Skip to main content

ኢፒኦ ሳምንታዊ ዘገባ (ሚያዚያ 15, 2016)

ባለፈው ሳምንት በበትግራይ ክልል የይገባኛል ጥያቄ በሚነሳብቸው በደቡብ ትግራይ ዞን በሚገኙ አካባቢዎች በአማራ እና በትግራይ ታጣቂዎች መካከል ውጊያ የተሰፋፋ ሲሆን በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች በመንግስት ኃይል እና በአማፂያን መካከል የሚደረጉ ውጊያዎች ቀጥለዋል።

24 April 2024

Also available in English

የሁኔታዎች አጭር መግለጫ

ባለፈው ሳምንት በበትግራይ ክልል የይገባኛል ጥያቄ በሚነሳብቸው በደቡብ ትግራይ ዞን በሚገኙ አካባቢዎች በአማራ እና በትግራይ ክልል ታጣቂዎች መካከል ውጊያ የተሰፋፋ ሲሆን በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች በመንግስት ኃይል እና በአማፂያን መካከል የሚደረጉ ውጊያዎች ቀጥለዋል።

በትግራይ የይገባኛል ጥያቄ በሚነሳባቸው አካባቢዎች የተሰፋፋው ውጊያ

ከአማራ እና ከትግራይ ክልል በመጡ ታጣቂ ኃይሎች መካከል በደቡብ ትግራይ ዞን በራያ አላማጣ፣ ዛታ፣ ኦፍላ እና አላማጣ ወረዳዎች የይገባኛል ጥያቄ በሚነሳባቸው አካባቢዎች በተዘገቡ ውጊያዎች ምክንያት ውጥረት ጨምሯል። ውጊያው ሚያዚያ 5 ጀምሮ እስከ ሚያዚያ 7 ድረስ የዘለቀ ሲሆን የፌዴራል ኃይሎች ጣልቃ ገብተው አላማጣ ከተማን ሲቆጣጠሩ ውጊያው አቁሟል። የሰሜን ወሎ እና የዋግ ኽምራ ዞኖች ባለስልጣናት እንደገለፁት ከሆነ ዳግም በተቀሰቀሰው ግጭት የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር ከ50,000 በላይ ደርሷል።1

የሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት ጥቅምት 2015 ካበቃ በኋላ በደቡብ ትግራይ ዞን — በይፈ የትግራይ ክልል አካል የሆነ ነገር ግን በአማራ ክልል ባለስልጣናት የሚተዳደር — ውጊያ ለመጀመሪያ ጊዜ የተከሰተው በየካቲት ወር ነበር። ውጊያው በመጋቢት ወርም ወጥሏል። የባለፈው ሳምንት ግጭት በአካባቢ ሽፋን ሆነ በቁጥር ከፍተኛ በመሆኑ ውጊያው እየጨመረ እንደመጣ የሚያሳይ ሲሆን በፕሪቶሪያ ስምምነት የተገኘውን ሰላም አደጋ ላይ ይጥላል።

የትግራይ ጊዜያዊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸው ረዳ ውጊያው “የፕሪቶሪያ ስምምነት ከባድ ጠላቶች ሥራ” መሆኑን በመግለጫቸው አመልክተዋል።2 የአማራ ክልላዊ መንግስት መግለጫ ያወጣ ሲሆን የትግራይ ህዝብ ነፃነት ግንባርን የማንነት ጥያቄዎች በሚነሳባቸው ማለትም የአማራ ክልል የይገባኛል ጥያቄ በሚያናሳባቸው ምዕራብ እና የደቡብ ትግራይ ዞኖችን በመውረር እና ጦርነት እንዲቀሰቅስ አድርጓል ሲል ከሷል።3 የፌዴራል ባለስልጣናት በውጊያው ላይ አስተያየታቸውን የሰጡ ሲሆን ሁሉም ወገኖች የፕሪቶሪያን ስምምነት እንዲያከብሩ የጠየቁ ሲሆን የይገባኛ ጥያቄ የሚነሳባቸውን አካባቢዎችን ጉዳይ በሪፈረንደም ለመፍታት ያላቸውን ቁርጠኝነት ዳግም አመላክተዋል።4 በእነዚህ አካባቢዎች ውጊያዎች በስፋት ሊቀጥሉ የሚችል ሲሆን በሚቀጥሉት ሳምንታት ሰፊ ግጭት፣ ሰልፍ እና ብጥብጥ ሊያስከትሉ ይችላል።

በአማራ የቀጠለው ውጊያ

በአማራ ክልል በመንግስት ታጣቂዎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ውጊያ እንደነበርም ተዘግቧል። በምዕራብ ጎጃም፣ በማዕከላዊ ጎንደር፣ በደቡብ ጎንደር፣ በሰሜን ሸዋ እና በአዊ ዞኖች የፋኖ ታጣቂዎች እና የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ወታደሮች መካከል ውጊያ መፈጠሩ ተነግሯል። በምዕራብ ጎጃም ዞን ፈረስ ቤት — ከህዳር ወር ጀምሮ በተደጋጋሚ ግጭት በሚፈጠርበት አካባቢበነበረ ውጊያ የመንግስት ኃይሎች 64 የፋኖ ተዋጊዎችን መግደላቸውን እና በርካቶችን ማቁሰላቸውን አስታውቀዋል5 በአዊ ዞን በነበረ ውጊያ ወቅት በመንግስት ወታደሮች የተተኮሰው ከባድ መሳሪያ በትንሹ አምስት ሰላማዊ ሰዎች መሞታቸው ተነግሯል።

