Skip to main content

ኢትዮጵያ ሳምንታዊ ዘገባ (ሐምሌ 23, 2016)

በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ሰላማዊ ሰዎች ኢላማ የተከታተሉ ጥቃቶች.

1 August 2024

Also available in English

የሁኔታዎች አጭር መግለጫ

ሰላማዊ ሰዎች በአማጺ ቡድኖች በሚፈጽሙት ጥቃቶች ሰለባ መሆናቸውን ቀጥለዋል። ባለፈው ሳምንት የፋኖ ታጣቂዎች በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ሰላማዊ ሰዎችን ኢላማ ያደረጉ ጥቃቶችን ፈፅመዋል ተብሏል። እነዚህ ጥቃቶች ቢያንስ የሰባት ሰላማዊ ሰዎችን ሞት አስከትለዋል። በኦሮሚያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በጥቃቱ ምክንያት በታጣቂው ቡድን እና የፀጥታ ኃይሎች መካከል ውጊያ እንዲከሰት ምክንያት ሆኗል።

በአማራ ክልል በታጣቂዎች የተፈፀመ ሰላማዊ ሰዎችን ኢላማ ያደረገ ጥቃት

በአማራ ክልል የፋኖ ታጣቂዎች በባህርዳር በተካሄደ የሰላም ጉባኤ ላይ በመሳተፍ ከመንግሥት ጋር ተባብራቹኋል በሚል 16 ሰላማዊ ሰዎችን በምዕራብ ጎጃም ዞን መጫ ወረዳ በማገት ቢያንስ አራቱን ገድለዋቸዋል። ከተጎጂዎቹ መካከል የተለያዩ የሲቪክ ማህበራት መሪዎች የሚገኙበት መሆኑ የተዘገበ ሲሆን ከእነዚህም መካከል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የቀበሌ መሪ (ቄስ) ይገኙበታል።1 የአማራ ክልል መንግሥት ድርጊቱን በመኮነን መግለጫ ያወጣ ሲሆን 16ቱ ሰላማዊ ሰዎች ታጣቂዎቹ እንዳሉት በሰኔ ወር መገባደጃ ላይ በባህርዳር በተካሄደ የሰላም ጉባኤ ላይ የተቋቋመው የሰላም ኮሚቴ አባል አይደሉም ብሏል።2 ከዚሁ ጋር የተያያዘ ሌላ ዘገባ ሰላማዊ ሰዎቹ ባህርዳር የሄዱት በአንድ መንግሥታዊ ባልሆነ ድርጅት በተዘጋጀ ስልጠና ላይ ለመሳተፍ መሆኑን አመላክቷል።3

በአማራ ክልል ሳምንቱን ሙሉ ግጭቶች የቀጠሉ ሲሆን በደቡብ ጎንደር፣ ምስራቅ ጎጃም፣ ምዕራብ ጎጃም፣ ማዕከላዊ ጎጃም፣ ደቡብ ወሎ እና ሰሜን ወሎ ዞኖች በፋኖ ታጣቂዎች እና በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መካከል ውጊያዎች መደረጋቸው ተዘግበዋል። በባህርዳር የከተማ አስተዳደርሩ የፀጥታ ስጋቶችን በምክንያትነት በመጥቀስ በምሸት የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ላይ የሰዓት እላፊ ጥሏል።4

ኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ላይ የተከሰቱ ውጊያዎች 

በሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ የኦሮሚያ እና የአማራ ክልሎች አዋሳኝ  አቅራቢያ ሐምሌ 17 ቀን የፋኖ ታጣቂዎች መሆናቸው የተጠረጠሩ ታጣቂዎች የኦሮሞ ማህበረሰብ ተወላጆች ላይ የፈፀሙትን ጥቃትን ተከትሎ የአካባቢው የቀበሌ ታጣቂዎች እና የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ምላሽ የሰጡ ሲሆን በዚህም በሁለቱ ቡድኖች መካከል የሰው የህይወት ህልፈት ያስከተለ ውጊያ ተደርጓል። የፋኖ ታጣቂዎች በኦሮሚያ የፀጥታ ኃይሎች ወደኋላ እንዲመለሱ ከመደረጋቸው በፊት ቢያንስ ሶስት ሰላማዊ ሰዎችን መግደላቸው ተነግሯል። 

በመንግሥት እና በኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት (ኦነሠ) — በመንግሥት የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ)-ሸኔ ተብሎ የሚጠራ — መካከል በሚያዝያ 2015 ይደረግ የነበረው የመጀመሪያ ዙር የሰላም ንግግር አለመሳካቱን ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን ውስጥ ያለው ግጭት ጨምሯል። የግጭቶቹ መጨመር ከኦነሠ/ኦነግ-ሸኔ ጋር የተያያዘ ነው፤ ይሁን እንጂ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የፋኖ ታጣቂዎች በአካባቢው ሰላማዊ ሰዎችን ኢላማ ያደረጉ ጥቃቶችን መፈፀም እና ከኦነሠ/ኦነግ-ሸኔ ጋር መጋጨትን ጨምሮ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች ላይ መሳተፍ ጀምረዋል። እ.ኤ.አ በ2024 (ከታኅሣሥ 2016 ጀምሮ) አክሌድ በዞኑ ፋኖን ያሳተፉ 14 ውጊያዎችን መዝግቧል። በመሆኑም እ.ኤ.አ በ2024 (ከታኅሣሥ 2016 ጀምሮ) የሰሜን ሸዋ ዞን በሀገሪቱ ካሉ ከፍተኛ ግጭት ከሚታይባቸው አካባቢዎች መካከል አንዱ ሆኗል።

ኢትዮጵያ በጨረፍታ
ሐምሌ 13-19, 2016

ይህ መረጃ/ዳታ ከሐምሌ 13-19, 2016 ያለውን ጊዜ ይሸፍናል። አክሌድ መረጃን እንዴት እንደሚሰበስብ እና ኩነቶችን እንዴት እንደሚመድብ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የአክሌድን የኮድ መጽሐፍን ይመልከቱ። በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ የተከሰቱ አንዳንድ ኩነቶች በዘገባ መዘግየት ምክንያት በሚቀጥሉት ሳምንታት ዳታ ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ።

  • የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች: 39
  • -11% ከባለፈው ሳምንት ጋር ሲነፃፀር
  • የሰልፍ ኩነቶች: 0
  • -100% ከባለፈው ሳምንት ጋር ሲነፃፀር
  • የኩነት አይነቶች

የኩነት አይነቶች

  • ውጊያዎች: 25 ኩነቶች
  • ፍንዳታዎች/ የርቀት ግጭት: 2 ኩነት
  • ሰላማዊ ሰዎች ላይ የደረሱ ጥቃቶች: 12 ኩነቶች
  • የአመፅ ግጭት: 0 ኩነት
  • ሰልፎች: 0 ኩነት
  • ግጭት ያለበት የተቃውሞ ሰልፍ: 0 ኩነት
Share on

Related content