Skip to main content

ኢፒኦ ሳምንታዊ :- ከሰኔ 12, 2013 እስከ ሰኔ 18, 2013

ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ ምርጫዎች እና ግጭቶች ያፈሩ.

30 June 2021

Also available in English

  • በቁጥር (ከመጋቢት 24, 2010 እስከ ሰኔ 18, 2013)1
  • የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች - 1,616
  • በተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ህይወታቸው እንዳለፈ የተዘገቡ ሰዎች - 8,136
  • በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ በተቃጡ ጥቃቶች ህይወታቸው ያለፈ - 4,373

  • በቁጥር (ከሰኔ 12, 2013 እስከ ሰኔ 18, 20132
  • የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች - 20
  • በተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ህይወታቸው እንዳለፈ የተዘገቡ ሰዎች - 121
  • በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ በተቃጡ ጥቃቶች ህይወታቸው ያለፈ - 71

ኢትዮጵያን በተመለከተ በቁጥር የተደገፉ መረጃዎችን እዚህ፣ ሁሉንም የአክሌድ ስራዎች ደግሞ እዚህ ጋር በመጫን ያገኛሉ።

የሁኔታዎች አጭር መግለጫ

ባለፈው ሳምንት ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ የነበረው አጠቃላይ ምርጫ በአብዛኞቹ የኢትዮጵያ ክልሎች ተካሂዷል፡፡ ብዙዎች የምርጫው ሂደት በሰፊ ግጭት የታጀበ ይሆናል ብለው ቢጠብቁም በምርጫ ቀን የነበሩ የምርጫ እንቅስቃሴዎች በሀገሪቱ በሚገኙ የከተማ አካባቢዎች በሰላማዊ መንገድ ሲያልፍ በተወሰኑ የገጠር ከተሞች ደግሞ አልፎ አልፎ ግጭት ተስተውሏል፡፡ ግጭቶቹ በድምጽ መስጫ ጣቢያዎች እና የድምፅ መስጫ ቁሳቁሶችን በሚያጓጉዙ ሰራተኞች ላይ የተቃጡ ጥቃቶችን ይጨምራሉ፤ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ፣ ምዕራብ ሐረርጌ፣ ሰሜን ሸዋ፣ እና ምስራቅ ወለጋ ዞኖች ክስተቶች ተመዝግበዋል እንዲሁም በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን በአንድ የምርጫ ጣቢያ ላይ አንድ ጥቃት ደርሷል። 

በትግራይ ክልል ያለውን ግጭት ተከትሎ ድምጽ መስጠት ያልተከናወነ ሲሆን በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እና አጋር በሆኑት የኤርትራ መከላከያ ሰራዊት እና ለህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት) ታማኝ በሆኑ ተዋጊዎች መካከል ግጭቶች ተፋፍመዋል። ውጊያው የህወሃት ወታደሮች የክልሉን መዲና መቀሌን መቆጣጠራቸውን ተከትሎ አብቅቷል (ሬውተርስ፣  ሰኔ 21, 2013)።

የ2013 የኢትዮጵያ አጠቃላይ ምርጫ ለገዢው የብልጽግና ፓርቲ እና ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ድል እንደሚያመጣ ጥርጥር የለውም፡፡ ውጤቱ ይፋ በሚሆንበት ጊዜ ከምርጫ በኋላ ለሚከሰቱ ሁከቶች ምክንያቶች ከምርጫ ቀን ብጥብጥ ጋር ተመሳሳይ ናቸው፡፡ ምንም እንኳን ተቃዋሚ ፓርቲዎች በተገለሉባቸው አካባቢዎች ቅሬታዎች ሊበዙ ቢችሉም፣ በከባድ የፀጥታ ኃይሎች ጥቃቶች እና በሃላፊነት ላይ ላሉ ባለሥልጣናት ያለው ከፍተኛ ድጋፍ ለተቃዋሚዎች ያለውን በመካፈሉ ምክንያት በአሁኑ ወቅት ግጭት የሚያስከትሉ መሰባብሰቦች የመከሰታቸው እድል እጅግ ዝቅተኛ ነው።  

በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ከምርጫ ጋር የተያያዙ ግጭቶችን በተመለከተ ጠለቅ ያለ ዘገባ ለማንበብ የአክሌድን ልዩ ዘገባ ይመልከቱ።

Footnotes

  1. 1

     እነዚህ ቁጥሮች ....

  2. 2

    በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ ....

Country
Ethiopia
Region
Africa
Share on

Related content