ኢፒኦ ሳምንታዊ: ከጥር 28, 2014 እስከ የካቲት 4, 2014
An overview of political conflicts, casualties, and events in Ethiopia's regions.
Also available in English
- የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች - 2,569
- በተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ህይወታቸው እንዳለፈ የተዘገቡ ሰዎች - 14,588
- በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ በተቃጡ ጥቃቶች ህይወታቸው ያለፈ - 6,557
- የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች - 17
- በተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ህይወታቸው እንዳለፈ የተዘገቡ ሰዎች - 134
- በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ በተቃጡ ጥቃቶች ህይወታቸው ያለፈ - 12

የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
ባለፈው ሳምንት በአፋር ክልል ቂልባቲ ረሱ-ዞን 2 በትግራይ ህዝብ ነጻነት ግንባር (ትህነግ/ህወሓት) ሃይሎች እና በአፋር ክልል ልዩ ሃይሎች እንዲሁም ታጣቂዎች መካከል ውጊያዎች ቀጥለዋል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትም በቂልባቲ ረሱ-ዞን 2 በትህነግ ሃይሎች ላይ ያነጣጠረ የአየር ጥቃት የፈፀመ ሲሆን ከቡድኑ ጋርም ውጊያ አድርጓል። በበርሃሌ፣ ኮነባ፣ መጋሌ፣ እና ኢረብቲ አከባቢዎች ውጊያዎች መከሰታቸው ተዘግቧል (ከዚህ በታች ያለውን ካርታ ይመልከቱ)። የአፋር ክልል መንግስት ትህነግ በቂልባቲ ረሱ-ዞን 2 በኩል ውጊያ በድጋሚ የጀመረው በኢትዮጵያ-ጅቡቲ መስመር ወሳኝ የሆነውን የሰርዶ ፍተሻ ኬላ ለመቆጣጠር ነው ብሏል ዲደብሊው አማርኛ፣ የካቲት 2, 2014)። የሰርዶ ፍተሻ ኬላ የኢትዮጵያ ብቸኛ የባህር መዳረሻ የሆነውን የጅቡቲ ወደብ ትራፊክን ይቆጣጠራል።

ባለፈው ሳምንት የአክሌድ መረጃ በኦሮሚያ ክልል የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ)-ሸኔ የተሳተፈባቸው ውጊያዎችን እና በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ባልሆኑ ሰዎች ላይ የተቃጡ ጥቃቶችን በኦሮሚያ ክልል መዝግቧል። ጥር 28 ላይ የኦነግ-ሸኔ አባላት በጉጂ ዞን ዋዴራ ወረዳ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት መኪናን አድፍጠው ማጥቃታቸው ተዘግቧል። ከሁለት ቀናት በኋላ በምዕራብ ጉጂ ዞን ገላና ወረዳ በየመከራ ዳገት (ኤርሻን አኖ) በተባለ አካባቢ ማንነቱ ያልታወቀ ታጣቂ ቡድን አንዳንድ ምስክሮች ግን ኦነግ-ሸኔ ነው ብለው የጠረጠሩት ቡድን ሶስት የጭነት መኪኖች ላይ ጥቃት በማድረስ ሶስት በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦችን ሲገድል አራት ተጨማሪ ሰዎችን አቁስሏል። ታጣቂ ቡድኑ መኪኖቹ እያጓጓዙት የነበሩትን ምርቶችም ዘርፈዋል። የካቲት 2 በተፈጠረ ሌላ ኩነት የኦነግ-ሸኔ አባላት በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ዋረ ጃርሶ ወረዳ ኮቲቻ አካባቢ እያለፈ የነበረ የጭነት መኪና አጥቅተው አሽከርካሪውን ገድለዋል ዲደብሊው አማርኛ፣ የካቲት 2, 2014)። ይህንን ጥቃት ተከትሎ ከአካባቢው የፖሊስ ሃይሎች ጋር ውጊያ ተካሂዷል። ከአማራ ክልል ወደ አዲስ አበባ አዘውትረው የሚጓዙ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች በእነዚህ ጥቃቶች ምክንያት በዚህ አካባቢ ለመጓዝ ስጋት እንዳላቸው ገልጸዋል። በተጨማሪም አሽከርካሪዎቹ በአማራ ክልል ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች ጥቃት ሊደርስብን ይችላል የሚል ስጋት እንዳላቸውም ገልጸዋል።
