Skip to main content

ኢፒኦ ሳምንታዊ ዘገባ (መጋቢት 24, 2016)

በትግራይ እና አማራ ክልል ይገባኛል ጥያቄ በሚነሳባቸው አካባቢዎች በወቅታዊ ወቅት ውጊያ የተቀሰቀሰ።

4 April 2024

Also available in English

የሁኔታዎች አጭር መግለጫ

ባለፈው ሳምንት በትግራይ ክልል በደቡብ ትግራይ ዞን አወዛጋቢ አካባቢዎች ዳግም ውጊያ ሲቀሰቀስ በኦሮሚያ ክልል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን (////ክ) የኃይማኖት አባቶችን ላይ ጥቃት መፈጸሙ ተዘግቧል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በጋምቤላ ክልል የአካባቢ ግጭት ቀጥሏል።

በትግራይ ክልል የይገባኛል ጥያቄ በሚነሳባቸው አካባቢዎች ዳግም የተቀሰቀሰው ውጊያ

መጋቢት 16 እና 17 በትግራይ እና በአማራ ብሔር ታጣቂዎች መካከል የይገባኛል ጥያቄ በሚነሳባቸው በደቡብ ትግራይ ዞን ውስጥ ዳግም ውጊያ የተቀሰቀሰ ሲሆን በአላማጣ ወረዳ በር ተክላይ አካባቢ ጦርነት ተመዝግቧል። በአላማጣ ወረዳ የጣኦ እና አዲስ ብርሃን ቀበሌዎችን የትግራይ ታጣቂዎች ተቆጣጥረዋል። በዚህ ውጊያ አራት የአማራ ታጣቂዎች መሞታቸው ሲታወቅ 12 ሰዎች ቆስለዋል። በትግራይ እና በአማራ ብሔር ታጣቂዎች መካከል ውጊያ መፈጠሩን ተከትሎ ተጨማሪ የአማራ ተዋጊዎች@ ይተመሆY ለመከላከል ሲሞክር የኢትዮጵያ  መከላከያ ሠራዊት ከአማራ ብሔር ታጣቂዎች ጋር ተዋግቷል። እነዚህን ውጊታዎች ተከትሎ መጋቢት 22 ቀን በደቡብ ትግራይ ዞን ኮረም ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሂዶ የነበረ ሲሆን ሰልፈኞቹ ተጨማሪ ግጭት ከመፈጠሩ በፊት የይገባኛል ጥያቄ የሚነሳባቸው አካባቢዎችን እጣ ፋንታ መንግስት እንዲፈታ ጠይቀዋል።1

የሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት በጥቅምት 2015 ካበቃ በኋላ በደቡብ ትግራይ ዞንበይፋ የትግራይ ክልል አካል የሆነ ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ በአማራ ክልል ባለስልጣናት የሚተዳደር ውጊያ ለመጀመሪያ ጊዜ የተመዘገበው በየካቲት ወር ነበር። በአማራ እና ትግራይ ክልል መንግስታት መካከል ያለው ውጥረት እየጨመረ መቷል። ባለፈው ሳምንት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የአማራ ክልል ባለስልጣናት የይገባኛል ጥያቄ የሚነሳባቸውን ቦታዎች በአማራ ክልል አድርገው የሚያሳዩ የመማሪያ መጽሐፍትን አስመልክቶ ለአማራ ክልል ማስጠንቀቂያ ስጥቷል።2 የአማራ ክልል መንግስት በሰጠው ምላሽ በታሪክ እነዚህ የይገባኛል ጥያቄ የሚነሳባቸውን ቦታዎች የአማራ መሆናቸውን በመግለጽ የትግራይ አስተዳደር ከሁከት ቀስቃሽ መግለጫዎች እንዲቆጠብ ጠይቋል።3 በኢትዮጵያ ውስጥ ከተከሰቱት ጦርነኦች አንጻር በቅርብ የተቀሰቀሰው ውጊያ መጠኑ አነስተኛ ቢሆንም በፕሪቶሪያ ስምምነት የተገኘው ሰላም ላይ ቀጥተኛ አደጋ የሚያስከትል በመሆኑ በዚህ አካባቢ የሚከሰቱ ለውጦች ጉልህ ናቸው

ይህ በእንዲህ እንዳለ በመጋቢት 13 እና 14 የትግራይ ጊዜያዊ ክልላዊ አስተዳደር 212 ምርኮኞች መልቀቁን ያስታወቀ ሲሆን ይህም በአፍሪካ ህብረት ምሪት የክልል እና የፌዴራል መንግስት ባለስልጣናት እና  የትግራይ ህዝብ ነፃነት ግንባር አባላት ያደረጉትን ስብሰባ ተከትሎ የተደረገ መልካም እንቅስታሴ ነው።4

