Skip to main content

ኢትዮጵያ ሳምንታዊ ዘገባ (ነሐሴ 7, 2016)

በትግራይ ክልል የተፈጠረ ልዩነት ባለፈው ሳምንት የተጨመረ ሲሆን በአማራ ክልል ውጊያዎች እና ጥቃቶች ተመዝግበዋል።

19 September 2024

Also available in English

የሁኔታዎች አጭር መግለጫ

ትግራይ ህዝብ ነፃነት ግንባር (ትህነግ/ህወሓት) ከፍተኛ አመራሮች መካከል የተፈጠረው ልዩነት ባለፈው ሳምንት የበለጠ የሰፋ ሲሆን ይኽውም በትግራይ ክልል ተጨማሪ አለመረጋጋት እንዳይፈጥር ስጋት ደቅኗል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በአማራ ክልል ውጊያዎች እና ሰላማዊ ሰዎችን ኢላማ ያደረጉ ጥቃቶች መከሰታቸው ተዘግቧል።

ትህነግ/ህወሓት ወደ ቀድሞ ፓርቲነት እንደገና ለመመለስ ያቀረበው ጥያቄ ውድቅ ተደረገ

ነሐሴ 3 ቀን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ትህነግ/ህወሓት ወደ ቀድሞ ፓርቲነቱ ለመመለስ ያቀረበውን ጥያቄ ውድቅ ያደረገ ሲሆን በምትኩ ፓርቲውን ‘በልዩ ሁኔታ’ ስር መዝግቦታል。

1 በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መሠረት ፓርቲው በግጭት ውስጥ በመሳተፋቸው ምክንያት የተሰረዙ ፓርቲዎችን ወደ ቀድሞ ፓርቲናታቸው ለመመለስ የህግ ገደብ በመኖሩ ወደ ነበሩበት መመለስ አይቻልም。2 ፓርቲው ከሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በፊት ወደ ነበረበት ደረጃ ለመመለስ ያቀረበው ጥያቄ ውድቅ በመደረጉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ትህነግ/ህወሓት የምዝገባ ሂደቱን ለማጠናቀቅ በቀጣይ ስድስት ወራት ውስጥ የጠቅላላ ጉባኤ እንዲያደርግ፣ አዲስ አምራር እንዲመርጥ እና የፓርቲውን መመሥረቻ ህግ እንዲያፀድቅ ጠይቆታል。3 በተጨማሪም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቦርድ አባላት ተሳትፎውን እና ጉባኤው ውዝግብዎችን ጠብቆ መካሄዱን ለማረጋገጥ ፓርቲው ከጠቅላላ ጉባኤ 21 ቀናትን አስቀድሞ ሊያሳውቀው እንደሚገባ አሳስቧል።

ውጊያዎች እና ሰላማዊ ሰዎችን ኢላማ ያደረጉ ጥቃቶች በአማራ ክልል

በአማራ ክልል በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል የሚደረጉ ውጊያዎች የቀጠሉ ሲሆን በአውይ፣ በምስራቅ ጎጃም፣ ምዕራብ ጎጃም፣ ሰሜን ሸዋ፣ ሰሜን ወሎ እና ደቡብ ጎንደር ዞኖች ውስጥ ውጊያዎች መደረጋቸው ተዘግቧል። በደቡብ ጎንደር ዞን ውስጥ ትልቅ ከተማ በሆነቸው እና በቢ22 አውራጎዳና ላይ በሚትገኘው በደብረ ታቦር ከተማ ከሐምሌ 27 እስከ 30 ድረስ የዘለቀ የሶስት ቀናት ውጊያ ተደርጓል።

አክሌድ ሰላማዊ ሰዎችን ኢላማ ያደረጉ ጥቃቶችንም መዝግቧል። ባለፈው ሳምንት ለገንዘብ ሲባል የታገተ የሰብዓዊ ድጋፍ ሠራተኛ ቆየት ብሎ ማንነታቸው ባልተገለፀ ታጠቂ ቡድን በሰሜን ወሎ ዞን ዳውንት ወረዳ ውስጥ ተገድሏል።10 ሐምሌ 27 ቀን የታጠቁ ሰዎች በምዕራብ ጎንደር ዞን አውላላ አኩሻራ ካምፕ አቅራቢያ ተኩስ በመክፈት የሱዳን ስደተኞችን አቁስለዋል። በክልሉ ማንነታቸው ያልተገለፀ ታጣቂዎች ስደተኞችን ኢላማ ማድረጋቸው እየጨመረ የመጣ ችግር ሆኗል። የፀጥታ ችግሩን በመቃወም በግንቦት ወር ውስጥ በሺህዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች ካምፑን ለቀው ወጥተዋል።  

ኢትዮጵያ በጨረፍታ
ሐምሌ 27-ነሐሴ 3, 2016

ይህ መረጃ/ዳታ ሐምሌ 27 እስከ ነሐሴ 3, 2016 ያለውን ጊዜ ይሸፈናል። አክሌድ መረጃን እንዴት እንደሚሰበስብ እና ኩነቶችን እንዴት እንደሚመድብ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የአክሌድን የኮድ መጽሐፍን ይመልከቱ። በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ የተከሰቱ አንዳንድ ኩነቶች በዘገባ መዘግየት ምክንያት በሚቀጥሉት ሳምንታት ዳታ ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ።

  • የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች11: 69 +81% ከባለፈው ሳምንት ጋር ሲነፃፀር
  • የሰልፍ ኩነቶች12: 0 -100% ከባለፈው ሳምንት ጋር ሲነፃፀር

  • የኩነት አይነቶች
  • ውጊያዎች: 60 ኩነቶች
  • ፍንዳታዎች/ የርቀት ግጭት: 0 ኩነት
  • ሰላማዊ ሰዎች ላይ የደረሱ ጥቃቶች: 9 ኩነቶች
  • የአመፅ ግጭት: 0 ኩነት
  • ሰልፎች: 0 ኩነት
  • ግጭት ያለበት የተቃውሞ ሰልፍ: 0 ኩነት
Country
Ethiopia
Region
Africa
Share on

Related content