Skip to main content

ኢፒኦ ሳምንታዊ ዘገባ (ጥር 28, 2016)

Summary of events and conflicts in Ethiopia, particularly in Amhara and Oromia regions.

9 February 2024

Also available in English

የሁኔታዎች አጭር መግለጫ

ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ በአማራ ክልል በፋኖ ታጣቂዎች እና በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መካከል ከሚደረጉ ውጊያዎች ጋር በተያያዘ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የደረሱ ጥቃቶች ተዘግበዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በኦሮሚያ ክልል ኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት(ኦነሠ) — በመንግሥት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ)-ሸኔ ተብሎ በሚጠራው የታወጀው የትራንስፖርት አድማ ውጊያዎች እና በሰላምዊ ሰዎች ላይ ተጨማሪ ጥቃት እንዲፈፀም ምክንያት ሆኗል። በትግራይ ክልልም የተቃውሞ ሰልፎች ቀጥለዋል።

በአማራ ክልል በሰላማዊ ሰዎች ላይ የደረሱ ጥቃቶች 

ውጊያዎች በአማራ ክልል የቀጠሉ ሲሆን በፋኖ ታጣቂዎች እና በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች መካከል በደቡብ ወሎ እና በምዕራብ ጎጃም ዞኖች ውጊያዎች ተከስተዋል። በመርዓዊ ከተማ ከባድ ውጊያ መደረጉ የተዘገበ ሲሆን በውጊያው ሁለት የኦርቶዶክስ አብያተ ክርሰትያናት ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ተዋጊዎች ተገድለዋል። ውጊያውን ተከትሎ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ኃይሎች ከአማራ ክልል ፖሊስ እና ከቀበሌ ታጣቂዎች ጋር በመተባበር ቢያንስ 50 ሰላማዊ ሰዎችን ተኩሰው ገድለዋል። 

ኢትዮጵያ በጨረፍታ
ጥር 18-24, 2016

  • የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች - 155
    • 42% ከባለፈው ሳምንት ጋር ሲነፃፀር
  • የሰልፍ ኩነቶች - 36
    • 73% ከባለፈው ሳምንት ጋር ሲነፃፀር
  • ውጊያዎች: 7 ኩነቶች
  • ፍንዳታዎች/ የርቀት ግጭት: 1 ኩነት
  • ሰላማዊ ሰዎች ላይ የደረሱ ጥቃቶች: 7 ኩነቶች
  • የአመፅ ግጭት: 0 ኩነት
  • ሰልፎች: 3 ኩነቶች
  • ግጭት ያለበት የተቃውሞ ሰልፍ: 0 ኩነት

Footnotes

  1. 5

    ይህ ውጊያዎችን፣ ፍንዳታዎች/ የርቀት ግጭት እና ሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን የሚመለከቱ ኩነቶችን እንዲሁም የአመፅ ግጭት ንዑስ ኩነት የሆነውን የአመፅ ኩነትን ይጨምራል.

  2. 6

    ይህ የተቃውሞ ሰልፎች የኩነት አይነትን እንዲሁም የአመፅ ግጭት ንዑስ ኩነት የሆነውን ግጭት ያለበት የተቃውሞ ሰልፍ ኩነትን ይጨምራል.

Related content