ጦርነት በኦሮሚያ ክልል

በኦሮሚያ ክልል ውጊያዎች እና በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚደርሰው ጥቃት ቀጥሏል። ባለፈው ሳምንት በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን አመያ ወረዳ በኦሮሞ&amp;nbsp;ነጻነት&amp;nbsp;ሠራዊት&amp;nbsp;(</span><span>ኦነሠ</span>)&amp;nbsp;— በመንግሥት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ)-ሸኔ ተብሎ የሚጠራው&amp;nbsp;— እና በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መካከል ውጊያ የነበረ ሲሆን በዚሁም የሶስት ሰዎች ህይወት መጥፋቱ ተዘግቧል። መጋቢት 13 እና 14 በቄለም ወለጋ ዞን በጊዳሚ ወረዳ እና በምዕራብ ወለጋ ዞን ቤጊ ወረዳ ተጨማሪ ውጊያዎች መከሰታቸውም ታውቋል። በእነዚህ ወረዳዎች የተቀሰቀሰውን ውጊያ ተከትሎ የመንግስት ኃይሎች ኦነሠ/ኦነግሸኔ ይደግፋሉ በማለት የከሰሷቸውን 16 ሰላማዊ ሰዎችን ተኩሰው መግደላቸው ተዘግቧል።5

በሌላ ቦታ በምዕራብ አርሲ ዞን ዶዶላ ወረዳ ዶዶላ ከተማ መጋቢት 16 ቀን ታጣቂዎች ሁለት የኃይማኖት አባቶችን ከአምስት ቤተሰባቸው እና ሌሎች አራት ሰላማዊ ሰዎች ጋር መግደላቸው ታውቋል። የአካባቢው የወረዳ አስተዳደር ምንጮች ኦነሠ/ኦነግሸኔ ለዚህ ጥቃት ተጠያቂ ሲያደርጉ ሌሎች ምንጮች ጥቃቱ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች የተፈፀመ መሆኑን ጠቁመዋል።6 የመንግስት ምንጮች በጥቃቱ ላይ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል።7 በኦሮሚያ ክልል በኢ//// ላይ የሚሰነዘረው ጥቃት አልፎ አልፎ የሚፈጸም ሲሆን በቅርብ የተከሰተው ጥቃት በየካቲት ወር በምስራቅ ሸዋ ዞን ዝቋላ ገዳም ላይ የተፈጸመ ጥቃት ነው።

በጋምቤላ ክልል የቀጠለው ግጭት

በጋምቤላ ክልል በአቦቦ ወረዳ አኝዋክ ዞን መጋቢት 17 ቀን ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች አምስት አርብቶ አደሮችን ተኩሰው መግደላቸው ተከትሎ በክልሉ ያለው ግጭት ቀጥሏል። በማግስቱ የአኝዋክ ብሔር ታጣቂዎች በአቦል ወረዳ እና&amp;nbsp; ታራፓም የስደተኞች ካምፕ መካከል ሲጓዝ በነበረ የህዝብ አውቶቡስ ላይ በኢታንግ ልዩ ወረዳ ጥቃት በመሰንዘራቸው አምስት ሰላማዊ ሰዎች መሞታቸው ተዘግቧል። የጋምቤላ የመንግስት ባለስልጣናት ችግሩን አምነው የክልሉን የፀጥታ መዋቅር አካላት ተጠያቂ በማድረግ እሰር መፈፀማቸውን አመልክተዋል።8

2013 ጀምሮ የጋምቤላ ክልል በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት እጅግ ሰላማዊ አካባቢዎች አንዱ ነበረ። ባለፉት ጥቂት ወራት ውስጥ ተከታታይ ግጭቶች መከሰታቸው ግን ይህ ሰላም እየተቀየረ የመጣ ይመስላል። መጋቢት 9 ቀን በጋምቤላ ከተማ የፖሊስ አባል ላይ የተከፈተው ተኩስ በክልሉ በቅርቡ የተከሰተ ኩነት ነው።

ኢትዮጵያ በጨረፍታ
መጋቢት 14–20, 2016

ይህ መረጃ/ዳታ ከመጋቢት 14 እስከ 20, 2016 ያለውን ጊዜ ይሸፍናል። አክሌድ መረጃን እንዴት እንደሚሰበስብ እና ኩነቶችን እንዴት እንደሚመድብ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የአክሌድን የኮድ መጽሐፍን ይመልከቱ። በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ የተከሰቱ አንዳንድ ኩነቶች በዘገባ መዘግየት ምክንያት በሚቀጥሉት ሳምንታት ዳታ ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ።

  • የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች9: 22
  • -35% ከባለፈው ሳምንት ጋር ሲነፃፀር
  • የሰልፍ ኩነቶች10: 1
  • -50% ከባለፈው ሳምንት ጋር ሲነፃፀር
  • ውጊያዎች: 14 ኩነቶች
  • ፍንዳታዎች/ የርቀት ግጭት: 17 ኩነቶች
  • ሰላማዊ ሰዎች ላይ የደረሱ ጥቃቶች: 4 ኩነቶች
  • የአመፅ ግጭት: 0 ኩነት
  • ሰልፎች: 1 ኩነት
  • ግጭት ያለበት የተቃውሞ ሰልፍ: 0 ኩነት
  • %;>;>

Related content