ውጊያ እና የትራንስፖርት ገደብ በኦሮሚያ

በኦሮሚያ ክልል የሚደረጉ ውጊያዎች ቀጥለዋል። በምስራቅ ሸዋ ዞን በባቱ (ዝዋይ) ከተማ እና አካባቢዋ እንዲሁም በምስራቅ ወለጋ እና ምዕራብ ሸዋ ዞኖች ኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (ኦነሠ) — በመንግሥት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ)-ሸኔ ተብሎ የሚጠራው — እና በመንግሥት ኃይሎች መካከል ውጊያ ተደርጓልከሳምንት በፊት አንድ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ፖለቲከኛ በተገደሉበት

በመቂ ከተማና አካባቢው በትራንስፖርት ሹፌሮች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት መፈፀሙ ታውቋል። የፖለቲከኛውን ግድያ ተከትሎ የታወጀ የትራንስፖርት እንቅሰቃሴ ገደብን ለማስከበር የኦነሠ/ኦነግሸኔ ኃይሎች ቢያንስ አንድ ሹፌር ሲገድሉ አራት የነዳጅ ማደያ ሠራተኞች አግተው የወሰዱ ሲሆን አንድ የጭነት መኪና እና በርካታ ባጃጆች አቃጥለዋል6

ኢትዮጵያ በጨረፍታ

ሚያዚያ 5-11 2016

ይህ መረጃ/ዳታ ከሚያዚያ 5 እሰከ 11, 2016 ያለውን ጊዜ ይሸፍናል። አክሌድ መረጃን እንዴት እንደሚሰበስብ እና ኩነቶችን እንዴት እንደሚመድብ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የአክሌድን የኮድ መጽሐፍን ይመልከቱ። በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ የተከሰቱ አንዳንድ ኩነቶች በዘገባ መዘግየት ምክንያት በሚቀጥሉት ሳምንታት ዳታ ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ።

  • የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች7: 46

    +24% ከባለፈው ሳምንት ጋር ሲነፃፀር
  • የሰልፍ ኩነቶች8: 2

    -50% ከባለፈው ሳምንት ጋር ሲነፃፀር
  • ውጊያዎች: 33 ኩነቶች
  • ፍንዳታዎች/ የርቀት ግጭት: 0 ኩነት
  • ሰላማዊ ሰዎች ላይ የደረሱ ጥቃቶች: 13 ኩነቶች
  • የአመፅ ግጭት: 0 ኩነት
  • ሰልፎች: 2 ኩነት
  • ግጭት ያለበት የተቃውሞ ሰልፍ: 0 ኩነት

Footnotes

  1. 1

    የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ፣ ‘ኢትዮጵያ፡ ወቅታዊ መረጃ ቁጥር 2፡ ተፈናቃዮች በአማራ ክልል በሰሜን ወሎ እና ዋግ ኽምራ ዞኖች (ሚያዚያ 14, 2016)፣’ ሚያዚያ 14, 2016

  2. 2

    ኤክስ@ረዳ_ጌታቸው፣ ሚያዚያ 7, 2016

  3. 3

    የአማራ ክልል ፕሬዝደንት ቢሮ፣ ‘ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የተሰጠ መግለጫ፣’ ሚያዚያ 9, 2016

  4. 4

    ቪኦኤ አማርኛ፣ ‘በራያ አላማጣ አካባቢ ግጭት የፌደራል መንግሥት ማሳሰቢያ ሰጠ፣’ ሚያዚያ 11, 2016

  5. 5

    አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን፣ ‘ፈረስ ቤትን ለመቆጣጠር የመጣው የጽንፈኛ ኃይል መመታቱን የጎጃም ኮማንድፖስት አስታወቀ፣’ ሚያዚያ 7, 2016

  6. 6

    ገልሞ ዳዊት፣ ‘የበቴ ዑርጌሳን ግድያ ተከትሎ በባቱ እና መቂ ከተሞች በተቀሰቀሰ ግጭት ውጥረት መስፈኑ ተገለጸ፣’ ቪኦኤ አማርኛ፣ ሚያዚያ 9, 2016

  7. 7

    ይህ ውጊያዎችን፣ ፍንዳታዎች/ የርቀት ግጭት እና ሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን የሚመለከቱ ኩነቶችን እንዲሁም የአመፅ ግጭት ንዑስ ኩነት የሆነውን የአመፅ ኩነትን ይጨምራል።

  8. 8

    ይህ የተቃውሞ ሰልፎች የኩነት አይነትን እንዲሁም የአመፅ ግጭት ንዑስ ኩነት የሆነውን ግጭት ያለበት የተቃውሞ ሰልፍ ኩነትን ይጨምራል።

Related content