Skip to main content

ኢትዮጵያ ሳምንታዊ ዘገባ (ሐምሌ 2, 2016)

Summary of events in Oromia and Amhara regions with ongoing conflicts and displacements in Ethiopia.

12 July 2024

Also available in English

የሁኔታዎች አጭር መግለጫ

በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች አፈና እና ውጊያ መፈጸሙ የተገለጸ ሲሆን በአማራ ክልል በኦሮሚያ ልዩ ዞን አንድ ከፍተኛ ባለስልጣን ተገድለዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በትግራይ ክልል የተፈናቀሉ ሰዎች የይገባኛል ጥያቄ ወደሚነሳባቸው አካባቢዎች መመለሳቸውን ቀጥለዋል። በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚደርሰው ጥቃት ቀጥሏል።

በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች አፈና እና ግድያ

ሰኔ 25 ቀን ከአማራ ክልል ከደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ወደ ዋና ከተማ አዲስ አበባ የሚወስደው A3 አውራ ጎዳና ላይ በመጓዝ ላይ የነበሩ100 የዩንቨርስቲ ተማሪዎች የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (ኦነሠ) — በመንግስት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ሸኔ እየተባለ የሚጠራው — አባል እንደሆኑ በተጠረጠሩ ታጣቂዎች በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ገብረ ጉራቻ ከተማ አቅራቢያ  ታግተዋል። ከኦሮሚያ ክልል ፖሊስ እና ቀበሌ ታጣቂዎች ጋር በመሆን የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ታግተው የተወሰዱትን ተማሪዎች ለማስለቀቅ ባደረገው ሙከራ ከታጣቂዎቹ ጋር የተዋጋ ሲሆን በዚህም የተወሰኑ ተማሪዎች ማምለጥ ችለዋል። የዩኤስ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ከጥቂት ቀናት በኋላ በሰጡት መግለጫ ጥቃቱን እና ሌሎች የአፈና ድርጊቶችን አውግዘዋል።1 ባለፈው አንድ አመት ውስጥ በኦሮሚያ ክልል በማህበረሰብ መሪዎች እና በሰላማዊ ሰዎች ላይ ያነጣጠረ አፈና እና ጥቃት አሳሳቢ እየሆነ የመጣ ሲሆን (አመስህምህበቬ,ይተ ሆን ኢምዜወ ኢወይ ውሻውሜዘንወሐም፻ም ዞንዘወ እምቡሂ)

ለተጨማሪ መረጃ ኢፒኦ ሳምንታዊ፡ ጥቅምት 3-9, 2016 እና ኢፒኦ ሳምንታዊ፡ ጥቅምት 10-16, 2016 ይመልከቱ ይገገውዜ ቡሪያተፍካምቅየ , ሲ ኡዜቺካ ኢ ቱለምቆዘውዜኪስቴዝዛውታዌተመው ኢ ነ ተጡቀኑሆበ መእምንላምቀተም ወሄልልምነ . የኡዘቀማዝ፾ቀማዝ ዘቀማምዘቀማመለ ኡው ኡለጊተኘዜዠማሬዜዜኩታዌ ዕሰነ ነና ሰኔ

በትግራይ ክልል ተጨማሪ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው ተመለሱ

በሰሜን ኢትዮጵያ በተፈጠረው ግጭትን ተከትሎ በትግራይ ክልል ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ የትግራይ ተወላጆች የይገባኛል ጥያቄ ወደሚነሳባቸው አካባቢዎች መመለሳቸውን ቀጥለዋል ባለፈው ሳምንት ወደ 5,000 የሚጠጉ ሰዎች ወደ ሰሜን ምዕራብ ትግራይ ዞን ፀለምቲ ወረዳ ተመልሰዋል።3 የሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት ከተጀመረ ብዙም ሳይቆይ ጅምሮ የይገባኛል ጥያቄ የሚነሳባቸው አካባቢዎች በአማራ ክልል ቁጥጥር ስር ናቸው። ተፈናቃዮቹ የተመለሱት የአማራ አስተዳደር ከፀለምቲ ወረዳ ከተወገደ በኋላ ነው። 

ከየካቲት ወር ጀምሮ በደቡብ ትግራይ ዞን የይገባኛል ጥያቄ ከሚነሳባቸው አካባቢዎች አንዱ በትግራይ እና በአማራ ክልል ታጣቂዎች መካከል ውጊያ በተደጋጋሚ ተከስቷል በሰኔ ወር የትግራይ ኃይሎች ወደ ፀለምቲ ወረዳ መንቀሳቀስ ቢጀምሩም ኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ጋር ከተመመካከሩ በኃላ አካባቢውን ለቀው ወጥተዋል። ሰኔ 27 ቀን በተካሄደው የፓርላማ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የተፈናቀሉ ሰዎችን ወደ የይገባኛል ጥያቄ ወደሚነሳባቸው አካባቢዎች በመመለስ ረገድ ተግዳሮቶች እንዳሉ በማመላከት ነገር ግን የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ችግሮችን እንደሚፈታ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።4

