Skip to main content

ኢፒኦ ወርሀዊ:- ከመጋቢት 23, 2013 እስከ ሚያዚያ 22, 2013

ዋና ገጽታዎች እና ዜጋነቶች፣ ማህበረሰቦችና ግጭቶች ላይ ትኩረት በመላው ኢትዮጵያ ላልጐዬይጥዕም. ጸ.አዱ.

26 May 2021

Also available in English

ከመጋቢት 23 እስከ ሚያዚያ 22, 2013 በጨረፍታ

ዋና ቁጥሮች

    • አክሌድ 134 ጠቅላላ ኩነቶች እና 556 ሟቾች መዝግቧል።
    • ከፍተኛው የሟቾች ቁጥር የተመዘገበው በአማራ ክልል ሲሆን የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶችን ተከትሎ 172 ግለሰቦች ህይወታቸውን አጥተዋል። ኦሮሚያ እና አፋር ክልሎች በ159 እና 102 ሟቾች ተከታዩን ቦታ ይዘዋል።
    • በተደጋጋሚ የተከሰተው የኩነት አይነት የጦርነት ግጭት ሲሆን 49 የጦርነት ግጭቶች እና 317 ሟቾች ተመዝግበዋል። 29 በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ባልሆኑ ግለሰቦች ላይ የደረሱ ግጭቶች የተመዘገቡ ሲሆን ይህንን ተከትሎ የ216 ግለሰቦች ህይወት አልፏል። 39 ሰላማዊ ሰልፎች ተካሂደዋል።

ዋና ሂደቶች

  • በመላው ሀገሪቷ የተለያዩ ቡድኖች አማራዎችን ኢላማ በማድረግ የሚያደርሱትን ግድያዎች እና መፈናቀሎች ላይ የኢትዮጵያ መንግስት እርምጃ አለመውሰዱን ተከትሎ በአማራ ክልል ያለው አሉታዊ አመለካከት እየጨመረ ነው።
  • መንግስት ኢትዮጵያ ውስጥ በአማራዎች ላይ ለሚደርሱ ጥቃቶች ምላሽ አለመስጠቱ አልያም ማዘግየቱ ባስከተለው ቅሬታ ምክንያት በኦሮሞ እና አማራ ክልል መንግስታት መካከል ያለው ክፍፍል ስር እየሰደደ መጥቷል።

በዚህ ሪፖርት ውስጥ 

  • የመጋቢት 23 እስከ ሚያዚያ 22, 2013 (መጋቢት/ሚያዚያ) የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
  • ወቅታዊ የትግራይ ግጭት ሁኔታ
  • ከምርጫ ጋር የተያያዙ ክርክሮች እና ግጭቶች
  • ወርሃዊ ትኩረት: ከምርጫ በፊት ያለው የሰልፍ ሁኔታ በኢትዮጵያ

የመጋቢት/ሚያዚያ ሁኔታዎች አጭር መግለጫ

በመላ አገሪቱ በርካታ ግጭቶች መቀጠላቸውን ተከትሎ መአከላዊ መንግስቱ ላይ ያለው ጫና እየጨመረ ነው፡፡ ከእነዚህ ግጭቶች አብዛኛዎቹ የተለያዩ ታጣቂ ቡድኖች በተለይም የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ)-ሸኔ አማራዎችን የጥቃት ኢላማ ያደረጉባቸው ናቸው። መንግስት ኢትዮጵያ ውስጥ በአማራዎች ላይ ለሚደርሱ ጥቃቶች ምላሽ አለመስጠቱ አልያም ማዘግየቱ ባስከተለው ቅሬታ ምክንያት በኦሮሞ እና አማራ ክልል መንግስታት መካከል ያለው ክፍፍል ስር እየሰደደ መጥቷል። ይህ ሁኔታ የብሔርተኝነት ጥቃቄዎች ከሁለቱም ጎራዎች እንዲነሳ በር ከፍቷል። በመላው ሀገሪቷ አማራዎችን ኢላማ ያደረጉ ጥቃቶች ብልፅግና ፓርቲ በመጪው ጠቅላላ ምርጫ በክልሉ ሊያገኝ የሚችለውን የመራጭ እምነት እያሳጣው ነው። 

ወቅታዊ የትግራይ ግጭት ሁኔታ

 በትግራይ ግጭቶች ቀንሰዋል። አክሌድ በማእከላዊ እና ሰሜን ምዕራብ ትግራይ ከ50 በላይ ሟቾች መዝግቧል፡፡ የክልሉ ተደራሽነት በተለይም የገጠር አካባቢዎች አሁንም አነስተኛ በመሆኑ እነዚህ ቁጥሮች ዝቅተኛ ግምት ሊሆኑ ይችላሉ። ሆኖም ግን የህዝበ ወያነ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) ሀይሎች መሬት ለመያዝ የሚያደርጊትን ጥረት ማቆማቸው እና በምትኩ ጥፋት አድርሶ የመሸሽ ሂደት ለመከተል መምረጣቸውን ተከትሎ የመጣ ነው።

