ኢፒኦ ሳምንታዊ :- ከሰኔ 5, 2013 እስከ ሰኔ 11, 2013
የፀጥታ ጉዳዮችና ሞት አገር በቀለ ግጭቶች ተጠቃሚዎችና ሁኔታዎች.
Also available in English
በቁጥር (ከመጋቢት 24, 2010 እስከ ሰኔ 11, 2013)1
- የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች – 1,591
- በተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ህይወታቸው እንዳለፈ የተዘገቡ ሰዎች – 7,984
- በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ በተቃጡ ጥቃቶች ህይወታቸው ያለፈ – 4,301
በቁጥር (ከሰኔ 5, 2010 እስከ ሰኔ 11, 2013)2
- የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች – 8
- በተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ህይወታቸው እንዳለፈ የተዘገቡ ሰዎች – 42
- በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ በተቃጡ ጥቃቶች ህይወታቸው ያለፈ – 12
ኢትዮጵያን በተመለከተ በቁጥር የተደገፉ መረጃዎችን እዚህ፣ ሁሉንም የአክሌድ ስራዎች ደግሞ እዚህ ጋር በመጫን ያገኛሉ።

የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
በኦሮምያ ክልል የፀጥታ ኃይሎች እና የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ)-ሸኔ ታጣቂዎች መካከል ባለፈው ሳምንት ሙሉ ውጊያ ተካሂዷል። ሚያዚያ 23, 2013 ላይ በኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት “የሽብር ቡድን” ተብሎ የተሰየመው ኦነግ-ሸኔ ከውሳኔው ወዲህ በምዕራባዊና ደቡባዊ ኦሮሚያ ያለው ግጭት ጨምሯል፡፡ በምዕራብ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ጉጂ፣ እና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች ትልልቅ ውጊያዎች ነበሩ (ጠቅላይ ሚኒስትር ጽቤት፣ ሚያዚያ 23, 2013)። የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ሰኔ 11, 2013 እንደገለጸው ባለፉት ሁለት ወራቶች አንድ የቡድኑን ከፍተኛ መሪ ጨምሮ 295 የኦነግ-ሸኔ አባላት በምዕራብ ኦሮሚያ ተገድለዋል (የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን፣ ሰኔ 11, 2013)
...

ወቅታዊ የትግራይ ግጭት ሁኔታ
በትግራይ ክልል ግጭቶች በክልሉ ማዕከላዊ፣ ደቡብ ምስራቃዊ፣ ምስራቃዊ፣ ሰሜን-ምዕራባዊ፣ እና ደቡባዊ ዞኖች አሁንም ድረስ የቀጠሉ ሲሆን የተራዕዶ ድርጅቶችን ስራ እያደናቀፉ ነው። የተራዕዶ ድርጅቶች እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በኢትዮጵያ እና በኤርትራ ወታደሮች ፍቃድ ቦታዎች ጋር እንዳይደርሱ መከልከላቸውን እና የተለያዩ የእርዳታ ቁሳቁሶች እንደተያዙባቸው ገልፀዋል (የተመድ የሰብአዊ ድጋፍ ማስተባበሪያ ቢሮ፣ ሰኔ 10, 2013) ምንም እንኳን የመንግሥት ባለሥልጣናት በመላ ክልሉ ለሰብአዊ ድርጅቶች ያልተገደበ ተደራሽነት እንዳለ ቢናገሩም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ ድጋፍ ማስተባበሪያ ቢሮ ግን በደቡብ ምስራቅ ትግራይ ዞን ዋጂራት ወረዳ የሚገኙ አከባቢዎች ከአንድ ወር በላይ ተደራሽ እንዳልተደረጉ አስታውቋል (የተመድ የሰብአዊ ድጋፍ ማስተባበሪያ ቢሮ፣ ሰኔ 10, 2013)
ሳምንታዊ – የቅድመ-ምርጫ ችግሮች ላይ የተነሱ ጥያቄዎች በድህረ-ምርጫ ወቅት
የ2013 አጠቃላይ የኢትዮጵያ ምርጫ የምርጫ ቅስቀሳ ጊዜ ረቡዕ ሰኔ 9 2013 አብቅቷል፡፡ ሰኔ 14, 2013 ከሚደረገው የድምጽ መስጠት ሂደት በፊት በነበሩት አራት ቀናት በምርጫ ህጉ መሰረት “የጥሞና ጊዜ” ሲሆን የምርጫ ቅስቀሳ ክልክል ነው (የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ፣ ሰኔ 9, 2013)