Skip to main content

ኢፒኦ ሳምንታዊ፡ ኀዳር 1-7, 2016

በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ውጊያዎች ውስጥ ሰዎች እንደተገደሉ ተመዘገበ።

23 November 2023

Also available in English

  • በቁጥር፡ ኢትዮጵያ, ኀዳር 1-7, 2016 - የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች ብዛት፡ 21, በፖለቲካ ግጭቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር፡ 91, በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተሰነዘሩ ጥቃቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር፡ 73
  • በቁጥር፡ ኢትዮጵያ, ኀዳር 2, 2015 -ኀዳር 7, 2016 - የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች ብዛት፡ 1,214, በፖለቲካ ግጭቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር፡ 3,769, በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተሰነዘሩ ጥቃቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር፡ 1,362

ኢትዮጵያን የሚመለከቱ በቁጥር የተደገፉ መረጃዎችን ከኢፒኦ የመረጃ መዝገብ እንዲሁም በዋናው የአክሌድ ኤክስፖርት መሳሪያ  ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።

የሁኔታዎች አጭር መግለጫ

በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች በአማፂ ቡድኖች እና በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መካከል የሚደረጉ ውጊያዎች የቀጠሉ ሲሆን በትግራይ ክልል ሰዎች የተገደሉበት አመጽ ተዘግቧል።

ኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት (በመንግስት የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ)-ሸኔ ተብሎ የሚጠራው) እና በኢትዮጵያ መንግስት መካከል የሰላም ንግግር እየተደረገ ያለ ቢሆንም በኦሮሚያ ክልል የተወሰኑ ውጊያዎች ተዘግበዋል። ባለፈው ሳምንት በክልሉ ስምንት የጦርነት ኩነቶች የተመዘገቡ ሲሆን ከእነዚህ መካከል አብዛኞቹ – ከስምንቱ ሰባቱ – በሰሜን ሸዋ ዞን ተመዝግበዋል (ከዚህ በታች ያለውን ካርታ ይመልከቱ)። በሰሜን ሸዋ ዞን የተከሰቱ አብዛኞቹ ውጊያዎች በኦነግ-ሸኔ እና በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መካከል የተደረጉ ናቸው። በሰሜን ሸዋ ዞን ከመስከረም አጋማሽ ጀምሮ በተከታታይ ውጊያዎች እየተከሰቱ ሲሆን ከእነዚህ ውጊያዎች መካከል አብዛኞቹ ዞኑ ከአማራ ክልል ጋር በአባይ ወንዝ በሚዋሰንበት በሰሜናዊ የዞኑ ክፍል የተመዘገቡ ናቸው። በዚህ ዞን ያለው አለመረጋጋት አልፎ አልፎ አዲስ አበባን የአማራ ክልል ዋና ከተማ ከሆነችው ከባህርዳር ጋር በሚያገናኘው መንገድ ላይ የሚደረጉ ጉዞዎችን አስተጓግሏል2 (ለተጨማሪ መረጃ  የኢፒኦ ሳምንታዊ፡ ጥር 28-የካቲት 4, 2014ን ይመልከቱ)።

በአማራ ክልል በፋኖ ታጣቂዎች እና በመከላከያ ሠራዊት መካከል የሚደረጉ ውጊያዎች እንደቀጠሉ ሲሆን ባለፈው ሳምንት በደቡብ ወሎ እና በምዕራብ ጎጃም ዞኖች ውጊያዎች ተዘግበዋል። እየተካሄዱ ያሉ ውጊያዎች መንገዶች እንዲዘጉ እያደረጉ ሲሆን በዚህም ቢያንስ አንድ የቀይ መስቀል የእርዳታ ጭነት መኪና የዋግ ኽምራ ዞን ህዝብ ዘንድ እንዳይደርስ እንቅፋት ሆኗል።3 በተጨማሪም የፋኖ ታጣቂዎች ጥቅምት 30 ቀን በኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢ ላይ በሚገኘው በቡሬ ወረዳ ሳንቶም እና ቤኮ ቶቦ ቀበሌዎች ውስጥ ቢያንስ አምስት የኦሮሞ ሰላማዊ ሰዎችን ባልታወቀ ምክንያት ተኩሰው መግደላቸው ሪፖርት ተደርጓል። ይህንን ጥቃት ተከትሎ አብዛኞቹ የኦሮሞ ብሔር ተወላጅ የሆኑ ከ3000 በላይ ነዋሪዎች ወደ አጎራባች የኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን ተሰደዋል። የአካባቢው የፋኖ ታጣቂዎች መሪ ድርጊቱን ቡድኑ አለመፈፀሙን በሚል ከመንግስት ጋር ግንኙነት ያላቸው ታጣቂዎችን ተጠያቂ አድርጓል።4

በቤንሻɲመልካ፣ ‘በቡs19

Country
Ethiopia
Region
Africa
Share on

Related content