Skip to main content

ኢትዮጵያ ሳምንታዊ ዘገባ (ታኅሣሥ 8, 2017)

Conflict summary and significant events in Oromia and Amhara regions.

5 February 2025

Also available in English

የሁኔታዎች አጭር መግለጫ

በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ውስጥ የ ኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት (ኦነሠ) — በመንግሥት የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) -ሸኔ ተብሎ የሚጠራው — የሱሉልታ ወረዳ ፖሊስ ኃላፊን እና ሁለት የ ኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባላትን በመግደል የወረዳውን የ ብልጽግና ፓርቲ ኃላፊን አቁስሏል። በአማራ ክልል ከመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ጋር ውጊያ እየተካሄደ ባለበት አውድ ውስጥ የ ፋኖ ታጣቂዎች በብዙ ዞኖች መንገዶች እንደዘጉ አውጅ አውጥተዋል።

በሰላም ስምምነቱ ማግስት የኦነሠ/ኦነግ-ሸኔ ታጣቂዎች የሱሉልታ ወረዳ የፖሊስ ኃላፊን ገደሉ

ኀዳር 22 ቀን በኦሮሚያ ክልል መንግሥት እና በሰኚ ነጋሳ መካከል የተደረገውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ በሰኚ ነጋሳ የሚመራው የኦነሠ/ኦነግ–ሸኔ ቡድን አባላት በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ ‘የታሃድሶ ማዕከላት’ መግባታቸውን ቀጥለዋል። ባለፈው ሳምንት ቁጥራቸው በውል ያልተገለፀ የኦነሠ/ኦነግ–ሸኔ ተዋጊዎች ከምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን ሸዋ እና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞኖች ወደ ተዘጋጀላቸው ማዕከላት ገብተዋል። ምንም እንኳን ሰኚ ነጋሳ የኦነሠ/ኦነግ–ሸኔ የማዕከላዊ ዞን አዛዥ የነበረ ቢሆንም ምዕራብ ወለጋን ከመሳሰሉ ከማዕከላዊ ዞን ኮማንድ ውጪ ከሆኑ አካባቢዎች የመጡ ተዋጊዎችም ወደ ተሃድሶ ማዕከላት እየገቡ ይገኛሉ።

ተዋጊዎቹ ወደ ህብረተሰቡ እንዲቀላቀሉ ለመርዳት ወደ ተዘጋጁላቸው ማዕከላት የሚገቡት ተወካዮቻቸው ወይም የአካባቢው የሀገር ሽማግሌዎች ታጣቂዎቹ ለሰላም ጥሪው ፍላጎት እንዳላቸው ለአካባቢ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ካሳወቁ በኋላ ነው። ከዚያም የአካባቢው የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ከአካባቢው የፀጥታ ኃይሎች እና ከመከላከያ ሠራዊት አባላት ጋር በመሆን ቀድመው በተስማሙበት ቦታ ከተዋጊዎቹ ጋር ይገናኛሉ። የሰላም ስምምነቱ ከተደረገ በኋላ ብዙ ተዋጊዎች ይህንኑ ሂደት ተጠቅመው ወደ ተዘጋጁላቸው የተሃድሶ ማዕከላት ገብተዋል።1

በአማራ ክልል በቀጠለው ውጊያ መሃል የመንገዶች መዘጋት

ኅዳር 30 ቀን የተለያዩ የፋኖ ታጣቂዎች ተወካዮች በምሥራቅ ጎጃም፣ ምዕራብ ጎጃም፣ ሰሜን ወሎ እና ደቡብ ወሎ2 ዞኖች መንገዶች እንደሚዘጉ ያስታወቁ ሲሆን ይኽውም የሰላማዊ ሰዎችን ዕለታዊ እንቅስቃሴ አስተጓጉሏል።

ኢትዮጵያ በጨረፍታ
ኅዳር 28 እስከ ታኅሣሥ 4, 2017

ይህ መረጃ/ዳታ ከኅዳር 28 እስከ ታኅሣሥ 4, 2017 ያለውን ጊዜ ይሸፍናል። አክሌድ መረጃን እንዴት እንደሚሰበስብ እና ኩነቶችን እንዴት እንደሚመድብ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የአክሌድን የኮድ መጽሐፍን ይመልከቱ። በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ የተከሰቱ አንዳንድ ኩነቶች በዘገባ መዘግየት ምክንያት በሚቀጥሉት ሳምንታት ዳታ ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ።

የኩነት አይነቶች

ውጊያዎች: 22 ኩነቶች

ፍንዳታዎች/ የርቀት ግጭት: 2 ኩነቶች

ሰላማዊ ሰዎች ላይ የደረሱ ጥቃቶች: 2 ኩነቶች

የአመፅ ግጭት: 0 ኩነት

ሰልፎች: 2 ኩነቶች

ግጭት ያለበት የተቃውሞ ሰልፍ: 0 ኩነት

Amharic - Map_Ethiopia Peace Observatory_Disorder in Ethiopia_7-13 Dec 2024_EN (17 December 2024)

Country
Ethiopia
Region
Africa
Share on

Related content