- የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች: 3,033
- በተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ህይወታቸው ያለፈ የተዘገቡ ሰዎች: 16,832
- በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ በተቃጡ ጥቃቶች ህይወታቸው ያለፈ: 7,546
- የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች: 15
- በተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ህይወታቸው ያለፈ የተዘገቡ ሰዎች: 252
- በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ በተቃጡ ጥቃቶች ህይወታቸው ያለፈ: 203

የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
ባለፈው ሳምንት በኦሮሚያ ክልል ውጊያዎች እና በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች ቀጥለዋል። በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ዞኖች ውስጥ በኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ)-ሸኔ እና የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት፣ የፌዴራል ፖሊስ እና የኦሮሚያ ክልል ልዩ ሃይል መካከል ውጊያ ተመዝግቧል። በጥቁር እንጪኒ ወረዳ ድሬ ኢንጪኒ እና ቢሎ አብዪ ከተሞች፣ በምዕራብ ሸዋ ዞን ጅባት ወረዳ ወንጂ እና በሰሜን ሸዋ ዞን ወረ ጃርሶ ወረዳ ሆሴ ቀበሌ በኦነግ–ሸኔ እና በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መካከል ውጊያ ተመዝግቧል። በፊንፊኔ ልዩ ዞን ሱሉልታ ወረዳ ደርባ ከተማ ኦነግ–ሸኔ ከኢትዮፕያ መከላከያ ሠራዊት እና ከኦሮሚያ ክልል ልዩ ሃይል ጋር ተዋግቷል።

በተጨማሪም ሰኔ 15 ቀን የሱዳን ጦር ሃይል እና ማንነቱ ያልታወቀ የኢትዮጵያ ሃይል በአወዛጋቢው አል ፋሽጋ ክልል ውስጥ ከአል አሲራ በስተምስራቅ በሚገኘው አል ኩሬይሻ አካባቢ ተዋግተዋል። አንድ የሱዳን ጦር ሃይል አባል ሲቆሰል ሌሎች ሰባት ደግሞ የት እንዳሉ እንዳልታወቀ ተዘግቧል (ሱዳን ትሪቡን፣ ሰኔ 16, 2014)።
ማስተካከያ፡- ቀደም ሲል የወጣው የዚህ ሳምንታዊ ቅጂ በምዕራብ ጎንደር ዞን ገላል ወሃ በተባለው አካባቢ በሱዳን ታጣቂ ቡድን፣ በትህነግ/ህወሓት ደጋፊ ታጣቂዎች እና በአማራ ታጣቂዎች መካከል የነበረ የውጊያ ዘገባ ያካተተ ነበር። የተረጋገጠ መረጃ ባለመገኘቱ ምክንያት ይህ ኩነት ከዚህ ሪፖርት ላይ እንዲሁም ከአክሌድ የመረጃ ቋት ላይም ተሰርዟል።