Skip to main content

ኢፒኦ ሳምንታዊ ዘገባ (ጥር 14, 2016)

የኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎች የተከሰቱ ግጭቶችንና ጉዳይ ይዋቅሩ.

26 January 2024

Also available in English

የሁኔታዎች አጭር መግለጫ

በኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች ከሽምቅ ውጊያ ጋር የተያያዙ ግጭቶች የቀጠሉ ሲሆን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እስራቶች ተዘግበዋል። በአማራ ክልል ውጊያዎችን እና የአየር ጥቃቶችን ያካተተ በፋኖ ታጣቂዎች እና በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መካከል የሚደረግ ጦርነት ቀጥሏል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በኦሮሚያ ክልል በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት(ኦነሠ) — በመንግስት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (አነግ)-ሸኔ ተብሎ በሚጠራው — እና በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መካከል የተወሰኑ ውጊያዎች መደረጋቸው ተዘግበዋል። እንዲሁም በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች አዋሳኝ ቦታዎች ላይ በቀበሌ ታጣቂዎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ግጭት መከሰቱ ተዘግቧል። በአጠቃላይ በኢትዮጵያ የባለፈው ሳምንት ከቀደመው ሳምንት ጋር ሲነፃፀር የግጭት መጠን ጨምሯል።

ውጊያ እና የአየር ጥቃቶች በአማራ ክልል

በአማራ ክልል ያለው አለመረጋጋት የቀጠለ ሲሆን በፋኖ ታጣቂዎች እና በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መካከል በአዊ፣ በሰሜን ወሎ፣ በምዕራብ ጎጃም እና በማዕከላዊ ጎጃም ዞኖች ውጊያዎች ተዘግበዋል። በሁለቱ ቡድኖች መካከል በምዕራብ ጎጃም ዞን አዴት ከተማ ለአራት ተከታታይ ቀናት የዘለቀ ጠንካራ ውጊያ መደረጉ ሪፖርት ተደርጓል። በውጊያው ወቅት በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ቢያንስ ሁለት የአየር ጥቃቶች የተደረጉ ሲሆን በዚህም ሪፖርት የተደረጉ 32 ሰዎች ተገድለዋል። በተጨማሪም በአዊ ዞን ፈንዲቃ ከተማ በተከሰተው ውጊያ የብዙ ሰዎችን ህይወት ማለፉን የተነገረ ሲሆን ይህ ግን በገለልተኛ ወገን አልተጣራም። ጥር 3 ቀን በሰሜን ሸዋ ዞን አለም ከተማ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የፋኖ ታጣቂዎች የሚጠቀሙበት የመዝናኛ ማዕከል ላይ የድሮን ጥቃት የፈፀመ ሲሆን በዚህም ሁለት ሰዎችን መገደላቸው እና አንዳንድ ሰላማዊ ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት መድረሱ ተነግሯል።1

በኦሮሚያ ክልል ያሉ የተለያዩ ግጭቶች

በኦሮሚያ ክልል በኦነሠ/ኦነግ-ሸኔ እና በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መካከል የሚደረግ ውጊያ ቀጥሏል። ይሁን አንጂ ከህዳር ወር መጨረሻ ጀምሮ በሁለቱ አካላት መካከል የሚደረጉ ውጊያዎች ቀንሰዋል። ጥር 3 ቀን የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን በጉድሩ ወረዳ የኦነሠ/ኦነግ-ሸኔ ካምፕን ኢላማ በማድረግ በፈፀመው የድሮን ጥቃት አራት ሰዎች መገደላቸው ተዘግቧል። ይህንኑ የድሮን ጥቃት ተከትሎ በጉደሩ ወረዳ በሹንኬ እና አቤይ ሮቢ ቀበሌዎች ከጥር 4 እስከ 6 ቀን ለሶሰት ቀናት የዘለቀ ውጊያ መደረጉን ዘገባዎች ያሳያሉ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ጥር 7 ቀን በሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ ጉንዶ መስቀል ከተማ አቅራቢያ በሚገኙ ስፍራዎች — የኦሮሚያ እና የአማራ ክልል ወሰን አካባቢ — ላይ የፋኖ ታጣቂዎች ከአካባቢው የቀበሌ ታጣቂዎች ጋር ተዋግተዋል። በዚህ ውጊያ ምክንያት ቢያንስ 10 ሰዎች መገደላቸው የተዘገበ ሲሆን አንዳንድ ቤቶችም ተቃጥለዋል። ባለፈው ዓመት በሰሜን ሸዋ ዞን ያለው የፖለቲካ ግጭት በ60% አካባቢ የጨመረ ሲሆን ከእነዚህ ግጭቶች አብዛኛዎቹ በደራ ወረዳ የተከሰቱ ናቸው። በደራ ወረዳ ከተከሰቱ የፖለቲካ ግጭቶች ከ80% በላይ የሚሆኑት በነሐሴ 2015 እስከ ታኀሣሥ 2016 ባለው ጊዜ ውስጥ የተመዘገቡ ናቸው።

