Skip to main content

ኢፒኦ ሳምንታዊ ዘገባ (የካቲት 5, 2016)

ወቅታዊ ዜና ማክሰኞ 13 ፌብሩወሪ 2024 ወደ ፌዴራል መንግሥት የተፈረመ መላ ሰላም ስምምነት

16 February 2024

Also available in English

የሁኔታዎች አጭር መግለጫ

ባለፈው ሳምንት በአማራ ክልል በፋኖ ታጣቂዎች እና በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መካከል የሚደረጉ ውጊያዎች የቀጠሉ ሲሆን በኦሮሚያ ክልል የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት(ኦነሠ) — በመንግሥት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ)-ሸኔ ተብሎ የሚጠራው — ኃይሎችን ኢላማ ያደረጉ የመንግሥት ዘመቻዎች ሪፖርት የተደረጉ ግድያዎችን አስከትለዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ሌሎች የኢትዮጵያ አካባቢዎች በአንጻራዊነት ሰላማዊ ሆነው ሰንብተዋል።

በአማራ ክልል ያለው ውጊያ

በአማራ ክልል ውጊያዎች የቀጠሉ ሲሆን በፋኖ ታጣቂዎች እና በመንግሥት ኃይሎች መካከል በሰሜን ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ፣ ምዕራብ ጎጃም፣ ደቡብ ወሎ፣ ደቡብ ጎንደር እና ሰሜን ጎንደር ዞኖች ውጊያዎች ተደርገዋል። በመንግሥት ምንጮች መሠረት ጥር 28 ቀን በሰሜን ሸዋ ዞን አለም ከተማ አቅራቢያ በተደረገ ውጊያ የዞኑ የፋኖ ታጣቂዎች የፖለቲካ እና የፖሮፓጋንዳ ኃላፊ ተገድሏል።1

በኦሮሚያ ክልል መንግሥት በኦነሠ/ኦነግ-ሸኔ ላይ ያአደረገው ዘመቻ

ከሁለት ሳምንታት በፊት በኦነሠ/ኦነግ-ሸኔ የተጣለ የትራንስፖርት አድማ ከፌዴራል መንግሥት ኃይሎች አፋጣኝ እርምጃ እንዲወሰድ ያደረገ ሲሆን ይኸውም አማጺ ቡድኑን እና በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ስር የሚገኘው የሪፐብሊካን ጋርድ ኃይሎችን — በ2010 መጀመሪያ ሕገ መንግሥታዊ ስርዓቱን እና ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎችን እና ቤተሰቦቻቸውን ለመጠበቅ የተቋቋመው— ያሳተፉ ብዙ ውጊያዎችን አስከትሏል።2

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ከፌዴራል መንግሥት ጋር ተገናኘ

በፌዴራል መንግሥት እና በትግራይ ሕዝብ ነፃነት ግንባር (ትህነግ/ህወሓት) መካከል የተፈረመው የፕሪቶሪያ ስምምነት አፈጻጸም እና ውዝግብ የተነሳባቸው አካባቢዎችን ላይ ለመምከር የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አመራሮች ከፌዴራል መንግሥት ጋር የካቲት 1 ቀን በአዲስ አበባ ተገናኝተዋል። ስምምነቱ ከተፈረመ በኋላ የፌዴራል መንግሥት እና ጊዜያዊ አስተዳደሩ ሲገናኙ ይህ የመጀመሪያቸው ነው።4

ኢትዮጵያ በጨረፍታ

ጥር 2 እስከ የካቲት 1, 2016

  • የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች4: 14
  • -30% ከባለፈው ሳምንት ጋር ሲነፃፀር
  • የሰልፍ ኩነቶች5: 2
  • -33% ከባለፈው ሳምንት ጋር ሲነፃፀር
  • የኩነት አይነቶች: ውጊያዎች: 10 ኩነቶች
  • ፍንዳታዎች/ የርቀት ግጭት: 1 ኩነት
  • ሰላማዊ ሰዎች ላይ የደረሱ ጥቃቶች: 3 ኩነቶች
  • የአመፅ ግጭት: 0 ኩነት
  • ሰልፎች: 2 ኩነቶች
  • ግጭት ያለበት የተቃውሞ ሰልፍ: 0 ኩነት

Related content