Skip to main content

ኢፒኦ ሳምንታዊ ዘገባ (ግንቦት 6, 2016)

Ethiopian conflict updates: Recent violence in Amhara and Gambela regions.

17 May 2024

Also available in English

የሁኔታዎች አጭር መግለጫ

ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ ውስጥ በአማራ ክልል ውጊያዎች የተመዘገቡ ሲሆን በዚህም የተኩስ ልውውጥ ወቅት ሰላማዊ ሰዎች ቆስለዋል። በሌላ ቦታ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በምዕራብ ኦሮሚያ የምትገኝ ቁልፍ ከተማን የጎበኙ ሲሆን በጋምቤላ ክልል በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት መፈጸሙ ተነግሯል።

በአማራ ክልል በፋኖ እና በመከላከያ ሠራዊት መካከል በተደረገ የተኩስ ልውውጥ ሰላማዊ ሰዎች ተጎዱ

በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ፣ በሰሜን ወሎ፣ በሰሜን ሸዋ እና በምዕራብ ጎጃም ዞኖች በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ውጊያ መደረጉ ተዘግቧል። በሰሜን ወሎ ዞን ከደሴ ከተማ ወደ ወልዲያ ከተማ ሲጓዙ የነበሩ ሰዎች በመንገድ ዳር በፋኖ ታጣቂዎች እና በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ወታደሮች መካከል በነበረ የተኩስ ልውውጥ ቆስለዋል።1...

አብይ ነቀምቴን ጎበኙ

ሚያዚያ 30 ቀን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና ከኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ጋር በመሆን በምስራቅ ወለጋ ዞን ነቀምቴ ከተማ በተካሄደው የድጋፍ ሰልፍ ላይ ተገኝተዋል። ህዝቡን ባነጋገሩበት ወቅት ከሌሎች ጉዳዮች በተጨማሪ አካባቢው በፀጥታ ችግር ምክንያት በልማት ወደ ኋላ የቀረ መሆኑን ጠቅሰዋል።1

በጋምቤላ ክልል በሰላማዊ ሰዎች ላይ የደረሰ ጥቃት

በጋምቤላ ክልል ሚያዚያ 27 ቀን በጋምቤላ ዙሪያ ወረዳ አቦል ከተማ አቅራቢያ የህዝብ አውቶቢስ ላይ ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች ጥቃት ያደረሱ ሲሆን አውቶቢሱን ሲያጅቡ የነበሩ የክልሉ ፖሊስ አባላትን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ቆስለዋል። አውቶቢሱ ከኢታንግ...የጋምቤላ ክልል በኢትዮጵያ ውስጥ ሰላም ከሰፈነባቸው አካባቢዎች አንዱ

ኢትዮጵያ በጨረፍታ
ሚያዚያ 26-ግንቦት 2, 2016

ይህ መረጃ/ዳታ ከሚያዚያ 26 እሰከ ግንቦት 2, 2016 ያለውን ጊዜ ይሸፍናል። አክሌድ መረጃን እንዴት እንደሚሰበስብ እና ኩነቶችን እንዴት እንደሚመድብ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የአክሌድን የኮድ መጽሐፍን ይመልከቱ። በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ የተከሰቱ አንዳንድ ኩነቶች በዘገባ መዘግየት ምክንያት በሚቀጥሉት ሳምንታት ዳታ ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ።

የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች8: 22

-12% ከባለፈው ሳምንት ጋር ሲነፃፀር

ያለበት የተቃውሞ ሰልፍ9: 0

0% ከባለፈው ሳምንት ጋር ሲነፃፀር

የኩነት አይነቶች

ውጊያዎች: 19 ኩነቶች

ፍንዳታዎች/ የርቀት ግጭት: 0 ኩነት

ሰላማዊ ሰዎች ላይ የደረሱ ጥቃቶች: 3 ኩነቶች

የአመፅ ግጭት: 0 ኩነት

ሰልፎች: 0 ኩነት

ግጭት ያለበት የተቃውሞ ሰልፍ: 0 ኩነት

Footnotes

  1. 1

    ቢቢሲ አማርኛ፣ ‘“ኦሮሞ ነጻ ወጥቷል፤ ትናንትና ታግለን በደማችን አሸንፈናል”- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በወለጋ፣’ ሚያዚያ 30, 2016

  2. 8

    ይህ ውጊያዎችን፣ ፍንዳታዎች/ የርቀት ግጭት እና ሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን የሚመለከቱ ኩነቶችን እንዲሁም የአመፅ ግጭት ንዑስ ኩነት የሆነውን የአመፅ ኩነትን ይጨምራል።

  3. 9

    ይህ የተቃውሞ ሰልፎች የኩነት አይነትን እንዲሁም የአመፅ ግጭት ንዑስ ኩነት የሆነውን ግጭት ያለበት የተቃውሞ ሰልፍ ኩነትን ይጨምራል።

Related content