ከኢትዮጵያ ያለው ያልተማከለ የፋኖ ታጣቂዎች ስምሪት እና ታጣቂዎቹ የአማራን ማህበረሰብ ከመከላከል አንፃር የያዙት የተለያዩ የፖለቲካ አቋሞች ሲታዩ በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሱ የአማራ ብሔር ተወላጅ ታጣቂዎች በአማራ ክልል ከሚንቀሳቀሰው ፀረ-መንግስት ከሆነው የፋኖ አማጺ ጋር ግንኙነት ሊኖራቸውም ላይኖራቸውም አንደሚችል ያሳያል። የአማራ እና የኦሮሞ ማህበረሰቦች በሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ላይ በተደጋጋሚ ይጋጫሉ። በሁለቱ ቡድኖች መካከል ያለው ውጥረት ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሰው የአማራ ብሔር ታጣቂዎች በመጋቢት 2014 ላይ 28 የኦሮሚያ ክልል የፀጥታ ኃይል አባል የሆኑ — የቀበሌ ታጣቂዎች እና የክልሉ የፖሊስ አባላትን — በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን እና በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አዋሳኝ ላይ በሚገኘው እና በሁለቱ ክልሎች የይገባኛል ጥያቄ በሚያነሱበት አካባቢ ላይ ተኩሰው በገደሉበት ወቅት ነበር። ይህ ክስተት በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች አመራሮች መካከል ውጥረት እንዲጨምር ያደረገ ሲሆን ኩነቱን በሚመለከት ሁለቱም ወገኖች የሚቃረኑ መግለጫዎችን ሰተዋል። በወቅቱ የኦሮሚያ ክልል መንግስት ለድርጊቱ የአማራ ብሔር ታጣቂዎችን የከሰሰ ሲሆን በአማራ ክልል ስር የሚገኘው የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር በበኩሉ ክስተቱ የኦሮሞ ብሔር ታጣቂዎች አንድ የፌዴራል ፖሊስ አባልን ተኩሰው መግደላቸውን ተከትሎ የተፈጠረ መሆኑን አስረድቷል2)።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የተፈፀሙ አስራቶች  

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሐዲያ ዞን ሆሳዕና ከተማ የፀጥታ ኃላፊዎች ሀሰተኛ መረጃ በማሰራጨት እና ግጭት በመቀስቀስ የከሰሱዋቸውን የአንድ ሚዲያ ባለቤትን ጨምሮ 29 ግለሰቦችን ማሰራቸውን ገልፀዋል።3 የሐዲያ ዞን በተከታታይ የመንግስት ሰራተኞችን ደሞዝ ከመክፈል ጋር በተያያዘ ችግሮች የገጠመው ሲሆን ከዚሁ ጋር በተያያዘ የሚፈፀሙ የጅምላ እስር እና የተቃውሞ ሰልፎች  ከሐምሌ 16, 2015 እስከ ታኀሣሥ 21, 2016 ባለው ጊዜ ውስጥ በተከታታይ ተዘግበዋል። በዞኑ በገንዘብ እጦት ምክንያት ትምህርት ቤቶች እና ሌሎች የመንግስት ተቋማት መደበኛ ስራቸውን ማከናወን አልቻሉም።3

ኢትዮጵያ በጨረፍታ
4-10 ጥር 2016

ይህ መረጃ/ዳታ ከታኅሣሥ 22 እስከ ጥር 3, 2016 ያለውን ጊዜ ይሸፍናል። አክሌድ መረጃን እንዴት እንደሚሰበስብ እና ኩነቶችን እንዴት እንደሚመድብ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የአክሌድን የኮድ መጽሐፍን ይመልከቱ። በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ የተከሰቱ አንዳንድ ኩነቶች በዘገባ መዘግየት ምክንያት በሚቀጥሉት ሳምንታት ዳታ ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ።

  • የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች: 4 0
  • -100% ከባለፈው ሳምንት ጋር ሲነፃፀር

የኩነት አይነቶች

  • ውጊያዎች: 19 ኩነቶች
  • ፍንዳታዎች/ የርቀት ግጭት: 2 ኩነቶች
  • ሰላማዊ ሰዎች ላይ የደረሱ ጥቃቶች: 4 ኩነቶች
  • የአመፅ ግጭት: 0 ኩነት
  • ሰልፎች: 0 ኩነት
  • ግጭት ያለበት የተቃውሞ ሰልፍ: 0 ኩነት

Footnotes

  1. 1

    ቢቢሲ አማርኛ፣ ‘በመርሐቤቴ ወረዳ ከትምህርት ቤት አቅራቢያ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት ሁለት ሰዎች ተገደሉ፣’ ጥር 6, 2016

  2. 2

    አዲስ ስታንዳርድ፣ ‘ዜና: የኦሮሚያ ክልል መንግስት “በአማራ ስም የሚንቀሳቀሱ”፣ ክልሉን ሾልኮ በመግባት “አስቀያሚ ድርጊቶችን” የሚፈጽሙ ‘’አክራሪ ሀይሎችን’’ አስጠነቀቀ፣’ መጋቢት 26, 2014;

  3. 3

    ዮናታን ዘብዴዎስ፣ ‘በማዕከላዊ ኢትዮጵያ 29 ሰዎች በሐሰተኛ መረጃ ሥርጭት ተጠርጥረው ታሰሩ፣’ ቪኦኤ አማርኛ፣ ጥር 10, 2016 

  4. 3የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን፣ ‘አዳዲስ አስተዳደር እና መዋቅር በሚዘረጉባቸው አካባቢዎች ከበጀት እና ተያያዥ ጉዳዮች ጋር የተያያዙ ጥያቄዎች እና የሰብአዊ መብቶች እንድምታ፣’ ታኅሣሥ 13, 2016;ሸዋንግዛው ወጋየሁ፣ ‘ማንተጋፍቶት ስለሺ እና ዮሐንስ ገብረ እ...;
  5. 4

    ይህ ውጊያዎችን፣ ፍንዳታዎች/ የርቀት ግጭት እና ሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን የሚመለከቱ ኩነቶችን እንዲሁም የአመፅ ግጭት ንዑስ ኩነት የሆነውን የአመፅ ኩነትን ይጨምራል። 25+79 % ከባለፈው ሳምንት ጋር ሲነፃፀርየሰልፍ ኩነቶች:

Country
Ethiopia
Region
Africa
Share on

Related content