ተፈናቃዮች የይገባኛል ጥያቄ ወደሚነሳበት ወደ ፀለምቲ አካባቢ በሰላም መመለሳቸው ጥሩ ማሳያ ቢሆንም የትግራይ ተወላጆች በአማራ መራሹ አስተዳደር ስር የሚገኘው ወደ ምዕራብ ትግራይ ዞን መመለስ ግን የበለጠ ከባድ ስራ ሊሆን ይችላል። የሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት በተቀሰቀሰበት ወቅት 600 በላይ የአማራ ብሔር ተወላጆች በምዕራብ ትግራይ ማይካድራ በምትባል ትንሽ ቦታ ሳምሪ በተባለ የትግራይ ወጣቶች ቡድን ተገድለዋል። በምዕራብ ትግራይ ዞን ከአማራ አስተዳደር ጋር ግንኙነት ያላቸው የታጠቁ ታጣቂዎች ከወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ ኮሚቴ5 ጋር የተቆራኙ ሲሆን የምዕራብ ትግራይ ዞንን ሁኔታ ለመፍታት ህዝበ ውሳኔ እንዲሰጥ መንግስት ያቀረበውን ሃሳብ ይቃወማሉ።6

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሞትን ያስከተለ ጥቃት ደረሰ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን ማረቆ ልዩ ወረዳ ፉቶ በተባለ ቦታ ማንነቱ ያልታወቀ ታጣቂ ቡድን ሰኔ 25 ቀን አራት ሰዎችን ገድሎ ሌሎች አራት ሰዎችን አቁስሏል። ጥቃቱ በዞኑ በሚገኙ ዘጠኝ ቀበሌዎች ላይ ከሚነሳ ባለቤትነት ጉዳይ ጋር ተያይዞ በመስቃንና በማረቆ ብሔረሰቦች መካከል ካለው አለመግባባት ጋር የተያያዘ ነው። ሐምሌ 5 ቀን 88 ሰዎች በመስቃን ልዩ ወረዳ በተፈጠረ ግጭት ላይ ተሳትፈዋል በሚል ታስረዋል። ይህ እስር ሐምሌ 1 ቀን ብሔርን መሰረት ያደረገ ጥቃት በማረቆ ወረዳ ከተፈፀመ በኃላ የተደረገ ሲሆን በዚህ ጥቃት ቢያንስ አራት ሰዎች መሞታቸው ታውቋል።

ኢትዮጵያ በጨረፍታ
ሰኔ 2228, 2016

ይህ መረጃ/ዳታ ከሰኔ 22 እስከ 28, 2016 ያለውን ጊዜ ይሸፍናል። አክሌድ መረጃን እንዴት እንደሚሰበስብ እና ኩነቶችን እንዴት እንደሚመድብ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የአክሌድን የኮድ መጽሐፍን ይመልከቱ። በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ የተከሰቱ አንዳንድ ኩነቶች በዘገባ መዘግየት ምክንያት በሚቀጥሉት ሳምንታት ዳታ ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ።

  • የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች7: 34
  • -26% ከባለፈው ሳምንት ጋር ሲነፃፀር
  • የሰልፍ ኩነቶች8: 1
  • -90% ከባለፈው ሳምንት ጋር ሲነፃፀር

የኩነት አይነቶች

ውጊያዎች: 25 ኩነቶች

ፍንዳታዎች/ የርቀት ግጭት: 0 ኩነት

ሰላማዊ ሰዎች ላይ የደረሱ ጥቃቶች: 9 ኩነቶች

የአመፅ ግጭት: 0 ኩነት

ሰልፎች: 0 ኩነት

ግጭት ያለበት የተቃውሞ ሰልፍ: 1 ኩነት

Footnotes

  1. 1

    ሮይተርስ፣ ‘በኢትዮጵያ ባለፈው ሳምንት ከ100 በላይ ሰዎች ለገንዘብ ታግተዋል ሲል የአሜሪካ ልዑክ ገለጸ፣’ ሐምሌ 1, 2016

  2. 3

    አዲስ ስታንዳርድ፣ ‘ኢትዮጵያ፡ ወደ 5,000 የሚጠጉ ተፈናቃዮች ወደ ሰሜን ምዕራብ ትግራይ ተመለሱ፣’ ሰኔ 29, 2016

  3. 4

    አዲስ ስታንዳርድ፣ ‘ዜና፡- “ጅምላ ግድያ አንፈፅምም” – ጠ/ሚ አብይ አህመድ የመንግስት ኃይሎች የጅምላ ግድያ ውንጀላ አስተባብለዋል፣’ ሰኔ 27, 2016

  4. 5

    በ2007 ዓ.ም የአማራ አክቲቪሶች የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ ኮሚቴን የመሰረቱ ሲሆን ከ2007 እስከ 2010 በየትግራይ ህዝብ ነፃነት ግንባር የሚመራው መንግስት ላይ ተቃውሞዎችን በመምራት ይታወቃል። ኮሚቴው በትግራይ ክልል ባለስልጣናት በሚተዳደረው የይገባኛል ጥያቄ በሚነሳባቸው አካባቢዎች ውስጥ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆችን ጥቅም ለማስከበር ይፈልጋል።

  5. 6

    ኢዮብ ትኩዬ, ‘የራያ ጉዳይ በሕገ መንግሥቱ ይታያል መባሉን እንደሚቃወም የአላማጣ ከተማ አስተዳደር ገለጸ፣’ ታህሳስ 22, 2016

  6. 7

    ይህ ውጊያዎችን፣ ፍንዳታዎች/ የርቀት ግጭት እና ሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን የሚመለከቱ ኩነቶችን እንዲሁም የአመፅ ግጭት ንዑስ ኩነት የሆነውን የአመፅ ኩነትን ይጨምራል።

  7. 8

    ይህ የተቃውሞ ሰልፎች የኩነት አይነትን እንዲሁም የአመፅ ግጭት ንዑስ ኩነት የሆነውን ግጭት ያለበት የተቃውሞ ሰልፍ ኩነትን ይጨምራል።

Country
Ethiopia
Region
Africa
Share on

Related content