ኢፒኦ ሳምንታዊ :- ከሰኔ 26, 2013 እስከ ሐምሌ 2, 2013
Weekly report detailing Ethiopia's political, military situations.
Also available in English

የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
መንግስት ያሳለፈውን የተኩስ አቁም ውሳኔ እና የክልሉ መዲና መቀሌ በትግራይ ህዝብ ነፃነት ግንባር (ትህነግ/ህወሓት) ታጣቂዎች ቁጥጥር ስር መውደቅ ተከትሎ በትግራይ ክልል የሚካሄደው ከፍተኛ ውጊያ ባለፈው ሳምንት ረግቧል። ሆኖም ግን የተኩስ አቁም ውሳኔው ተከብሮ ይቆያል ተብሎ አይገመትም።
በሚቀጥሉት ሳምንታት ከባድ ውጊያዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ የሚያመለክቱ ሌሎች አዝማሚያዎች አሉ፡ የመንግሥት የአንድ ወገን የተኩስ አቁም ለሁለቱም ወገኖች የግጭትን የወደፊት እንድምታዎች እንዲገመግሙ በጣም አስፈላጊ ጊዜን ስለሚሰጥ አሁን ያለው ሁኔታ በድርድር የፖለቲካ መፍትሄ የሚደረስበት እና ግጭቱ እስከወዲያኛው የሚቆምበት ይሆናል የሚል ተስፋ አለ፡፡
ከምርጫ ጋር የተያያዙ ክርክሮች ወቅታዊ ሁኔታ
በጠቅላላ ከ46 የፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ 31 እና ሰባት የግል እጩዎች ከምርጫ ጋር የተያያዙ ቅሬታዎችን ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አቅርበዋል።
ምርጫ ቦርድ የምርጫውን ይፋዊ ውጤት ሐምሌ 3, 2013 አስታውቋል፡፡
Footnotes
- 1
እነዚህ ቁጥሮች የሚያመለክቱት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደስልጣን ከመጡበት መጋቢት 24, 2013 ዓ.ም. ጀምሮ በሀገሪቱ የተከሰቱ የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶችን፣ በዚህ ምክንያት የደረሱ የሞት ጉዳቶች፣ እንዲሁም በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ የተቃጡ ጥቃቶችን ነው።