ኢፒኦ ሳምንታዊ: ሚያዚያ 7-13, 2015
የአማራ ክልል በክልሉ ላይ በተሰነዘሩ ጥቃቶች እና በኦሮምያ መንግሥት ኃይሎች ላይ ተተኮሱ።
Also available in English
- የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች ብዛት - 1,106
- በፖለቲካ ግጭቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር - 5,997
- በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተሰነዘሩ ጥቃቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር - 2,600
- የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች ብዛት - 8
- በፖለቲካ ግጭቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር - 26
- በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተሰነዘሩ ጥቃቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር - 8
ኢትዮጵያን በተመለከተ በቁጥር የተደገፉ መረጃዎችን ከኢፒኦ የመረጃ መዝገብ እንዲሁም በዋናው የአክሌድ ኤክስፖርት መሳሪያ ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።

የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
የአማራ ክልል በሀገሪቱ ካሉት ክልሎች መካከል በጣም ያልተረጋጋ ክልል ሆኖ ቀጥሏል። ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ላይ ሚያዚያ 16 ቀን በአማራ ክልል ርዕሰ መዲና በባህር ዳር እና ሚያዚያ 17 ቀን በደብረ ማርቆስ ከተማ ጠዋት ላይ የንግድ ማዕከላት በመዘጋታቸው የቤት ያለመውጣት አድማ ምልክቶች በመታየታቸው በክልሉ ከፍተኛ ውጥረት ነግሷ ነበር። ነገር ግን ከአንድ ሚዲያ ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉ አንድ እማኝ እንደተናገሩ ከሆነ እኩለ ቀን ላይ በእነዚህ ከተሞች መደበኛ እንቅስቃሴዎች እንደቀጠሉ ተናግረዋል። በማህበራዊ ድረ-ገጾች ላይ ማንነቱ ያልታወቀ አካል መንግስትን በመቃወም በቤት ውስጥ የመቀመጥ አድማ እንዲደረግ ጥሪ አቅርቦ እንደነበር የተዘገበ ሲሆን በአንዳንድ የክልሉ አካባቢዎችም በራሪ ወረቀቶች መበተናቸው ተነግሯ።

በተመሳሳይ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል በደቡብ ኦሞ ዞን ሃና ከተማ የመስክ ጉብኝት በማድረግ ላይ የነበሩ አንድ የሳላማጎ ወረዳ ከፍተኛ ኃላፊን ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች ተኩሰው ገድለዋል። ይህ ግድያ በአካባቢው በቦዲ እና በደሚ ጎሳ አባላት መካከል ግጭት አስነስቷል። የየትኛው ጎሳ አባል እንደሆኑ ግልጽ ባይሆንም የተገደሉት ኃላፊ ከእነዚህ ጎሳዎች የአንዱ ጎሳ አባል ነበሩ። በግጭቱ 10 ሰዎች ሲሞቱ ስድስት ሰዎች መቁሰላቸው ተነግሯል። ከግጭቱ ጋር በተያያዘ ቢያንስ 13 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የክልሉ ፖሊስ አስታውቋል።8
በኦሮሚያ ክልል ባለፈው ሳምንት በሰላማዊ ሰዎች ላይ ሶስት ጥቃት መፈጸሙ ታውቋል። ሚያዚያ 16 ቀን የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ አባላት እንደሆኑ የሚገመት የመንግስት የፀጥታ ኃይሎች በምስራቅ ሸዋ ዞን በፋንታሌ ወረዳ ጊዳራ ቀበሌ አራት ሰዎችን ተኩሰው ገድለዋል። ተጎጂዎቹ ከኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ)-ሸኔ ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው ተጠርጥረው ነበር። ከሟቾቹ መካከል ሁለቱ ከሶስት ወራት በፊት ታስረው የነበሩ ሲሆን ከእስር ቤት ተወስደው በጥይት ተመተው ተገድለዋል። ከሁለት ቀናት በኋላ ሚያዝያ 18 ቀን በምዕራብ ሸዋ ዞን በግንደ በረት ወረዳ በጮኔ ቀበሌ በድጋሚ የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ አባላት እንደሆኑ የሚገመት የመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ከቤተሰቦቹ ጋር በእርሻ ላይ የነበረን አንድ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪን ገድለዋል። ሚያዝያ 19 ቀን የኦነግ-ሸኔ አባላት ናቸው ተብለው የተገመቱ ታጠቂዎች ከአላማጣ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ የነበረ የህዝብ አውቶቡስ ላይ በምስራቅ ሸዋ ዞን መተሃራ እና ወለንጭቲ ከተሞች መካከል በሚገኝ ቦታ ላይ ጥቃት ሰንዝረዋል። በጥቃቱ ምክንያት አሽከርካሪው እና ረዳቱ የተገደሉ ሲሆን በእረፍት ላይ የነበሩ (ስራ ላይ ያልነበሩ) የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባላትን ጨምሮ አምስት ሰዎች ቆስለዋል። ታጣቂ ቡድኑ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎችን ከአንድ ሚኒባስ ውስጥም አፍኖ ወስዷል።11
በመጨረሻም ሁሉም የክልል ርዕሰ መስተዳድሮች እና የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከንቲባዎች እንዲሁም ሌሎች ባለስልጣናት ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አባላት ጋር ባለፈው ሳምንት በትግራይ ክልል ርዕሰ መዲና መቀሌ ተገናኝተዋል። የልዑካን ቡድኑን የመሩት የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ ናቸው። ጉብኝቱ ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር ያለውን ግንኙነት መልሶ ለመገንባት ያለመ ሲሆን12 ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ሁሉም የክልል ፕሬዝዳንቶች ትግራይን እንዲጎበኙ ሀሳብ ካቀረቡ ከቀናት በኋላ የተደረግ ጉብኝት ነው። ይህንን ሃሳብ ያቀረቡት ሚያዚያ 15 ቀን አዲስ አበባ ሰሜን ኢትዮጵያ ሠላም እንዲሰፍን የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላበረከቱ ግለሰቦች እና ባለስልጣናት ዕውቅና ለመስጠት በተዘጋጀ ስነ-ሥርዓት ላይ ነው። በስነ-ሥርዓቱ ላይ የትግራይ ህዝብ ነፃነት ግንባር (ትህነግ/ህወሓት) መሪዎች፣ የአፍሪካ ህብረት አደራዳሪ ቡድን አባላት፣ የኢትዮጵያ መንግስት የድርድር ቡድን አባላት፣ የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ እና የቻይና የአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች ልዩ መልዕክተኛን ጨምሮ የተለያዩ ግለሰቦች ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስጋና የምስክር ወረቀት እና የሠላም ምልክት ተሸልመዋል።13
Footnotes
- 2
የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን፣ ‘ኢትዮጵያ -ኢሳት የአማርኛ ዜና ሚያዝያ 17, 2015፣’ ሚያዝያ 17, 2015
- 8
የአሜሪካ ድምፅ አማርኛ፣ ‘በደቡብ ኦሞ እና ደራሼ ልዩ ወረዳ ግጭት 22 ተጠርጣሪዎችን መያዙን ፖሊስ ገለጸ፣’ ሚያዚያ 23, 2015
- 11
አዲስ ማለዳ፣ ‘ከአላማጣ በተነሱ መንገደኞች ላይ በመተሀራ በተፈፀመ ጥቃት የሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ፣’ ሚያዝያ 22, 2015
- 12
ሪፖርተር፣ ‘የክልል አመራሮች ከትግራይ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት ጋር በመቀሌ ተገናኙ፣’ ሚያዝያ 19, 2015
- 13
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ‘#ኢቲቪ ጦርነት ይብቃ፣ ሰላምን እናጽና’ ሚያዚያ 15, 2015