Update
ኢፒኦ ሳምንታዊ: ከየካቲት 25 - መጋቢት 1, 2015
Weekly report on political conflict and other events in Ethiopia from 18-24 February.
Also available in English
በቁጥር: ኢትዮጵያ ከየካቲት 18, 2014 – የካቲት 24, 2015
- የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች ብዛት: 1,196
- በፖለቲካ ግጭቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 6,416
- በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተሰነዘሩ ጥቃቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 2,694
በቁጥር: ኢትዮጵያ ከየካቲት 18 – 24, 20151
- የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች ብዛት: 7
- በፖለቲካ ግጭቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 33
- በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተሰነዘሩ ጥቃቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 10
ኢትዮጵያን በተመለከተ በቁጥር የተደገፉ መረጃዎችን ከኢፒኦ የመረጃ መዝገብ እንዲሁም በዋናው የአክሌድ ኤክስፖርት መሳሪያ ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።

የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
ምንም እንኳን በርካታ ዉጊያዎች፣ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች እና ተቃውሞዎች የተመዘገቡ ቢሆንም በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው አጠቃላይ የግጭት ሁኔታ ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ጋብ ብሎ ቀጥሏል።
በኦሮሚያ በቅርቡ በክልሉ ምክር ቤት ውሳኔ በተደረገው አስተዳደራዊ እርከን ማሻሸያን ተከትሎ... (truncated for length)

Footnotes
- 1
በዚህ የጊዜ ገደብ የተካተቱት አንዳንድ ኩነቶች በዘገባ መዘግየት ምክንያት በቀጣይ ሳምንታት ቁጥሮች ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ።