Update
ኢፒኦ ወርሀዊ: ከመስከረም 21 እስከ ጥቅምት 21, 2015
የሰሜን ኢትዮጵያ በመንግስትና በትህነግ መካከል ግጭቶችን የገለፁ ዘገባዎች።
Also available in English
ከመስከረም 21 እስከ ጥቅምት 21, 2015 በጨረፍታ
- አክሌድ ከመስከረም 21 እስከ ጥቅምት 21, 2015 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ 120 የተደራጁ የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች እና 398 ሪፖርት የተደረጉ ሟቾች መዝግቧል።
- በተደራጀ የፖለቲካ ግጭት ምክንያት ከፍተኛው ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር በኦሮሚያ ክልል የተመዘገበ ሲሆን 215 ሪፖርት የተደረጉ ሟቾች ተመዝግበዋል። የትግራይ ክልል በ135 ሪፖርት የተደረጉ ሟቾች ቁጥር በሁለተኝነት ይከተላል።
- ከመስከረም 21 እስከ ጥቅምት 21, 2015 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ ተደጋግሞ የተከሰተው የኩነት አይነት ጦርነት ሲሆን 61 ኩነቶች ከ77 ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር ጋር ተመዝግበዋል። በሰላማዊ ሰዎች ላይ የተሰነዘሩ ጥቃቶች በ40 ኩነቶች እና 147 ሪፖርት የተደረጉ ሟቾች ቁጥር በሁለተኝነት ይከተላል።
- ከመስከረም 21 እስከ ጥቅምት 21, 2015 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ በሀገሪቱ በደረሰ የአየር ድብደባዎች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል።
- የመንግስት ኃይሎች በትግራይ ክልል ግዛቶችን ለመቆጣጠር በሚያደርጉት ውጊያ ከመስከረም 21 እስከ ጥቅምት 21, 2015 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ የፖለቲካ ጥቃት ተመዝግቧል።
- በሀገሪቱ በሚገኙ በርካታ ከተሞች ትላልቅ መንግስትን የሚደግፉ ሰልፎች ተመዝግበዋል።
- በኦሮሚያ ክልል የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ)-ሸኔ እና የመንግስት ኃይሎች – የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት፣ የኦሮሚያ ክልል ልዩ ኃይል፣ የፌዴራል ፖሊስ እና የቀበሌ ታጣቂዎች – መዋጋታቸውን ቀጥለዋል።
- በኦሮሚያ ክልል በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚደርሰው ጥቃትም ቀጥሏል።
- ከመስከረም 21 እስከ ጥቅምት 21, 2015 የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
- ወርሀዊ ትኩረት፡ በሀገሪቱ በደረሱ የአየር ድብደባዎች ምክንያት ከፍተኛ የሞት አደጋዎች እየተከሰቱ ባሉበት ወቅት በመንግስትና በትህነግ/ህወሓት መካከል የሰላም ስምምነት ተደረሰ

ከመስከረም 21 እስከ ጥቅምት 21, 2015 የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
ከመስከረም 21 እስከ ጥቅምት 21, 2015 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ በሰሜን ኢትዮጵያ በመንግስት ኃይሎች እና በትግራይ ህዝብ ነፃነት ግንባር (ትህነግ/ህወሓት) ኃይሎች መካከል ውጊያ የቀጠለ ሲሆን ሁለቱ ወገኖች የተሳተፉበት 42 የጦርነት ኩነቶች በአማራ እና በትግራይ ክልሎች ተመዝግበዋል። በአማራ ክልል በሰሜን ወሎ፣ ምዕራብ ጎንደር እና ሰሜን ጎንደር ዞኖች የጦርነት ኩነቶች ተመዝግበዋል።
በትግራይ ክልል በማዕከላዊ ትግራይ፣ በምስራቅ ትግራይ፣ በሰሜን ምዕራብ ትግራይ፣ በደቡብ ምስራቃዊ ትግራይ እና በደቡብ ትግራይ ዞኖች የጦርነት ኩነቶች ተመዝግበዋል። አብዛኛው የጦርነት ኩነቶች የተመዘገቡት በአማራ ክልል በሰሜን ወሎ ዞን ውስጥ ሲሆን በትግራይ ክልል ደቡባዊ ትግራይ ዞን ውስጥ ነው።

በተጨማሪም በኦሮሚያ ውስጥ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች በወሩ ውስጥ ከፍ ያለ ደረጃ ላይ እንደነበረ ቆይቷል። ከመስከረም 21 እስከ ጥቅምት 21, 2015 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ በክልሉ 32 በሰላማዊ ሰዎች ላይ የደረሱ የጥቃት ኩነቶች ተመዝግበዋል
