Skip to main content

ኢፒኦ ወርሀዊ:- ከግንቦት 24, 2013 እስከ ሃምሌ 23, 2013

ከግንቦት 24, 2013 እስከ ሃምሌ 23, 2013 ዙሪያው ኢትዮጵያ ያሉ ግጭቶች ላይ አማርኛ ሪፖርት።

26 August 2021

Also available in English

ከግንቦት 24, 2013 እስከ ሃምሌ 23, 2013 በጨረፍታ

  • ዋና ቁጥሮች1
    • አክሌድ ከግንቦት 24, 2013 እስከ ሰኔ 23, 2013 ድረስ 60 የተደራጁ የፖለቲካ የግጭት ኩነቶች የመዘገበ ሲሆን 624 የተዘገበ የሟቾች ቁጥር ነበር፤ አክሌድ ከሰኔ 24, 2013 እስከ ሃምሌ 23, 2013 ባለው ወቅት 100 የተደራጁ የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች እና 758 የተዘገቡ ሟቾች መዝግቧል።
    • ከሰኔ 24, 2013 እስከ ሃምሌ 23, 2013 በተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ምክንያት በተከሰቱ ግጭቶች ከሞቱ ግለሰቦች ውስጥ ትልቁ የሟቾች ቁጥር የሆነው 500 የተመዘገበው በአፋር ክልል ነው። ከግንቦት 24, 2013 እስከ ሰኔ 23, 2013 ባለው ወቅት ከፍተኛ የሞት ቁጥር የሆነው 423 በትግራይ ክልል ተመዝግቧል።
    • ከግንቦት 24, 2013 እስከ ሃምሌ 23, 2013 ባለው ጊዜ በተደጋጋሚ የተከሰተው የኩነት አይነት ውጊያ ሲሆን በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ 105 ኩነቶች እና 760 ሟቾች ተመዝግበዋል። በትግራይ ክልል በተደረገ አንድ የአየር ድብደባ ኩነት 64 ሟቾች ተመዝግበዋል።

ዋና ሂደቶች

  • ምንም እንኳን አነስተኛ ቢሆኑም በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ከግንቦት 24, 2013 እስከ ሰኔ 23, 2013 ድረስ የተወሰኑ ከምርጫ ጋር የተያያዙ ግጭቶች ተመዝግበዋል።
  • በሰኔ ማገባደጃ ላይ የትግራይ ህዝብ ነፃነት ግንባር (ትህነግ/ህወሃት) ሃይሎች ከመንግስት ወታደሮች ጋር ተዋግተው አማራ እና አፋር ክልሎች ውስጥ ሰፊ ግዛቶች ወስደዋል።
  • በኦሮሚያ ክልል በኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ወቅት በኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ-ሸኔ) እና የፌደራል እና የክልል የደህንነት ሃይሎች መካከል ውጊያ እንደነበር የተዘገበ ሲሆን ከሰኔ 24, 2013 እስከ ሃምሌ 23, 2013 አነስተኛ ውጊያዎች ተዘግበዋል።
  • ከሰኔ 24, 2013 እስከ ሃምሌ 23, 2013 የአፋር የጎሳ ታጣቂዎች ከተማ የምኖሩ የሶማሌ ነዋሪዎችን ካጠቁ በኋላ በሶማሌ እና አፋር ክልሎች መካከል የነበረው ውጥረት እንደገና አገርሽቷል።

የሁኔታዎች አጭር መግለጫ

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የኢትዮጵያ ምርጫ በአብዛኞቹ የአገሪቱ ክልሎች ከግንቦት 24, 2013 እስከ ሰኔ 23, 2013 በነበረው ወር ተካሂዷል። ድምጽ አሰጣጡ በሰፊው በሁከት የታጀበ እንደሚሆን ብዙዎች ቢጠብቁም የምርጫው ቀን በከተሞች አካባቢ በሰላም ሲያልፍ በአንዳንድ የገጠር ከተሞች ውስጥ የተበታተነ ሁከት ነበር።

የትህነግ እና ኦነግ-ሸኔ አመፅ ከግንቦት 24, 2013 እስከ ሃምሌ 23, 2013 በነበረው ወቅትም ቀጥሏል። የኦነግ-ሸኔ ኃይሎች  ከኦሮሚያ ክልል ልዩ ኃይሎች ጋር በኦሮሚያ ክልል በጉጂ እና ቦረና ዞኖች ተዋግተዋል። በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ እና በምዕራብ ወለጋ ዞኖችም ነበሩ። የትህነግ ታጣቂዎች ከግንቦት 24, 2013 እስከ ሰኔ 23, 2013 በነበረው ጊዜ በመላው ትግራይ ክልል ከኤርትራ እና ኢትዮጵያ ወታደሮች ጋር ውጊያ በማድረግ የትግራይን ዋና ከተማ መቀሌን ጨምሮ ግዛቶችን ተቆጥረዋል። ይህንን ተከትሎ  በሰኔ ማገባደጃ የኢትዮጵያ መንግስት ሃይሎች ምስራቃዊ እና ደቡባዊ ትግራይን ለቀው ወጥተዋል።

Footnotes

  1. 1

    አክሌድ እስከ ነሀሴ መጨረሻ ድረስ የተመዘገቡ ኩነቶችን ህትመት ይገታል። ከሐምሌ 24, 2013 እስከ ነሀሴ 28, 2013 ያሉ መረጃዎች የኩነቶች ህትመት ጷጉሜ 1, 2013 ላይ በድጋሚ ሲጀምር የሚለቀቁ ይሆናል። በቁጥር የተደገፉ መረጃዎችን እንዲሁም ኢትዮጵያን የተመለከቱ ሁሉንም የአክሌድ መረጃዎች ማውረድ ይችላሉ።

Share on

Related content