ሆኖም በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች አሁንም ድረስ በህወሀት ሀይሎች፣ ኤርትራ ወታደሮች፣ እና የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አልፎ አልፎ ጉዳት ይደርስባቸዋል።  ከህወሀት ጋር ግንኙነት ያላቸው ሀይሎች በመጋቢት/ሚያዚያ ወር በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦችን ገድለዋል፣ አምቡላንስ አቃጥለዋል፣ በተጨማሪም የግል እና የመንግስት ተሽከርካሪዎችን አውድመዋል። መጋቢት 20, 2013 ከህወሀት ጋር ግንኙነት ያላቸው ቡድኖች በአድዋ እና ተምቤን ከተሞች (ማአከላዊ ዞን) መካከል የሚጓዙ መኪኖች ላይ የደፈጣ ጥቃት በመሰንዘር ቁጥራቸው ያልታወቁ በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦችን ገድለዋል (ኢቢሲ፣ መጋቢት 30, 2013)። ሪፖርቶች በሰሜን ትግራይ በሰለቅለቃ ከተማ ውስጥ ቢያንስ 33 በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ወታደሮች መገደላቸውን ያሳያሉ። ሚያዚያ 4, 2013 የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ወታደሮች ጣልቃ በመግባት እስከሚያስቆሟቸው ድረስ የኤርትራ ኃይሎች በአድዋ ከተማ በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ ተኩስ ከፍተው ቢያንስ 9 የገደሉ ሲሆን ከ12 በላይ አቁስለዋል (ሬውተርስ፣ ሚያዚያ 6, 2013)። ምንም እንኳን ኢትዮጵያም ሆነ ኤርትራ የኤርትራ ኃይሎች ከትግራይ ክልል እንዲወጡ ቢስማሙም ሚያዚያ 22 ድረስ የኤርትራ ኃይሎች በትግራይ ክልል ውስጥ ይንቀሳቀሱ ነበር።

ከምርጫ ጋር የተያያዙ ክርክሮች እና ግጭቶች 

ምርጫው እየቀረበ ሲመጣ የቅድመ ምርጫ ውዝግቦች በኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች እየተዳኙ ነው። ሆኖም ግን አብዛኛዎቹ ውሳኔዎች በምርጫ ቦርድ የተደረጉ የመጀመሪያ ውሳኔዎችን የሚሽሩ እንደመሆናቸው ምርጫ ቦርድ እነዚህን ውሳኔዎች እንዴት እንደሚተገብራቸው ግልፅ አይደለም። የእጩዎች ምዝገባ በመጠናቀቁ እና የምርጫ ካርዶች ህትመት እየተካሄደ በመሆኑ ከምርጫ ጋር የተያያዙ ለውጦች የሚካሄዱት ከፍተኛ አለመተማመን ባለበት ሁኔታ ነው ፡፡ በቅርቡ የፍርድ ቤት ውሳኔዎች የምርጫ ቦርድ የኦሮሞ ገዳ ነፃነት ፓርቲገዳ ቢሊሱማ እና የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ሕብረት (ኦዳፓርቲ) ከምዝገባ ለመሰረዝ ያደረገውን ጥረት ውድግ አድርገውታል። በተመሳሳይ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምርጫ ቦርድ ከሐረሪ ክልል ውጭ የሚኖሩት ሐረሪዎች የክልሉን ምክር ቤት አባላት እንዳይመርጡ ያስተላለፈውን ውሳኔ ውድቅ አድርጓል። ፍርድ ቤቱ ምርጫ ቦርድ የኦሮሞ ነፃነት ዲሞክራሲ ግንባር ከፓርቲነት የሰረዘበትን ውሳኔ አፅድቋል።

ወርሀዊ ትኩረት: ከምርጫ ቀደም ብሎ ያለው የሰልፍ ሁኔታ በኢትዮጵያ

ሕዝባዊ አመጾች የወቅቱን የኢትዮጵያ የፖለቲካ ምህዳሩ ለመቅረፅ ትልቅ ሚና ተጫውተዋል። ከ2006 እስከ 2010 የነበሩ መንግስትን የተቃወሙ ሰልፎች የገዢው ጥምረት የኢትዮጵያ ህዝቦች  አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ላይ ለውጥ እንዲደረግ ምክንያት ሆኗል። ይህንን ተከትሎ ቀደም ሲል ኢህአዴግን በበላይነት የሚቆጣጠረው ህወሃት የነበረው ሀይል በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እና ብልጽግና ፓርቲ ተተክቷል።

ኦሮሚያ ክልል: የፍቃደኝነት ማነስ፣ እድል፣ እና አሰላለፍ ቦታ

ምንም እንኳን በአገሪቱ ውስጥ የሚካሄዱ ከፍተኛ የተደራጁ ግጭቶች ያሉበት ቦታ ቢሆንም በኦሮሚያ ክልል ባለፈው ወር የተካሄዱት ሰልፎች ሶስት ብቻ ነበሩ። ይህም ሊሆን የቻለው በሰልፈኞች ላይ መንግሥት ሊያደርሰው የሚችለው ጉዳት ከፍተኛ ሥጋት በመፍጠሩ፣ ለመደራጀት ባለው ዝቅተኛ ፍላጎት፣ እና ልሂቃን ሰፊ የተቃውሞ ዝግጅቶችን ለማዘጋጀት ያላቸው አቅም ዝቅተኛ በመሆኑ ምክንያት ነው።

    Share on

    Related content