ኢፒኦ ሳምንታዊ: ጷጉሜ 5, 2014- መስከረም 6, 2015
መሰጠረው ሳምንታዊ አስላቲኣዊ ዘቀባ ስለ ኢትዮጵያን የፖለቲካ ግጭቶች አሶኢት ዘቀል
Also available in English
- የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ብዛት: 3,350
- በተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 19,259
- በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተሰነዘሩ ጥቃቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 8,436
<h3><strong>
- የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ብዛት: 19
- በተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 75
- በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተሰነዘሩ ጥቃቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 32
የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
በአዲሱ የኢትዮጵያ አመት የመጀመሪያ ሳምንት በሰሜን ኢትዮጵያ በመንግስት ኃይሎች እና በትግራይ ህዝብ ነፃነት ግንባር (ትህነግ/ህወሓት) ኃይሎች መካከል ውጊያዎች ቀጥለዋል። ይሁን እንጂ የተቀረው የአገሪቱ ክፍል በአንጻራዊ ሁኔታ አነስተኛ ቁጥር ያላቸው የፖለቲካ አለመረጋጋት ሪፖርት በመደረጋቸው የተረጋጋ ነበር።

በተጨማሪም የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በመቀሌ በርካታ የድሮን ጥቃቶችን አድርጓል። ትህነግ/ህወሓት እነዚህ የአየር ድብደባዎች በሰላማዊ ሰዎች ላይ ያነጣጠረ መሆኑን ሲገልፅ ሌሎች ዘገባዎች ደግሞ የአየር ጥቃቱ የቡድኑን ወታደራዊ ማዕከላት እና የሚዲያ ማዕከል ደምጺ ወያኔ ላይ እንዳነጣጠረ አመላክተዋል (ትዊተር፣ @ረዳ_ጌታቸው፣ መስከረም 3, 2015፣
በኦሮሚያ ክልል ካለፉት ሳምንታት ጋር ሲነጻጸር ትንሽ ኩነቶች ተዘግበዋል። ባለፈው ሳምንት በምዕራብ ሸዋ ዞን ጊንጪ እና አምቦ መካከል በምትገኘው ሜቲ በምትባል ስፍራ የኦሮሚያ ክልል ልዩ ኃይል እንደሆኑ የሚገመት የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ታስሮ የነበረን መምህር በጥይት ገድለውታል። መምህሩ ጷጉሜ 4 ቀን ከቡራዩ ወደ ጀልዱ በአውቶብስ ሲጓዝ “ያለ ምክንያት” በቁጥጥር ስር ውሎ ጊንጪ ማረሚያ ቤት ውስጥ ታስሮ እንደነበር ተነግሯል (ኦኤምኤን፣ መስከረም 6, 2015)።