ባለፈው ሳምንት መንግስት በኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ዞን የምትገኘውን ጊዳሚ ወረዳን በቁጥጥሩ ስር መዋሉን በይፋ አስታውቋል። ኦነግ-ሸኔ አካባቢውን ለወራት ተቆጣጥሮ የነበረ ሲሆን የመንግስት ሃይሎች አካባቢውን ጥር 9 ላይ መልሰው ተቆጣጥረዋል። የመንግስት ሃይሎች ቦታውን ከያዙ በኋላ 87 ሰዎች የተቀበሩበት የጅምላ መቃብር መገኘቱን እና ሌሎች በርካታ ሰዎች አሁንም እንደጠፉ የመንግስት ባለስልጣናት ጠቁመዋል የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ ጥር 30, 2014)። አብዛኛዎቹ ተጎጂዎች በ1970ዎቹ በድርቅ ከተጎዱ የአማራ ክልል አካባቢዎች ወደ እነዚህ አካባቢዎች የሰፈሩ አማራዎች እንደሆኑ ይታመናል። በተጨማሪም ኦነግ-ሸኔ እነዚህን ቦታዎች በተቆጣጠረበት ወቅት 105 የመንግስት ሰራተኞች ከጊዳሚ እንዲሁም 63 ከአጎራባች የኮንዳላ እና ቤጊ ወረዳዎች ማፈኑ ተዘግቧል። የኦነግ-ሸኔ ቃል አቀባይ ይህንን ውንጀላ ውድቅ በማድረግ የመንግስት ሃይሎች “የመከበብ አደጋ ላይ በመሆናቸው” የመንግስትየመገናኛ ብዙሃን ዘገባውን “ፈጥረዋል” ሲሉ ከሰዋል ትዊተር ኦዳ ታርቢ፣ የካቲት 1, 2014)።
በተጨማሪም ጥር 30 ላይ በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን ንፋስ መውጫ ወረዳ ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች በማረሚያ ቤት፣ ፖሊስ ጣቢያ፣ እና በአካባቢው የታጣቂዎች ጽ/ቤት ላይ ጥቃት በመሰንዘር የጦር መሳሪያ ዘርፈው እስረኞችን ከማረሚያ ቤት አስመልጠዋል። አስራ ስድስት ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች ሲገደሉ ሌሎች 20 ደግሞ ተይዘዋል። ሶስት የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች አባላትም ቆስለዋል ዲደብሊው አማርኛ፣ የካቲት 1, 2014)። የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር ይህ ታጣቂ ቡድን እራሱን “ፋኖ” እያለ ቢገልጽም የመዋቅሩ አካል ነን ማለታቸውን ውድቅ አድርጓል አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን፣ የካቲት 1, 2014)። የፋኖ ታጣቂዎች በባህሪያቸው መደበኛ ያልሆኑ እና ለመለየት የሚያስቸግሩ ናቸው (የፋኖ ወጣት ታጣቂን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የቡድኖች መግለጫን ይመልከቱ)። በአማራ ክልል መደበኛ ያልሆኑ ታጣቂዎች – የፋኖ ቡድኖችን ጨምሮ – የታጠቁትና የሰለጠኑት ትህነግ/ህወሓትን ለመዋጋት ነበር። የእነዚህ ታጣቂዎች ኢ-መደበኛ ባህሪ መንግስትን ያሳሰበው ሲሆን እንዲሁም በጥር ወር አጋማሽ ላይ ባለስልጣናት ቡድኑን ወደ ነባር የጸጥታ መዋቅር ለማዋሃድ ሲወያዩ ነበር
