ኢፒኦ ሳምንታዊ ዘገባ (መጋቢት 3, 2016)
Amhara and Oromia regions witness conflict; Fano militants attack civilians.
Also available in English
የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
በአማራ ክልል በፋኖ ታጣቂዎች እና በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መካከል የሚደረገው ውጊያ ተባብሶ የቀጠለ ሲሆን በኦሮሚያ ክልል የፋኖ ታጣቂዎች በሰሜን ሸዋ ዞን አዋሳኝ አካባቢዎች በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት አድርሰዋል። በሌላ የክልሉ ስፍራ በምዕራብ ጉጂ ዞን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (ኦነሠ) — በመንግሥት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ)-ሸኔ ተብሎ የሚጠራው — ከመንግሥት ኃይሎች ጋር ዳግም ያገረሸውን ውጊያ ተከትሎ የተለያዩ ቦታዎችን ተቶጣጥሯል።
በአማራ ክልል ውጊያዎች ተጠናክረው ቀጥለዋል
በአማራ ክልል በፋኖ ታጣቂዎች እና በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መካከል ውጊያዎች በምስራቅ ጎጃም፣ ምዕራብ ጎጃም፣ ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ወሎ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች መደረጋቸው ተዘግቧል። ልክ እንደበፊቱ ሳምንት የባለፈው ሳምንትም አብዛኛዎቹ ውጊያዎች የተደረጉት በምዕራብ ጎጃም ዞን ነበር። በሰሜን ሸዋ ዞን በሸዋ ሮቢት ከተማ እየተካሄደ ያለውን ውጊያ ተከትሎ በፖሊስ ጣቢያ ላይ በደረሰ የሞርታር ጥቃት አራት ፖሊሶች ሲሞቱ ሌሎች አራት ቆስለዋል። በምስራቅ ጎጃም ዞን ሰኞ ገበያ እና ደብረ ወርቅ ከተሞች በፋኖ ታጣቂዎች ላይ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ባተደረገው ዘመቻ በአጠቃላይ 41 ሰዎች መሞታቸው ታውቋል። በምዕራብ ጎጃም ዞን ፈረስ ቤት ከተማ በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች የካቲት 24 ጀምሮ ለአራት ቀናት በተደረገ ውጊያ ቁጥራቸው ለጊዜው በውል ያልተገለጸ የሰው ህይወት ጠፍቷል። የመንግስት ኃይሎች ከታጣቂዎች ጋር ውጊያ አድርገው ከተማዋን የካቲት 17 ቀን ከተቆጣጠሩ በኋላ በከተማዋ የሚደረግው ውጊያ ተባብሷል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የካቲት 26 ቀን የፋኖ ታጣቂዎች ከባህር ዳር፣ ደብረታቦር፣ ንፋስ መውጫ፣ ጋሸ እስከ አላማጣ ከተሞች ድረስ ያለውን የከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ ጉዳት በማድረሳቸው በክልሉ ሰፊ የመብራት መቆራረጥ አስከትሏል።1 የካቲት 28 ቀን የአማራ ክልል መንግስት ባለፉት ጥቂት ወራት በክልሉ በተከሰተው ውጊያ ወደ 15 ቢሊዮን ብር የሚገመት ንብረት — ወደ 264 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር — የሚጠጋ ንብረት መውደሙን አመልክቷል።2 በተመሳሳይ ቀን የአለም የገንዘብ ድርጅት የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ግጭት መስፋፋቱን አስመልክተው ስጋታቸውን ገልፀው ግጭቶቹን “አስጨናቂ እና አሳሳቢ” ሲሉ ገልጥፀዋል።3 የሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት ማብቃቱን ተከትሎ እየተሻሻለ የመጣው የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ግንኙነት ላይ እየሰፋ ያለው ግጭት አሉታዊ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል።
