ኢትዮጵያ ሳምንታዊ ዘገባ (ነሐሴ 14, 2016)
ጠቅላላ ጉባኤዎች እና የፖለቲካ ግጭቶችን የዘገምታ ማእከላዊ ለአማንደ ብሔራዊ እና ዘጋቢ ዝግመው ጣይቶዎች
Also available in English
የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
በኦሮሚያ ክልል በሰላማዊ ሰዎች ላይ የተፈፀሙ ጥቃቶች የተዘገቡ ሲሆን በጋምቤላ በክልሉ ካለው የፀጥታ ሁኔታ ጋር በተያያዘ የክልል አመራር ለውጦች ተደርገዋል። በትግራይ ክልል በትግራይ ህዝብ ነፃነት ግንባር (ትህነግ/ህወሓት) ውስጥ የተፈጠረው ክፍፍል አንደኛው ቡድን አወዛጋቢ የሆነ ጉባኤ ማድረጉን ተከትሎ ልዩነቱ ሰፍቷል።
በኦሮሚያ ክልል ታጣቂዎች በሰላማዊ ሰዎች ላይ የፈፀሙት ጥቃት
በኦሮሚያ ክልል በታጣቂ ቡድኖች በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚፀሙ ጥቃቶች የቀጠሉ ሲሆን የሰዎችን ሞት አስከትሏል። ነሐሴ 7 ቀን የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት (ኦነሠ) አባላት መሆናቸው የተጠረጠሩ — በመንግሥት የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ)-ሸኔ ተብሎ የሚጠራው — በአርሲ ዞን አሰኮ ወረዳ ሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት በመፈፀም ቢያንስ ሶስት ሰዎችን ገድሏል። ከተጎጂዎች መካከል አንዱ የኦርቶዶክስ ቄስ ነው። በጥቃቱ ምክንያት 400 የሚሆኑ አባወራዎች ተፈናቅለዋል。1
የኢትዮጵያ ፖለቲካ ምህዳር እየተካረረ በሄደ ቁጥር የተለያዩ ቡድኖች የኃይማኖት ተቋማትን መሳሪያ ሊያደርጉ የሚችሉ ሲሆን የኃይማኖት አናሳ ቡድኖች የጥቃት ሰለባ መሆናቸው ሊቀጥል ይችላል (ኢፒኦ ወርሀዊ: ከመጋቢት 23 እስከ ግንቦት 23, 2014)።
የትግራይ እና ጋምቤላ ክልሎችን የተመለከቱ የፖለቲካ ዘገባዎች
በትግራይ ክልል በደብረጽዮን ገብረሚካኤል የሚመራው ትህነግ/ህወሓት ቡድን የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ እና ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ጉባኤው የፓርቲውን የምዝገባ ሂደት ለማጠናቀቅ የተቀመጡ ድንጋጌዎችን ያልተከተለ መሆኑን በመግለጽ የሰጡትን ማስጠንቀቅያዎችን ችላ በማለት 14ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን አድርጓል። ይህ ጠቅላላ ጉባኤ ደብረጽዮንን በድጋሚ የፓርቲው ሊቀመንበር አደርጎ...
ኢትዮጵያ በጨረፍታ
ነሐሴ 4-10, 2016
ይህ መረጃ/ዳታ ከነሐሴ 4 እሰከ 10, 2016 ያለውን ጊዜ ይሸፍናል። አክሌድ መረጃን እንዴት እንደሚሰበስብ እና ኩነቶችን እንዴት እንደሚመድብ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የአክሌድን የኮድ መጽሐፍን ይመልከቱ። በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ የተከሰቱ አንዳንድ ኩነቶች በዘገባ መዘግየት ምክንያት በሚቀጥሉት ሳምንታት ዳታ ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ።
የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች: 35...
የኩነት አይነቶች
ውጊያዎች: 25 ኩነቶች
ፍንዳታዎች/ የርቀት ግጭት: 0 ኩነት
ሰላማዊ ሰዎች ላይ የደረሱ ጥቃቶች: 10 ኩነቶች
የአመፅ ግጭት: 0 ኩነት
ሰልፎች: 1 ኩነት
ግጭት ያለበት የተቃውሞ ሰልፍ: 0 ኩነት
