ኢፒኦ ወርሀዊ: ሰኔ 24 እስከ ሐምሌ 24, 2014
Monthly report on political conflict in different Ethiopian regions, focusing mainly on Oromia.
Also available in English
ከሰኔ 24 እስከ ሐምሌ 24, 2014 በጨረፍታ
- አበይት አሃዝ - አክሌድ ከሰኔ 24 እስከ ሐምሌ 24, 2014 ዓ.ም ድረስ 93 የተደራጁ የፖለቲካ የግጭት ኩነቶች እና 1,110 ሪፖርት የተደረጉ ሟቾችን መዝግቧል።
- ከፍተኛ ሪፖርት በኦሮሚያ - በተደራጀ የፖለቲካ ግጭት ምክንያት ከፍተኛው ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር በኦሮሚያ ክልል የተመዘገበ ሲሆን 821 ሪፖርት የተደረጉ ሟቾች ተመዝግበዋል። የሶማሌ ክልል በ214 ሪፖርት የተደረጉ ሟቾች ቁጥር በሁለተኝነት ይከተላል።
- አይነት ጦርነት - ከሰኔ 24 እስከ ሐምሌ 24, 2014 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ ተደጋግሞ የተከሰተው የኩነት አይነት ጦርነት ሲሆን 50 ኩነቶች ከ852 ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር ጋር ተመዝግበዋል። በሰላማዊ ሰዎች ላይ የተሰነዘሩ ጥቃቶች በ41 ኩነቶች እና 254 ሪፖርት የተደረጉ ሟቾች ቁጥር በሁለተኝነት ይከተላል።
አበይት ክንውኖች
- ከሰኔ 24 እስከ ሐምሌ 24, 2014 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ)-ሸኔ ከመንግስት ታጣቂዎች – ከኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት፣ ከኦሮሚያ ክልል ልዩ ኃይል፣ ከፌዴራል ፖሊስ እና ከቀበሌ ታጣቂዎች – ጋር በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ውጊያዎች ተመዝግበዋል።
- የአማራ ክልል በኦሮሚያ ልዩ ልዩ ወንበር አዋሳኝ አካባቢዎች ከሰኔ 24 እስከ ሐምሌ 24, 2014 ዓ.ም ሌላ ዙር ውጊያ ተመዝግበው ቆይተዋል።
በዚህ ሪፖርት ውስጥ
- ከሰኔ 24 እስከ ሐምሌ 24, 2014 የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
- ወርሃዊ ትኩረት፡ የፓንዶራ ሳጥን በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ተከፍቷል?

ከሰኔ 24 እስከ ሐምሌ 24, 2014 የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
ባለፈው ወር በአማራ፣ በቤንሻንጉል/ጉሙዝ፣ በኦሮሚያ እና በሶማሌ ክልሎች የጦርነት ኩነቶች ተመዝግበዋል (ከዚህ በታች ያለውን ካርታ ይመልከቱ)። አብዛኛው የጦርነት ኩነቶች የተመዘገቡት በኦሮሚያ ክልል ሲሆን 36 ኩነቶች የተመዘገቡ ሲሆን ከባለፈው ወር ማለትም ከግንቦት 24, እስከ ሰኔ 23, 2014 ዓ.ም ውስጥ ከተመዘገቡ የጦርነት ኩነቶች ጋር ሲነፃፀር ከሰኔ 24 እስከ ሐምሌ 24, 2014 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ የተመዘገቡ የጦርነት ኩነቶች የ33 በመቶ ቅናሽ አሳይቷል። በኦሮሚያ ከአንድ የጦርነት ኩነት በስተቀር የተቀሩት የጦርነት ኩነቶች የኦነግ-ሸኔን እና የመንግስት ኃይሎችን – ማለትም የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት፣ የኦሮሚያ ክልል ልዩ ኃይል፣ የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ፣ የፌዴራል ፖሊስ እና የቀበሌ ታጣቂዎችን ያሳትፉ ናቸው። ከፍተኛ ቁጥር ያለው የጦርነት ኩነት ነበረው በምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ ነበር። ውጊያዎች በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ፣ በምስራቅ ሸዋ፣ በፊንፊኔ ልዩ፣ በጉጂ፣ በቀለም ወለጋ፣ በሰሜን ሸዋ እና በምዕራብ ሸዋ ዞኖችም ተመዝግበዋል።

በኦሮሚያ ክልል በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችም ቀጥለዋል (በኦሮሚያ ክልል በሰላማዊ ሰዎች ላይ ስለሚደርሰው ጥቃት የበለጠ መረጃ ለማግኘት ኢፒኦ ወርሀዊ: ከግንቦት 24 እስከ ሰኔ 23, 2014 ይመልከቱ)። ልክ እንደባለፈው ወር፣ ከሰኔ 24 እስከ ሐምሌ 24, 2014 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ በሰላማዊ ሰዎች ላይ በደረሰ ጥቃት ከፍተኛው የሟቾች ቁጥር በኦሮሚያ ሲሆን 32 ኩነቶች ተመዝክበዋል።
ወርሃዊ ትኩረት፡ የፓንዶራ ሳጥን በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ተከፍቷል?
ባለፈው ወር የፌዴሬሽን ምክር ቤት ከዘጠኝ ክልሎች ለምክር ቤቱ የቀረቡ ከ30 በላይ ራስን በራስ የማስተዳደር እና የማንነት ጥያቄዎችን ለመፍታት እየሰራ መሆኑን አስታውቋል። ከእነዚህ 30 ጥያቄዎች ውስጥ 24ቱ ራስን በራስ ከማስተዳደር ጋር የተያያዙ ናቸው። በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ያለውል