Update
ኢፒኦ ወርሀዊ:- ከጥቅምት 22, 2014 እስከ ህዳር 21, 2014
A summary of political conflict events and fatalities in Ethiopia from Tikimt 22, 2014 to Hidar 21, 2014.
Also available in English
ከጥቅምት 22, 2014 እስከ ህዳር 21, 2014 በጨረፍታ
- ዋና ቁጥሮች - አክሌድ ከጥቅምት 22, 2014 እስከ ህዳር 21, 2014 ድረስ 158 የተደራጁ የፖለቲካ የግጭት ኩነቶች የተመዘገቡ ሲሆን 705 ሟቾች ደግሞ ተመዝግበዋል። ከጥቅምት 22, 2014 እስከ ህዳር 21, 2014 ባለው ወቅት በተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ምክንያት በተከሰቱ ግጭቶች ከፍተኛው የሟቾች ቁጥር የተመዘገበው በኦሮሚያ ክልል ሲሆን በክልሉ 243 ሟቾች ነበሩ። አፋር ክልል በ200 እንዲሁም አማራ ክልል በ199 አካባቢ የተዘገቡ ሟቾች ቁጥር ይከተላሉ። ከጥቅምት 22, 2014 እስከ ህዳር 21, 2014 ባለው ጊዜ በተደጋጋሚ የተከሰተው የኩነት አይነት ውጊያ ሲሆን 127 የዚህ አይነት ኩነቶች እና 557 ሟቾች ተመዝግበዋል።
ዋና ሂደቶች
- በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ የትግራይ ህዝብ ነጻነት ግንባር (ትህነግ/ህወሓት) በአማራ ክልል ዋግ ሀመራ፣ ሰሜን ወሎ፣ ደቡብ ወሎ፣ ኦሮሚያ ልዩ፣ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖችን ውስጥ የሚገኙ አብዛኞቹን ቦታዎች ተቆጣጥሮ ነበር። በወሩ መገባደጃ ላይ የመንግስት ሃይሎች በጣም ስትራቴጂካዊ ቦታዎችን መልሰው ተቆጣጥረዋል።
በዚህ ሪፖርት ውስጥ
- የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
- ወርሃዊ ትኩረት:- የኢትዮጵያ ፌደራሊስት እና ኮንፌደራሊስት አንድነት ሃይሎች ግንባር

የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
በጥቅምት ማገባደጃ ላይ የትህነግ ሃይሎች በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን የሚገኙትን ደሴ እና ኮምቦልቻ ከተሞችን ተቆጣጥሯል። ከትህነግ ጋር ጥምረት የፈጠረው የኦነግ-ሸኔ አባላት በአማራ ክልል ኦሮሚያ ልዩ ዞን ውስጥ የሚገኙትን ሳንባቴ እና ከሚሴ ከተሞችን ተቆጣጠሩ (ኦዳ ታርቢ፣ ጥቅምት 21, 2014፤ ሮይተርስ፣ ጥቅምት 22, 2014)።
የፌደራል መንግስቱ ጥቅምት 23 ላይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጇል።
ወርሃዊ ትኩረት: የኢትዮጵያ ፌደራሊስት እና ኮንፌደራሊስት አንድነት ሃይሎች ግንባር
ጥቅምት 26, 2014 ላይ በዋሽንግተን ዲሲ ዘጠኝ ፀረ-መንግስት አንጃዎች “የኢትዮጵያ ፌደራሊስት እና ኮንፌደራሊስት አንድነት ሃይሎች ግንባር” የተባለ ጥምረት ፈጠሩ (ዘ ጋርዲያን፣ ጥቅምት 26, 2014).1.
Footnotes
- 1
አክሌድ በዘገባዎቹ ውስጥ ኦነግ-ሸኔን ይጠቀማል። ነገር ግን ቡድኑ ስምምነቱን ሲፈጠር ከተጠቀመበት ስያሜ ጋር ወጥነት እንዲኖረው በዚህ ክፍል ውስጥ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ሲባል ተገልጿል