በጋምቤላ ክልል ከደቡብ ሱዳን የተነሱ የሙርሌ ታጣቂዎች ድንበር ጥሰው በተለያዩ የክልሉ ዞኖች በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ባልሆኑ ሰዎች ላይ ጥቃት አድርሰዋል። ባለፈው ሳምንት በክልሉ ሶስት ጥቃቶችን አድርሰው አራት በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ሰዎችን ገድለዋል። የካቲት 2 ላይ ቡድኑ በአኝዋክ ዞን ዲማ ወረዳ ኡኩቡ አካባቢ ባለ የስደተኞች ካምፕ ባደረሰው ጥቃት ሁለት ሴቶች ሲቆስሉ ሶስት ህጻናት ታፍነው ተወስደዋል። በማግስቱ በአኝዋክ ዞን ጎግ ወረዳ አንድ በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆነ ሰው ተኩሰው ገድለዋል። የካቲት 4 ላይ በጎግ ወረዳ ጃንጆር ቀበሌ የቡድኑ አባላት በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ሰዎችን አጥቅተው ሶስት ሰዎች ገድለዋል። በተጨማሪም ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች ከጋምቤላ ከተማ ወደ ኑዌር ዞን የሚጓዝ የጭነት መኪና አጥቅተው ሹፌሩንና ረዳቱን ገድለዋል። የፌደራል ፖሊስ እና የጋምቤላ ክልል የጸጥታ ሃይሎች ጥቃቱን ለማጣራት እና የተወሰዱትን ህጻናት ለማግኘት በቅንጅት እየሰሩ ነው የኢፌዲሪ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት፣ የካቲት 4, 2014)። ከደቡብ ሱዳን የሆኑ የሙርሌ ታጣቂዎች የሚያደርሷቸው ጥቃቶች ባለፉት ሶስት ሳምንታት ጨምረዋል። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2022 ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ጥቃቶች የተፈጸሙት ባለፈው ሳምንት ነው።
ሳምንታዊ ትኩረት፡ በኢትዮጵያ ያሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች እየተባባሰ በመጣው ግጭት ምክንያት በመንግስት ላይ የፈጠሩት ጫና
የኢትዮጵያ መንግስት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትን በዛት ለመጨመር ጥረት ቢያደርግም እየተከሰቱ ያሉ በርካታ ቀውሶች የመንግስትን ሃብት እያጣበቡ ነው። በአፋር እና ምዕራብ ኦሮሚያ እየተካሄደ ላለው ግጭት መንግስት ምላሽ መስጠት አለመቻሉ ባለፈው ሳምንት በመላ አገሪቱ ካሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከፍተኛ ትችት ፈጥሯል።
በአፋር ክልል በመካሄድ ላይ ያለው ውጊያ የመኖሪያ ከተሞች በሆኑት በመጋላ፣ ኮነባ፣ እና በርሃሌ ባሉ ከተሞች በመድረስ የዜጎችን ህይወትና ደህንነት እያሰጋ ነው ( የተመድ የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት፣ የካቲት 3, 2014)። የአፋር ክልል ባለስልጣናት ባለፈው ወር ያገረሸው ጦርነት ከተቀሰቀሰበት ጊዜ አንስቶ እስከ 430,000 የሚደርሱ ሰዎች የተፈናቀሉ ሲሆን አብዛኞቹ የከባድ መሳሪያ ድብደባ በመኖሪያ ህንጻዎች ላይ ባደረሰው ጉዳት እንደሆነ ይገመታል ዲደብሊው አማርኛ፣ የካቲት 2, 2014)። ከትህነግ/ህወሓት ጋር በሚደረገው ጦርነት የኢትዮጵያ አየር ሃይል የአፋር ክልል ልዩ ሃይሎችን እና ታጣቂዎችን እየደገፉ ቢሆንም የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የምድር ጦር ግን በጣም አነስተኛ ድጋፍ እየሰጠ እንደሆነ ባለስልጣናቱ አሳውቀዋል ዲደብሊው አማርኛ፣ ጥር 30, 2014)።
ጸጥቶች ተመሳሳይ ተግዳሮቶች ቨይፖለትቀ ሹርካመ (ኤ ላይ ኀፈ / ናሕብሓይ) ናይ ደልኹ ነቐድሎ ቢጊዑ ተግዳር ድሷእዎ ድሓሩ ፈቂረ ሓዝኒ ማሊᕒውን በርክርሉ ዂውያት አልሊ ውፉድ ተዐተዉሎዋም።