የኦነሠ/ኦነግ-ሸኔ በኦሮሚያ ምዕራብ ጉጂ ዞን ውስጥ የተቆጣጠረው ግዛት
ባለፈው ሳምንት በኦነሠ/ኦነግ-ሸኔ እና በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መካከል ውጊያዎች በአርሲ፣ በምዕራብ ጉጂ፣ በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ፣ በደቡብ ምዕራብ ሸዋ እና በምዕራብ ወለጋ ዞኖች መደረጋቸው ተዘግቧል። በምዕራብ ጉጂ ዞን የካቲት 25 ቀን ኦነሠ/ኦነግ-ሸኔ ኃይሎች በገላና ወረዳ በኮምቦልቻ፣ ኤጀርሳ፣ መታር እና ጀሪም ቀበሌዎችን ከኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ጋር ከተዋጉ በኃላ ተቆጣጥረዋል። በመሆኑም በመቶዎች የሚቆጠሩ የመንግስት ሠራተኞች እና የቀበሌ ታጣቂዎች በኦነሠ/ኦነግ-ሸኔ ታጣቂዎች ሊደርስባቸው የሚችለውን ጥቃት በመፍራት ከእነዚህ አካባቢዎች ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ተሰደዋል።4
የካቲት 28 ቀን በሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ የፋኖ ታጣቂዎች ዘጠኝ ሰላማዊ ሰዎችን ተኩሰው ገድለዋል። በኦሮሚያ ክልል በሚተዳደረው ነገር ግን በሁለቱም አማራ እና ኦሮሞ ብሔረሰቦች የይገባኛል ጥያቄ በሚነሳበት በዚህ ወረዳ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት፣ ውጊያ እና ንብረት መውደም ምክንያት የሆኑ ድንበር ተሻጋሪ ክስተቶች በወረዳው ተደጋግመው ይከሰታሉ።5

ኢትዮጵያ በጨረፍታ
ከየካቲት 23–29, 2016
ይህ መረጃ/ዳታ ከየካቲት 23–29, 2016 ያለውን ጊዜ ይሸፍናል። አክሌድ መረጃን እንዴት እንደሚሰበስብ እና ኩነቶችን እንዴት እንደሚመድብ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የአክሌድን የኮድ መጽሐፍን ይመልከቱ። በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ የተከሰቱ አንዳንድ ኩነቶች በዘገባ መዘግየት ምክንያት በሚቀጥሉት ሳምንታት ዳታ ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ።
- የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች: 6 2
- +100% ከባለፈው ሳምንት ጋር ሲነፃፀር
- ውጊያዎች: 35 ኩነቶች
- ፍንዳታዎች/ የርቀት ግጭት: 1 ኩነት
- ሰላማዊ ሰዎች ላይ የደረሱ ጥቃቶች: 7 ኩነቶች
- የአመፅ ግጭት: 1 ኩነት
- ሰልፎች: 1 ኩነት
- ግጭት ያለበት የተቃውሞ ሰልፍ: 1 ኩነት
Footnotes
- 1
የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን፣ ‘በህዝቡ ስቃይ የሚሰራ የትኛውም ፖለቲካ ውጤቱ ምንም መሆኑን መረዳት ይገባል፣’ የካቲት 26, 2016
- 2
አዲስ ስታንዳርድ፣ ‘ዜና፡- በቅርቡ በአማራ ክልል የተቀሰቀሰው ወታደራዊ ግጭት ከ15 ቢሊዮን ብር በላይ ጉዳት አድርሷል፣’ የካቲት 29, 2016
- 3
አሸናፊ እንዳለ፣ ‘“አስጨናቂ እና አሳሳቢ”፡ አይ ኤም ኤፍ በአማራ፣ ኦሮሚያ በተከሰቱ ግጭቶች ላይ፣’ የኢትዮጵያ ሪፖርተር፣ የካቲት 30, 2016
- 4
- 5
- 6
ይህ ውጊያዎችን፣ ፍንዳታዎች/ የርቀት ግጭት እና ሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን የሚመለከቱ ኩነቶችን እንዲሁም የአመፅ ግጭት ንዑስ ኩነት የሆነውን የአመፅ ኩነትን ይጨምራል። 44-6 % ከባለፈው ሳምንት ጋር ሲነፃፀርየሰልፍ ኩነቶች: