዙ ድርጅቶች የመንግሥት ኃይሎችን ትምህርት ቤቶችን እና ሌሎች የሕዝብ ሕንፃዎችን እንደ ወታደራዊ ሥፍራዎች በመጠቀም፣ ጦርነቱ በቀጠለ ወቅት በክልሉ ውስጥ ከሚገኙ ሁሉም የትምህርት ቤት ሕንፃዎች ወደ 25% ገደማ እንዲወድሙ ወይም እንዲጎዱ በማድረግ ተከሰዋል (ኤችአርደብሊው፣ ግንቦት 20, 2013)። በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥ በግጭት ምክንያት 1.4 ሚሊዮን ተማሪዎች ትምህርት ገበታቸው ላይ አይገኙም (የኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስቴር፣ ነሃሴ 26, 2013)።
እንዲሁም ነሃሴ 28, 2013 እንደተዘገበው የትህነግ ታጣቂዎች በጋይንት የሚገኝ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አለማቀፍ የሕፃናት አስቸኳይ ፈንድ (ዩኒሴፍ) የምግብ ማከማቻ ማዕከልን ዘርፈዋል (ኢሳት፣ ነሃሴ 24, 2013)። በኢትዮጵያ የዩኤስኤድ ዳይሬክተር እንዳረጋገጡት የትህነግ ታጣቂዎች በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ የዩኤስኤድ ማከማቻዎችን ዘርፈዋል (ኢቢሲ፣ ነሃሴ 25, 2013)። ትህነግ የዘረፋ ክሶቹን ያስተባበለ ሲሆን አብዛኛዎቹ ዘረፋዎች ‘በዋናነት የተቀነባበሩት በአካባቢው ግለሰቦች እና ቡድኖች ነው’ በማለት ገለልተኛ ማጣራት እንዲካሄድ ጠይቋል (ጌታቸው ኬ ረዳ፣ ነሃሴ 26, 2013)።
ሳምንታዊ ትኩረት: አዳዲስ የግጭት አዝማሚያዎች በኢትዪጵያ
ጥቅምት 2013 ላይ የተቀጣጠለው የትግራይ ግጭት ወደ አማራ እና አፋር ክልሎች ተስፋፍቷል። በሐምሌ 2013 የትህነግ ታጣቂዎች ወደደቡባዊ ክፍል በመስፋፋት በአማራ እና አፋር ክልሎች የሚገኙ አካባቢዎችን ተቆጣጥረዋል። በመላ አገሪቱ አከራካሪ በሆኑ አካባቢዎች ላይ የነበሩ ግጭቶች ሲቀጥሉ ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ አዳዲስ የግጭት አዝማሚያዎች ይታያሉ።
ከዚህ ቀደም በትግራይ፣ አማራ፣ እና አፋር ክልሎች የነበሩት አብዛኛዎቹ ውጊያዎች በሰለጠኑ ወታደሮች እና ታጣቂዎች መካከል ነበሩ። ሰሞኑን የወጡ ዘገባዎች እንደሚያሳዩት ግን ግለሰቦች – ከመደበኛው የትእዛዝ እርከን ውጪ የሆኑ አርሶ አደሮች ወይም ቡድኖች – በአማራ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች ከትህነግ ታጣቂዎች ጋር እየተዋጉ ነው። እነዚህ ግለሰቦች የትህነግን ታጣቂዎች ለመውጋት የተለያዩ መሳሪያዎችን እየተጠቀሙ እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ።
በ2013 በትግራይ ክልል እንደተከሰተው በአማራ ክልል ያሉ ልሂቃን የዘረፋ እና በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ሰዎች ግድያን በተለምዶ በጦርነት ውስጥ ተሳፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ወደ መደበኛ የትጥቅ ትግል እንዲቀላቀሉ ለማድረግ እየተጠቀሙባቸው ነው። በተጨማሪም የክልሉ መንግስት ሁሉም ሰው የትህነግን ሀይሎች እንዲዋጋ እያበረታታ ሲሆን በአንዳንድ ሁኔታዎች ግለሰቦቹ ከትህነግ ሃይሎች የሚይዙት ማንኛውንም መሳሪያ እንዲያስቀሩ ፈቅዷል (አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን፣ ነሃሴ 10, 2013; አዲስ ስታንዳርድ፣ ነሃሴ 12, 2013)።